የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በክልሉ ታጥቆ ለሚብቀሳቀሰው የኦነግ ሸኔ ቡድን የሰላም እና የእርቅ ጥሪ አቀረቡ። ጨፌ ኦሮሚያ በዛሬው እለት መደበኛ ስብሰባውን እያደረገ ይገኛል። አቶ ሽመልስ አብዲሳ መንግሥት የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል። ጨፌ ኦሮሚያ በዛሬው እለት መደበኛ ስብሰባውን ማድረግ የጀመረ ሲሆን፣ የክልሉ ርእሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የክልሉ መንግሥት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል። በዚህም አቶ ሽመልስ፣ "ሰላም ለሁሉም ነገር መሰረት ነው፣ ሰላም በሌለበት ስለ ልማት ማሰብ አይቻልም" ያሉ ሲሆን፣ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል። ርእሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ በንግግራቸው፣ "በዚህ በተከበረው ጨፌው ፊት በክልላችን ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ … [Read more...] about ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት
shemelis abdissa
በሆሩ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጉደኔ ጫላ ሲበሬ ቀበሌ ነዋሪዎች በኦነግ ሸኔ ላይ ጀብዱ ፈፀሙ
ነገሩ እንዲህ ነው። በኦሮሚያ ክልል በሆሩ ጉድሩ ወለጋ ዞን ጮማን ጉዱሩ ወረዳ ውስጥ ካሉት ቀበሌዎች መካከል በአንዲት ቀበሌ ውስጥ ታላቅ ጀብዱ ተፈፅሟል። ቀበሌዋ ጉደኔ ጫላ ሲበሬ ትባላለች። እንደወትሮው ሁሉ ህዝቡ ውስጥ ለመደበቅ የአሸባሪው ሸኔ ታጣቂዎች ወደዚህች ቀበሌ ዘልቀው ይገባሉ። ነገር ግን የጉደኔ ጫላ ሲበሬ ቀበሌ አሁን በቃችሁን በማለት 07 ወጣቶች ከታጠቁት ሸኔ ታጣቂዎች ጋር በጦርና በገጀራ ጦርነት ገጠሙ። ከ7ቱ ሶስቱ የዩኒቨሪሲቲ ተማሪዎች ሲሆኑ አራቱ ደግሞ አርሶ ከደር ናቸው። ጩሃቱን የሰማው የቀበሌው ህዝብ በሙሉ በነቂስ ወጥቶ ከታጠቁት ሸኔዎች ጋር በባህላዊ ጦርና ገጀራ ገጠሙ። ይህንኑ ያላሰቡትን የህዝብ ማዕበልና ቁጣ አይተው የተደናበሩት አሸባሪዎች እግር አውጪኝ ብለው እግራቸው ወደመራቸው አቅጣጫ መሸሽን መረጡ። ነገር ግን የህዝብ ማዕበሉ አንዱን በጦር … [Read more...] about በሆሩ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጉደኔ ጫላ ሲበሬ ቀበሌ ነዋሪዎች በኦነግ ሸኔ ላይ ጀብዱ ፈፀሙ
“አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና ነው” አቶ ሃንጋሳ
በወለጋ የንፁሃንን ጭፍጨፋ እየተፈፀመ ያለው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ነው ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ሃንጋሳ አህመድ ኢብራሂም ተናገሩ። አክለውም የኦሮሚያ ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ጠ/ሚ አብይ አህመድን በይፋ በፌስቡክ የቀጥታ ስርጭታቸው ጠይቀዋል። ከ 2 ቀናት በፊትም ጠባቂያቸው መገደሉን ተናግረዋል። አቶ ሀንጋሳ ትላንት ሁለት ሰዓት በፈጀውና ከ15 ሺህ በላይ ተመልካቾች በተከታተሉት የፌስቡክ የቀጥታ ስርጭት በኦሮምኛ (የተወሰኑ ቁልፍ ነገሮችን ደግሞ በአማርኛ) አስተላልፈዋል፡፡ የሚከተሉት ዋነኛ ነጥቦች ነበሩ: አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና እቅድና ተግባር ነው፣ አብዲ ኢሌ ሲነሳ ሶማሊያ ሰላም እንደሆነው ሁሉ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ በክልሉ ያሉ ባለስልጣናትን እስር … [Read more...] about “አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና ነው” አቶ ሃንጋሳ
አዲስ አበባን “irrelevant” በማድረግ ሥራ የሽመልስና የታከለ መናበብ
ሽመልስ አብዲሣ በድብቅ የተናገረውና ለዓላማቸው ሲሉ በቅርቡ አፈትልኮ እንዲወጣ ያደረጉ ወገኖች በለቀቁት መረጃ አዲስ አበባን አስመልክቶ ሽመልስ ይህንን ብሎ ነበር፤ “አዲስ አበባ ላይ መፍትሄ የሚያመጣው ሶስት ነገር ነው፣ “አንደኛው ሰውን ማስፈር ነው፣ በስራ፣ ከማውራት በስራ፣ አትጠይቁን የምንችለውን እያደረግን ነው። “ሁለተኛው አዲስ አዲስ አበባን irrelevant ማድረግ ነው። አዲስ አበባን irrelevant ለማድረግ እየሰራን ነው። ከተሳካልን ከምርጫ በኋላ የፌዴራል መንግስቱን መቀመጫ፣ አራት አምስት ቦታ ለመክፈል እንፈልጋለን። “ዝም ብሎ አዲስ አበባን በስራችን እናስገባለን ብሎ መለፍለፍ አይደለም። እንዴት ታደርገዋለህ ፣ ፈንጂውን እንዴት ታፈነዳዋለህ? አሁን እኛ ኦሮሚያ ከልክ በላይ እየለማች ነው፣ ሌላው ክልል ከልክ በላይ እየተጎዳ ነው። ይህ ደግሞ እየሆነ … [Read more...] about አዲስ አበባን “irrelevant” በማድረግ ሥራ የሽመልስና የታከለ መናበብ