የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ መስከረም 15/2013 ዓ.ም ባካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባው፣ በከተማዋ የተጀመረውን ትምህርት ተሞክሮ እና አገልግሎቶች በአካታች ልማት (inclusive development) መርህ መሰረት አዲስ አበባ ዙሪያ ልዩ ዞን ወይም የኦሮሞ ብልጽግና “የፊንፊኔ ልዩ ዞን” በሚል መጠሪያ ባካተታቸው አካባቢዎች በሚገኙ 346 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚማሩ አንድ መቶ ሃምሳ ሁለት ሺህ(152,000) ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ፣ የተማሪ ደንብ ልብስ፣ጫማ እና የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችል 669,210,780 (ስድስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሚልዮን ሁለት መቶ አስር ሽህ ሰባት መቶ ሰማንያ ብር) በጀት በመመደብ ለእርዳታ አገልግሎቱ እንዲውል በልዩ ሁኔታ ውሳኔ አሳልፏል። ፓርቲያችን ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ … [Read more...] about የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ወቅታዊ መግለጫ
balderas
አዲስ አበባ በክልልነት እንድትደራጅ ባልደራስ የፓርቲዎችን ድጋፍ ጠየቀ
አዲስ አበባ በራሷ ግዛተ-መሬት ላይ የፌዴራል አድያምነት /ክልልነት/ መደራጀት በተመለከተ ባልደራስ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በትብብር ለመስራት ለፓርቲዎች ጥያቄ አቅርቧል። ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ትላንት ባወጣው ደብዳቤ እንደጠየቀው የአዲስ አበባን ህልውና ለማስጠበቅ በሚደረገው ታሪካዊ ጉዞ እንዲሳተፉ ለ10 ፓርቲዎች ጥሪውን አቅርቧል። ይህ ባልደራስ ለብልጽግና፤ ለመኢአድ፤ ለኢዜማ፤ ለአብን፤ ለመድረክ፤ ለአረና፤ ለትዴፓ፤ ለኦብነግ እና ሌሎች ፓርቲዎች ባቀረበው ጥሪ ፓርቲዎቹ መስከረም 20፤ ከ4 ሰዓት ጀምሮ ለሚደረገው ውይይት ፓርቲያቸውን የሚወክሉ 3 አመራሮችን እንዲልኩ ጥሪ አድርጓል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about አዲስ አበባ በክልልነት እንድትደራጅ ባልደራስ የፓርቲዎችን ድጋፍ ጠየቀ