• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና ነው” አቶ ሃንጋሳ

July 6, 2022 01:53 am by Editor 1 Comment

በወለጋ የንፁሃንን ጭፍጨፋ እየተፈፀመ ያለው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ነው ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ሃንጋሳ አህመድ ኢብራሂም ተናገሩ። አክለውም የኦሮሚያ ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ጠ/ሚ አብይ አህመድን በይፋ በፌስቡክ የቀጥታ ስርጭታቸው ጠይቀዋል። ከ 2 ቀናት በፊትም ጠባቂያቸው መገደሉን ተናግረዋል።

አቶ ሀንጋሳ ትላንት ሁለት ሰዓት በፈጀውና ከ15 ሺህ በላይ ተመልካቾች በተከታተሉት የፌስቡክ የቀጥታ ስርጭት በኦሮምኛ (የተወሰኑ ቁልፍ ነገሮችን ደግሞ በአማርኛ) አስተላልፈዋል፡፡ የሚከተሉት ዋነኛ ነጥቦች ነበሩ:

  • አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና እቅድና ተግባር ነው፣
  • አብዲ ኢሌ ሲነሳ ሶማሊያ ሰላም እንደሆነው ሁሉ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ በክልሉ ያሉ ባለስልጣናትን እስር ቤት በማስገባት ሰላም ይስፈን፣
  • ዶ/ር አብይ ከለማ የቀረበ ወዳጅ አልነበረህም። በእሱ ላይ የጨከንክ በሽመልስ ላይ መጨከን እንዴት አቃተህ?
  • ዶ/ር አብይ የኦሮሚያ ክልልን ካቢኔን አፍርሰህ በአዲስ ተካ፣ ይህንን ካላደረክ አማራ እንዲጨፈጨፍ የምታደርገው አንተ ነህ ወደሚል ድምዳሜ እሄዳለው፣
  • እኔ ብሞት እንኳን ወንድሞቼ (አማራ፣ ኦሮሞ፣ ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች) እውነቱን ስሙ (እወቁት)
  • ዶ/ር አብይ መሬት ላይ ወርደህ ህዝቡን ይቅርታ ጠይቅ፣ አንተን እና ህዝቡን ለይተው ሊበሉህ ደጅህ ላይ የቆሙ ጅቦች አሉና ቅደማቸው፣
  • ዶ/ር አብይ እሰር፣ ቀፍድድ፣ ወስን እና ጨክን፤ አንተን ገለው ቤተመንግስት ሊገቡ ያሰቡ ሰዎች ሰፈራችን ላይ ደርሰዋል (አጃቢዬን ዛሬ ገለውታል ነገ እኔንም ቢገሉኝ እውነት እናገራለሁ)
  • ኦነግ ለዘመናት ወለጋ ውስጥ ነበር፣ ኦነግ ሀረርጌ እና አርሲ አለ፤ አሁን ኦነግ የመግደያ፣ የመጨፍጨፊያ አቅሙን ከየት አመጣው ብለህ ጠይቅ፤ እኔ ግን እነግርሃለው ሀይሉን እና አቅሙን ያገኘው ከክልሉ መንግስት ነው
  • እነ ሽመልስ ዙሪያውን ከበው ሊበሉህ ነው፣ ሊጨርሱህ ነው የመጨረሻው ሰዓት ላይ ደርሰሃል አይንህን ግለጥ
  • አማራን ኦሮሚያ ውስጥ መጨፍጨፍ የሚጎዳው ከአማራ ይልቅ ኦሮሞን ነው፣
  • የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ስንት ገዳይ እንፈልጋለን፣ ለፍትህ እናቀርባለን ብላችሁ ስንቱን አሳካችሁ፤ ምኑንም አላሳካችሁም ወሬ ብቻ፤ በዚህ መሃል ግን ወንድም እና እህቶቼ (አማራዎች) ወለጋ ውስጥ አለቁ
  • መቼ ነው ዶ/ር አብይ ከአትክልት ስራ ወጥተህ ጠንከር ያለ ስራ የምትሰራው፤ መቼ ነው የከበበህ መከራ የሚታይህ፣ መቼ ነው ሊበላህ የተነሳው ጅብ የሚታይህ
  • ዛሬ አማራን እየገደለ የሚመጣው ሀይል መቆሚያው አንተ ቤት (አራት ኪሎ) ነው
  • ሽመልስ እና ፍቃዱ ታደሰን (ፍቃዱ ተሰማ ለማለት መሰለኝ) ወደ እስር ቤት ካላስገባህ ከዚህ ጥቃት ጀርባ አንተ አለህ ማለት ነው፣
  • ለአብዲ ኢሌ ክፍት የሆነ እስር ቤት ለሽመልስ እና ፍቃዱ ዝግ የሆነው ኦሮሞ ስለሆኑ ነው? ወይስ አዛዡ አንተ ስለሆንክ?
  • አጉል ጥጋብ እና ሁኔታ ውስጥ ገብታችሁ የአማራን መገደል የምትደግፉ የኦሮሞ ወንድሞቼ እረፉ (ዋ እረፉ ብያለሁ)፣ ነገ ጠዋት አማራ ኦሮሞ ላይ እንዲነሳና እርስ በእርስ እንድንትላለቅ ነው ፍላጎቱ፣ የኦሮሞ ወንድሞቼ ንቁ (በጭራሽ በኦሮሞ ብልጽግና ገመድ እንዳትጠለፉ)
  • አንተን (አብይን) እያስጠሉ ያሉት ዙሪያህን የከበቡህ እና ሰው ያደረካቸው መናዎች ናቸው
  • ኦሮሚያ የሁላችንም ቤት ነው፣ አማራው ተመርጦ ሲታረድ ለምን ካላልን ነገ መከራው በኛና በልጆቻችን ላይ ይደርሳል
  • ዶ/ር አብይ እስኪ ድንገት ጅማ፣ ሀረርጌ፣ ገራሙለታ፣ አርሲ፣ ወለጋ፣ ባሌ፣ ጭሮ ሂድና ህዝቡን ስማ (መሬት ላይ ያለውን መከራ እይ)፣ ያኔ ምን አይነት የሚመር ዜና እንደምትሰማ እነግርሃለው
  • የኦሮሞ ካቢኔ ተጠራርጎ እስር ቤት ካልገባና ለፍርድ ካልቀረበ የአማራ መጨፍጨፍም አይቆምም ሀገርም ሰላም አትሆንም (የኔታ ሚዲያ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, Opinions, Uncategorized Tagged With: olf shanee, opdo, operation dismantle tplf, OPP, shemelis abdissa, tplf terrorist, wollega

Reader Interactions

Comments

  1. Getahun says

    July 7, 2022 05:26 pm at 5:26 pm

    Late but Good! This is exactly what the public was talking for years!
    As far as I remember OLF has such behavior. Before TPLF come ro power AMHARA settlers were brutally killed at BENISHANGUL/ASSOSA area by OLF, backed by TPLF,and EPLF!!! Many publi workers were also disapeared/abducted.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule