በአዲስ አበባ 1 ሺሕ 338 ሄክታር መሬት አሁንም በወረራ ተይዞ እንደሚገኝ አስተዳደሩ አስታወቀ። የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ በህገወጥ መሬት ወረራ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። ወይዘሮ አዳነች በዚህ ጊዜ እንዳሉት በአዲስ አበባ ካሉ 121 ወረዳዎች ውስጥ በ88ቱ የመሬት ወረራ ተፈጽሟል። በአጠቃላይ በከተማዋ 1 ሺህ 338 ሄክታር መሬት የተወረረ ሲሆን በተደረገው የህንጻ ቆጠራ 322 ህንጻዎች እና ቤቶች ባለቤት አልባ መሆናቸውን ወይዘሮ አዳነች ተናግረዋል። ወይዘሮ አዳነች በዚህ ጊዜ እንዳሉት በአዲስ አበባ በህገወጥ መንገድ 21 ሺህ 695 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በህገወጥ መንገድ ተይዘው መገኘታቸውን ተናግረዋል። ከዚህ ቤቶች ውስጥ 15 ሺህ 891 ቤቶች የባለቤትነት መረጃ አልቀረበባቸውም። 850 ቤቶች ደግሞ ዝግ ሆነው ሲገኙ 4 ሺህ 530ዎቹ ደግሞ ባዶ … [Read more...] about በአዲስ አበባ የተወረረው መሬት፣ ባለቤት አልባ ቤቶችና ሕንጻዎች ይፋ ሆኑ
addis ababa land grab
ኢዜማ በአዲስ አበባ አስተዳደር ላይ ክስ መሠረተ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሰሰ። ፓርቲው ክሱን የመሰረተው የከተማው አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት በሰጠው ትዕዛዝ፤ የፓናል ውይይት እንዳያደርግ መከልከሉን በመቃወም ነው። በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ፍትሐ ብሔር ችሎት ባለፈው አርብ መስከረም 30፤ 2013 የተከፈተው የክስ መዝገብ፤ በፓርቲው ላይ የደረሰው “የሁከት ተግባር እንዲታገድ” የሚጠይቅ ነው። ኢዜማ ይህን ክስ ለማቅረብ የተገደደው ሕገ መንግስታዊ የሆነው “የመሰብሰብ መብት” በተከሳሽ መስሪያ ቤት በተሰጠ ትዕዛዝ በመገደቡ መሆኑን ገልጿል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ለክስ ያበቃውን ትዕዛዝ ለፓርቲው የጻፈው ባለፈው ሳምንት ሰኞ መስከረም 25፤ 2013 ነበር። … [Read more...] about ኢዜማ በአዲስ አበባ አስተዳደር ላይ ክስ መሠረተ
አዲስ አበባ ብዙ ዋጋ የተከፈለባት ከተማ
1. መግቢያ፣ አዲስ አበባ ብዙ ዋጋ ተከፍሎባታል ሲባል ነገር ለማጣፈጥ የተነገረ ወሬ ሳይሆን በተጨባጭ የሆነና የተደረገ መሆኑን እኔ በህይወቴ ያየሁትን እንዲት ገተመኝ እንደ ምሳሌ ልጥቀስ። ስሜ ደረጀ ተፈራ ይባላል ተወልጄ ያደኩት አዲስ አበባ ፊትበር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው። ሰፈራችን ለታላቁ ቤተመንግስት (ምኒልክ ቤ/መ) ቅርብ በመሆኑ የደርግ ቅልብ ወታደሮችም ሆኑ የወያኔ አጋዚ ጦር የአካባቢውን ጸጥታ ለማስከበር ብቻ ሳይሆን ኮረዶችንም ለማሽኮርመም እኛ ሰፈር አይጠፉም ነበር። በደርግም ሆነ በወያኔ አገዛዝ ዘመን አንድ ነገር ኮሽ ባለ ቁጥር ከቤተ መንግስት፣ የደርግ ቅልቦችና የወያኔ አጋዚ ጦር፣ ከውጭ ጉዳይ ሚ/ር አና ከፓሊስ ገራዥ ደግሞ ፌዴራል ፖሊሶች ክላሻቸውን እያንቀጫቀጩ መጀመሪያ የሚመጡት እኛ ሰፈር ነበር። በዚህ ላይ ኮ/ል መንግሥቱ … [Read more...] about አዲስ አበባ ብዙ ዋጋ የተከፈለባት ከተማ
አዲስ አበባ በክልልነት እንድትደራጅ ባልደራስ የፓርቲዎችን ድጋፍ ጠየቀ
አዲስ አበባ በራሷ ግዛተ-መሬት ላይ የፌዴራል አድያምነት /ክልልነት/ መደራጀት በተመለከተ ባልደራስ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በትብብር ለመስራት ለፓርቲዎች ጥያቄ አቅርቧል። ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ትላንት ባወጣው ደብዳቤ እንደጠየቀው የአዲስ አበባን ህልውና ለማስጠበቅ በሚደረገው ታሪካዊ ጉዞ እንዲሳተፉ ለ10 ፓርቲዎች ጥሪውን አቅርቧል። ይህ ባልደራስ ለብልጽግና፤ ለመኢአድ፤ ለኢዜማ፤ ለአብን፤ ለመድረክ፤ ለአረና፤ ለትዴፓ፤ ለኦብነግ እና ሌሎች ፓርቲዎች ባቀረበው ጥሪ ፓርቲዎቹ መስከረም 20፤ ከ4 ሰዓት ጀምሮ ለሚደረገው ውይይት ፓርቲያቸውን የሚወክሉ 3 አመራሮችን እንዲልኩ ጥሪ አድርጓል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about አዲስ አበባ በክልልነት እንድትደራጅ ባልደራስ የፓርቲዎችን ድጋፍ ጠየቀ
ከመሬት ጋር በተያያዘ ጉቦኞች እጅ ከፍንጅ እየተያዙ ነው
በጉለሌ ክፍለከተማ ከመሬት ጋር በተያያዘ አገልግሎት ለማግኘት ወደ መስሪያ ቤቱ የሄዱ ተገልጋዮችን ጉዳይ እናስፈጽማለን በሚል ጉቦ ሲቀበሉ የተገኙ ግለሰቦች በትላንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ በወንጀል ድርጊቱ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ከክፍለከተማ እስከ ወረዳ ከተዘረጋው ሠንሠለት በተጨማሪ ደላሎችም ይገኙበታል፡፡ የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ከተገልጋዮቹ ጋር በመሆን ባደረገው ተከታታይ ክትትል ለአገልግሎት እንዲከፈላቸው የጠየቁትን ገንዘብ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ኅብረተሰቡም በህጋዊ መንገድ ማግኘት የሚችለውን አገልግሎት ገንዘብ በመቀበል በህገ-ወጥ መንገድ አገልግሎት የሚሰጡ የመንግስት አካላትን በማጋለጥ ግዴታውን እንዲወጣ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን አቅርቧል፡፡ የወንጀል ድርጊቱን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎች በፌዴራል ፖሊስ … [Read more...] about ከመሬት ጋር በተያያዘ ጉቦኞች እጅ ከፍንጅ እየተያዙ ነው
አዲስ አበባን “irrelevant” በማድረግ ሥራ የሽመልስና የታከለ መናበብ
ሽመልስ አብዲሣ በድብቅ የተናገረውና ለዓላማቸው ሲሉ በቅርቡ አፈትልኮ እንዲወጣ ያደረጉ ወገኖች በለቀቁት መረጃ አዲስ አበባን አስመልክቶ ሽመልስ ይህንን ብሎ ነበር፤ “አዲስ አበባ ላይ መፍትሄ የሚያመጣው ሶስት ነገር ነው፣ “አንደኛው ሰውን ማስፈር ነው፣ በስራ፣ ከማውራት በስራ፣ አትጠይቁን የምንችለውን እያደረግን ነው። “ሁለተኛው አዲስ አዲስ አበባን irrelevant ማድረግ ነው። አዲስ አበባን irrelevant ለማድረግ እየሰራን ነው። ከተሳካልን ከምርጫ በኋላ የፌዴራል መንግስቱን መቀመጫ፣ አራት አምስት ቦታ ለመክፈል እንፈልጋለን። “ዝም ብሎ አዲስ አበባን በስራችን እናስገባለን ብሎ መለፍለፍ አይደለም። እንዴት ታደርገዋለህ ፣ ፈንጂውን እንዴት ታፈነዳዋለህ? አሁን እኛ ኦሮሚያ ከልክ በላይ እየለማች ነው፣ ሌላው ክልል ከልክ በላይ እየተጎዳ ነው። ይህ ደግሞ እየሆነ … [Read more...] about አዲስ አበባን “irrelevant” በማድረግ ሥራ የሽመልስና የታከለ መናበብ
በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላን አስመልክቶ የተደረገ ጥናት ውጤት
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በአዲስ አበባ ከተማ የሚፈፀም የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላ ጋር በተያያዘ ያደረገውን ጥናት ውጤት ይፋ አድርጓል። የጥናቱ ውጤት ዋነኛ ይዘት ከዚህ በታች ተቀምጧል። በአዲስ አበበ ከተማ መሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላ ጥናት አንኳር፥ • የከተማው አስተዳደር እያየና እየሰማ በሕገ ወጥ እና በተደራጀ መልኩ በወረራ የተያዙ ቦታዎች በፍጥነት ካርታና ፕላን ተሰርቶላቸው ለ3ተኛ ወገን በሽያጭ ተላልፈዋል። በማኅበር እና በግል ለማምረቻና ለንግድ አገልግሎት እንዲውሉ ተደርገዋል፤ በምንም መስፈርት የቤት ተጠቃሚ ሊሆኑ የማይገባቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ቤት እና የነዋሪነት መታወቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ • በዋናነት በመሬት ወረራው ላይ ግንባር ቀደም ተሳታፊ የነበሩት ሰዎች የአርሶ አደር ልጆች … [Read more...] about በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላን አስመልክቶ የተደረገ ጥናት ውጤት
ኢዜማ፡ በአዲስ አበባ 210ሺህ ካሬሜትር በላይ መሬት ተወርሯል፥ 95ሺህ በላይ ኮንዶ ለማይገባቸው ተሰጥቷል
በአዲስ አበባ በአምስት ክፍለ ከተሞች ብቻ ከ210 ሺህ ካሬ ሜተር በላይ መሬት መወረሩን ኢዜማ አስታወቀ። ፓርቲው አደረኩት ባለው ጥናት በ2012 በጀት ዓመት መስከረም ወር ላይ ለባለዕድለኞች ወጥተዋል ያላቸው ከ95 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቤቱ ለማይገባቸው ሰዎች መተላለፉንም አስታውቋል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ በአዲስ አበባ ህገወጥ የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች እደላን በሚመለከት ለአንድ ወር አደረኩት ያለውን የጥናት ግኝት ዛሬ ይፋ አድርጓል። እንደ ፓርቲው ጥናት መሰረት ከሆነ በአዲስ አበባ አምስት ክፍለከተሞች ማለትም የካ፣ ቦሌ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች ከ210 ሺህ በላይ ካሬ ሜትር ቦታዎች በመንግስት አመራሮች ድጋፍ ተወረዋል። ይህ መሬት ገሚሱ በመንግስት ተቋማት ድጋፍ ጭምር ካርታ … [Read more...] about ኢዜማ፡ በአዲስ አበባ 210ሺህ ካሬሜትር በላይ መሬት ተወርሯል፥ 95ሺህ በላይ ኮንዶ ለማይገባቸው ተሰጥቷል
ፈራሚዋ ሚኒስትር የሉም በሚል ኢዜማ መግለጫ እንዳይሰጥ በድጋሚ ተከለከለ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ኢዜማ በአዲስ አበባ እየተደረገ ነው ያለውን የመሬት ወረራና ህገ-ወጥ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እደላ በተመለከተ ሊሰጠው የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ለሁለተኛ ጊዜ ተከለከለ፡፡ የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ እንዳሉት ጋዜጣዊ መግለጫው የተከለከለው መግለጫ የሚሰጥበት ቦታ የሆነው ራስ ሆቴል ከሰላም ሚኒስቴር የተፃፈ ደብዳቤ ስጡኝ በማለቱ፤ የሰላም ሚኒስትር ደግሞ ደብዳቤ ለመፃፍ ባለመፍቀዱ ነው ሲሉ ነግረውናል፡፡ ፓርቲው ለሁለተኛ ጊዜ መግለጫ እንዳይሰጥ ስለተከለከለ፣ መግለጫውን በፅ/ቤቱ ዛሬ ከሰዓት በኋላ እንደሚሰጥ አቶ ናትናኤል ፈለቀ ነግረውናል፡፡ ሸገር ይህንኑ ጉዳይ ለማጣራት ወደ ሰላም ሚኒስትር ቢሮ ደውዬ ተነገረኝ እንዳለው፣ የሚኒስትሯ ፅህፈት ቤት ፈቃዱን የሚሰጠው አካል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚኒስትሮች … [Read more...] about ፈራሚዋ ሚኒስትር የሉም በሚል ኢዜማ መግለጫ እንዳይሰጥ በድጋሚ ተከለከለ