በጉለሌ ክፍለከተማ ከመሬት ጋር በተያያዘ አገልግሎት ለማግኘት ወደ መስሪያ ቤቱ የሄዱ ተገልጋዮችን ጉዳይ እናስፈጽማለን በሚል ጉቦ ሲቀበሉ የተገኙ ግለሰቦች በትላንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
በወንጀል ድርጊቱ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ከክፍለከተማ እስከ ወረዳ ከተዘረጋው ሠንሠለት በተጨማሪ ደላሎችም ይገኙበታል፡፡
የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ከተገልጋዮቹ ጋር በመሆን ባደረገው ተከታታይ ክትትል ለአገልግሎት እንዲከፈላቸው የጠየቁትን ገንዘብ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ኅብረተሰቡም በህጋዊ መንገድ ማግኘት የሚችለውን አገልግሎት ገንዘብ በመቀበል በህገ-ወጥ መንገድ አገልግሎት የሚሰጡ የመንግስት አካላትን በማጋለጥ ግዴታውን እንዲወጣ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
የወንጀል ድርጊቱን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎች በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ በኩል ለህዝብ ይፋ የሚደረጉ ይሆናል።
በሌላ በኩል ኤፍሬም አለሙ የተባለ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 03 አስተዳደር የግንባታ ፍቃድ ጽኅፈት ቤት ሃላፊ ለተገልጋይ ህገ ወጥ የግንባታ ፍቃድ ለመስጠት በ140 ሺህ ብር ተዋውለው ተበዳዩ አልችለም በማለታቸው 60ሺ ግን ሊቀብል ሲል እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ሥር ውሏል፡፡
ባለጉዳዩ ለከንቲባ ጽ/ቤት እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባደረሰው ጥቆማ ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር በተደረገ ክትትል የጽህፈት ቤት ሃላፊውን ገንዘቡን ሲቀበል በቁጥጥር ስር መዋሉን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወንጀል ክትትል ሃላፊ ኮማደር አወሉ አህመድ ተናግረዋል፡፡
ይህ መረጃ ከተሰማ በኋላ ፖሊስ ተጨማሪ መረጃ ሰጥቷል፥….
ኤፍሬም አለሙ የተባለው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 03 አስተዳደር የግንባታ ፍቃድ ጽኅፈት ቤት ሃላፊ ለተገልጋይ ህገ ወጥ የግንባታ ፍቃድ ለመስጠት 140 ሺህ ብር ሲቀበል እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ሥር ውሏል፡፡
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 3 አስተዳደር የግንባታ ፈቃድ ቁጥጥር ሃላፊ የሆነው ግለሰብ በቁጥጥር ስር የዋለው ዛሬ ነሃሴ 27 ቀን 2012 ዓም ነው፡፡
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ተወካይ ሃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር እሸቱ ቅጣው እንዳስረዱት ዶ/ር አድል አብደላ የተባሉት የግል ተበዳይ በረንዳ ለመስራት ፈልገው ወደ ወረዳው በመሄድ የግንባታ ፈቃድ ጠይቀው ከተፈቀደላቸው በኋላ ግንባታ ጀምረው ነበር፡፡
ይሁን እንጂ የአስተዳደሩ የቁጥጥር ሰራተኞች ወደ ግንባታው ስፍራ በመሄድ በተፈቀደው መሰረት ሳይሆን ከዚያ ውጪ እየተገባ እንደሆነ በመግለፅ እና በተጀመረው መንገድ መቀጠል ካስፈለገ የግል ተበዳይ 150 ሺህ ብር እንዲሰጡ መጠየቃቸውን ረዳት ኢንስፔክተር እሸቱ ቅጣው ተናግረዋል፡፡
የግል ተበዳይ ግን 150 ሺህ ብር የለኝም ሲሉ ወደ 80 ሺህ ብር ዝቅ እንደተደረገላቸው እና ከዚያ በኋላ ሁኔታውን ለፖሊስ ማሳወቃቸውን የጠቀሱት ረዳት ኢንስፔክተር እሸቱ ቅጣው 80ሺህ ብር እንደሌላቸውም በአካልም በስልክም ተገናኝተው ከተደራደሩ እና በ60 ሺህ ብር ከተስማሙ በኋላ ተጠርጣሪው ብሩን ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዞ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡
በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን እና ማህበራዊ ትስስር ገፆች ተጠርጣሪው የተቀበለው ገንዘብ 140 ሺህ ብር እንደሆነ ተደርጎ የተገለፀው ስህተት መሆኑን ረዳት ኢንስፔክተር እሸቱ ቅጣው ጠቅሰዋል። (የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድርና ፖሊስ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply