• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የአማራ ክልል ትልልቅ ከተሞች ተኩስ ዓልባ ሆነው ውለዋል

August 10, 2023 04:31 pm by Editor Leave a Comment

  • በደብረ ታቦር 800 መቶ ብር የነበረ የምግብ ዘይት እስከ 1500 ብር ድረስ እየተሸጠ ነው

በአማራ ክልል በትልልቆቹ ከተሞች በዛሬው ዕለትም ተኩስ ሳይሰማባቸው መዋላቸውን፤ ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ እንዳልተጀመረ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ነዋሪዎች ምን አሉ?

ባሕር ዳር

ዛሬ የተኩስ ድምጽ አለመሰማቱን ፤ ግጭትም ይሁን ውጊያ እንዳልነበር ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ አልጀመረም።

የንግድና የተለያዩ ቋማት በአብዛኛው ባለመከፈታቸው ከተማዋ ጭር ብላ ነው የዋለችው።

የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ መኪኖች እና ባጃጆች ወደ ሥራ ባለመመለሳቸው የነዋሪው እንቅስቃሴ ተገትቶ ውሏል።

ተቋርጦ የነበረው የ ‘ኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ’ ወደ ባሕር ዳር መጀመሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ነገር ግን ከአውሮፕላን ማረፊያ ወደ ከተማ የሚወስድ ትራንስፖርት ስለሌለ ተሳፋሪዎች በእግራቸው ለመጓዝ ተገደዋል።

አሁንም የተወሰኑ መንገዶች በትላልቅ ቋጥኖች እና ድንጋዮች እንደተዘጉ ስለሆኑ ለትራንስፖርት አስቸጋሪ ነው።

ከተማዋ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዋ ባትመለስም አንዳንድ ነዋሪዎች በእግራቸው ሲንቀሳቀሱ ውለዋል።

ደብረ ማርቆስ

በደብረ ማርቆስ ከተማ ትራንስፖርትም ሆነ የንግድ መደብሮች ወደ ስራ እንዳልተመለሱ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

“ሱቅ፣ ሆቴል ዝግ ነው።” ያሉ አንድ ነዋሪ “ምንም እንኳን በአይኔ ባላይም ጥዋት አንድ ባስ ከማርቆስ ወጥቶ ወደ አ/አ ሄዷል የሚባል ነገር አለ ፤ ከአዲስ አበባ መስመር ግን አንድ ሁለት ባሶች ማርቆስ ገብተዋል።” ሲሉ ገልጸዋል።

በደብረ ማርቆስ ወደ ጎንደር፣ ወደሌሎችም ቦታዎች የሚሄዱ ተሽከርካሪዎች እንደቆሙ ናቸው ፤ መደበኛ እንቅስቃሴም አልተጀመረም።

ደጀን

ከተማዋ አሁን ላይ የተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ ብትሆንም ሰሞኑን ከተፈጠረው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ አገልግሎቶች ተስተጓጉለዋል።

የውሃ እንዲሁም መብራት አገልግሎት ከተቋረጠ ቀናት እንደተቆጠሩ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አንድ አስተያየት ሰጪ፤ በብቸና መስመር ወደ ሞጣ የሚያልፍ በርካታ የመከላከያ ኃይል እንደተመለከቱ ገልጸዋል።

ብቸና ላይ ግጭት እንደነበር የሚጠርጥሩት ነዋሪው ሥፍራው ከደጀን ከ35 ኪሎ ሜትር ርቀት በላይ ቢሆንም የከባድ ተኩስ ድምፅ ግን ይሰማ እንደነበር ጠቁመዋል።

ጎንደር

ከትላንት ረቡዕ ጀምሮ ተኩስ እንደማይሰማና አሁን ላይ ሰላም መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ሰዎች በእግር ይንቀሳቀሱ እንጂ፣ ተሽከርካሪ የለም።  በብዛት ሱቆች እና ወፍጮ ቤቶች አገልግሎት እየሰጡ አይደለም።

በከተማው የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲከፈቱ ቢታዘዙም ሁሉም ሙሉ በሙሉ እንዳልተከፈቱ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በጎንደር የመከላከያ ሠራዊት አባላት እና ታንኮች በተለይ ደግሞ አድማ በታኞች በስፋት እንደሚታዩ ተነግሯል።

ዛሬ ወደ ጎንደር ከተማ በረራ ይጀመራል ቢባልም ወደ ከተማው አውሮፕላን እንዳልገባ ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።

ደብረ ብርሃን

በደብረ ብርሃን ሱቆች እና ትራንስፖርት ሙሉ በሙሉ ባይሆንም ወደ አገልግሎት እየተመለሱ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አንድ አስተያየት ሰጪ ከትላንት ከሰዓት ጀምሮ ባጃጅ መንቀሳቀስ መጀመሩን ጠቁመዋል። ዛሬ ደግሞ ሱቆች መከፈታቸውንና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ስራ መጀመራቸውን ገልጸዋል።

የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ፍተሻ እያደረጉ መሆኑ ተመላክቷል።

ላሊበላ

“ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ባይሆንም ” የመንግስት ሰራተኞች ወደ ስራ መግባታቸው፣ ተቋማት እና ተሽከርካሪዎች በተወሰነ ደረጃ ስራ እንደጀመሩ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ከወትሮው የተለየ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንዳልታየ የገለፁት ነዋሪዎች የአውሮፕላን በረራ እንዳልተጀመረና የበረራው መጀመር እየተጠበቀ መሆኑን ጠቁመዋል።

በላሊበላ በረራ ለመጀመር ቀናት ሊፈለግ እንደሚችል ተነግሯል።

ደብረ ታቦር

የከተማዋ እንቅስቃሴ በጣም ቀዝቃዛ ነው። ነዋሪው በጊዜ ነው ወደ ቤቱ እየገባ ያለው።

አሁን ላይ በከተማዋ ፤ ምንም ዓይነት የተኩስ ድምፅ ባይሰማም በከተማዋ የጦር መሣሪያም ሆነ ስለት ያለው ቁስ ይዞ መንቀሳቀስም ሆነ መገኘት አደጋ እንደሆነ ነዋሪዎች ገልጻዋል። ይህን ይዞ የተገኘ ሰው እርምጃ ይወስድበታል ብለዋል።

ሆቴሎችና ባንኮች ዝግ እንደሆኑ ይገኛሉ።

ምንም እንኳን በከተማው ላይ የተረጋጋ ሁኔታ ቢኖርም 800 መቶ ብር የነበረ የምግብ ዘይት እስከ 1500 ብር ድረስ እየተሸጠ እንዳለ፤ ይሄም ቢሆን ሱቆች አሁንም ዝግ ስለሆኑ በሰው በሰው የሚገኝ እንደሆነ ተጠቁሟል።

መረጃው ከኤኤፍፒ፣ ዶቼቨለ፣ ቢቢሲ የተሰባሰበ ነው።

ማስታወሻ፤ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ፦

– በባህር ዳር ፣

– በደብረ ማርቆስ፣

– በደብረ ብርሃን፣

– በላሊበላ ፣

– በጎንደር ፣

– በሸዋሮቢት ከባጃጆችና ከሞተር ሳይክሎች በስተቀር ሌሎች የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ከነሐሴ 4 ጀምሮ ወደ ሥራ የመመለስ እና አገልግሎት የመስጠት ግዴታ እንደተጣለባቸው ማሳወቁ ይታወሳል።

ከዚህም በተጨማሪ፤ የሕዝብ የአገልግሎት ሰጪ፣ የመንግሥት፣ የማኅበረሰብና የንግድ ተቋማት ከነሐሴ 4/2015 ጀምሮ ክፍት እንዲሆኑ ማዘዙ አይዘነጋም። (tikvahethiopia)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: ethiopian terrorists, Fake Fano, Jawissa, operation dismantle tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
Copyright © 2026 · Goolgule