
አዲስ አበባ በራሷ ግዛተ-መሬት ላይ የፌዴራል አድያምነት /ክልልነት/ መደራጀት በተመለከተ ባልደራስ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በትብብር ለመስራት ለፓርቲዎች ጥያቄ አቅርቧል።
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ትላንት ባወጣው ደብዳቤ እንደጠየቀው የአዲስ አበባን ህልውና ለማስጠበቅ በሚደረገው ታሪካዊ ጉዞ እንዲሳተፉ ለ10 ፓርቲዎች ጥሪውን አቅርቧል።

ይህ ባልደራስ ለብልጽግና፤ ለመኢአድ፤ ለኢዜማ፤ ለአብን፤ ለመድረክ፤ ለአረና፤ ለትዴፓ፤ ለኦብነግ እና ሌሎች ፓርቲዎች ባቀረበው ጥሪ ፓርቲዎቹ መስከረም 20፤ ከ4 ሰዓት ጀምሮ ለሚደረገው ውይይት ፓርቲያቸውን የሚወክሉ 3 አመራሮችን እንዲልኩ ጥሪ አድርጓል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply