የእስክንድር አፋሕድ ጥሪ አቀረበ ለበርካታ ወራት ኅብረት ለመፍጠር ታስቦ ሲሠራበት የቆየው የአማራ ፋኖ ኅብረት በቋራ ጎንደር መመሥረቱ ተሰምቷል። የኅብረቱ ዓላማና ግብ ወደ አንድነትን ለማምጣትና የተቀናጀ ጥቃት ለመሰንዘር ሳይሆን ዓቅምን አስተባብሮ ለድርድር ለመቅረብ የታለመ እንደሆነ እየተነገረ ነው። እስክንድር ነጋ የሚመራው አፋሕድ ባወጣው መግለጫ “ከተቻለ እንዋሃድ፣ ካልሆነም አንቀናጅ ካልሆነ ቢያንስ እናበብ” ብሏል። ከጎንደር፣ ከሸዋ፣ ከወሎና ከጎጃም የተሰባሰቡ የፋኖ አመራሮች ባደረጉት ውይይት አንድ የፋኖ አደረጃጀት መመሥረታቸውን ተናግረዋል። ስሙንም አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) በማለት መሰየማቸውን አስታውቀዋል። የወጣው መግለጫ እንደሚለው “የአማራ ፋኖ በጎጃም፣ የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ - አማራ)፣ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር እና የአማራ ፋኖ … [Read more...] about የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ

