
* ሸኔም ላይ ጉዳት ደርሷል ተብሏል
በሁሉም የጎጃም ዞኖች እና በደቡብ ጎንደር የሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት ክፍሎች በፋኖ ላይ በወሰዱት እርምጃ አመራሮችን ጨምሮ በርካታዎችን መግደላቸው፣ መማረካቸው እንዲሁም መሥሪያዎችንና ተተኳሾችን መማረካቸውን የመከላከያ ሠራዊት በማኅበራዊ ገጹ አስታውቋል። በሸኔም ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በ6ኛ ዕዝ የኮር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ጋዲሳ ዲሮን ጠቅሶ፤ በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ በፅንፈኛው እና አሸባሪው ሸኔ ላይ የምንወስደውን እርምጃ አጠናክረን ቀጥለናል አመርቂ ውጤትም ተገኝቷል ይላል የወጣው መረጃ። ከዚህም በተጨማሪ ኮሎኔል ጋዲሳ ዲሮ ሰሞኑን በፅንፈኛ ቡድኑ ላይ ከፍተኛ እርምጃ በመውሰድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሣራ ማድረስ ተችሏል ማለታቸውን ዘግቧል።
በፋኖ ላይ የደረሰውን በተመለከተ፤ መረጃው የምስራቅ ዕዝ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ተሾመ አስማማውን ጠቅሶ ሲናገር፤ “የሠራዊታችን ክፍሎች በተሰማሩባቸው ቀጣናዎች የኅብረተሰቡ የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ እንዳይስተጓጎልና የተጀመሩ መሠረተ-ልማቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማስቻል ፅንፈኛውን የማጥፋት ተልዕኮ” ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል።
ድል የተገኘባቸው አካባቢዎች
- በሰሜን ጎጃም ዞን
- ይልማና ደንሳ ወረዳ
- ደብረማዊ፣ ሰንቀኛ አዜት፣ ቆቀርና በዜት አብካ ቀበሌዎች
- ይልማና ደንሳ ወረዳ
- በምስራቅ ጎጃም ዞን
- በሸበል በረንታ ወረዳ
- ቁጥቋጥና ኪርኩበት ቀበሌ
- በሸበል በረንታ ወረዳ
- በምዕራብ ጎጃም ዞን
- በደጋዳሞት ወረዳ
- ፈላጢት፣ ቋቁቻና ቡና ቀበሌ
- በአዊ ዞን ጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ
- አሸፋና አጉት ቀበሌ
- በደጋዳሞት ወረዳ
- በደቡብ ጎንደር ዞን
- ሰዴ ሙጃ ወረዳ
- አዳዲና ወለል ባህር ቀበሌዎች
- ፎገራ ወረዳ
- መነጉዘር ቀበሌዎች ላይ የተሰማሩት አሀዱዎችም አመርቂ ግዳጆችን አስመዝግበዋል ብሏል።
- ሰዴ ሙጃ ወረዳ
መረጃው እርምጃ የተወሰደባቸውን አመራሮች በሚከተለው መልኩ አቅርቧል፤
- በፅንፈኞች አደረጃጀት የፅንፈኛው ሻለቃ መሪ ፈንታው ሽታው
- የአገው ምድር ዘመቻ አስተባባሪ ሰለሞን
- የዘንገና ብርጌድ አዛዥ ፅጋይ አጥናፉ
- የፅንፈኛው ቡድን ሎጂስቲክስ ኃላፊ መንጌ ይርዳው
- የአፄ ፋሲል ተወርዋሪ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ የነበረ ዳንኤል አሰፋ
- እንዲሁም ሌሎች በርካታ የጽንፈኛው አመራሮች እና አባላቶች ተደምስሰዋል።
በአጠቃላይ የደረሰውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሣራ የመከላከያ ሠራዊት መረጃ በሚከተለው መልኩ በዝርዝር አስታውቋል፤ በዚህ ዘመቻ
- 95 የፅንፈኛውን ኃይል አባላት ሲደመሰሱ
- 29 ቆስለዋል
- 2 ተማርከዋል
- 2ሺህ 354 ልዩ ልዩ ተተኳሽ
- 15 ኤ ኬ ኤም
- 36 ኋላ ቀር መሳሪያ
- ሶስት ቦምብ
- ስምንት ትጥቅ
- ስድስት የኤ ኬ ኤም ካዝና
- አንድ ጄኔሬተርና ሶስት ተሸከርካሪ በቁጥጥር ስር ውለዋል፤ 50 አባላቱም እጅ ሰጥተዋል።
በአሁኑ ጊዜ በተበታተነ አደረጃጀት ላይ የሚገኘው የፋኖ ሁኔታ ወደ ማኅበራዊ ሽፍታነት እየተቀየረ መምጣቱ ይነገራል። በተለይ በሕዝብ ላይ የሚያደርሰው ግፍ ማኅበረሰቡን ለከፍተኛ ችግር የጋረጠው በመሆኑ መከላከያ በሚወስደው እርምጃ ላይ የየአካባቢው ሕዝብ በንቃት እየተሳተፈ እንደሆነ በስፋት ይነገራል። በዚህ በሁሉም የጎጃም ዞኖች እና በደቡብ ጎንደር ለተገኘውም ድል የኅብረተሰቡ ከሠራዊቱ ጎን መሰለፍ እንደ ማስረጃ የሚጠቀስ ነው።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply