ነገሩ እንዲህ ነው። በኦሮሚያ ክልል በሆሩ ጉድሩ ወለጋ ዞን ጮማን ጉዱሩ ወረዳ ውስጥ ካሉት ቀበሌዎች መካከል በአንዲት ቀበሌ ውስጥ ታላቅ ጀብዱ ተፈፅሟል። ቀበሌዋ ጉደኔ ጫላ ሲበሬ ትባላለች። እንደወትሮው ሁሉ ህዝቡ ውስጥ ለመደበቅ የአሸባሪው ሸኔ ታጣቂዎች ወደዚህች ቀበሌ ዘልቀው ይገባሉ። ነገር ግን የጉደኔ ጫላ ሲበሬ ቀበሌ አሁን በቃችሁን በማለት 07 ወጣቶች ከታጠቁት ሸኔ ታጣቂዎች ጋር በጦርና በገጀራ ጦርነት ገጠሙ። ከ7ቱ ሶስቱ የዩኒቨሪሲቲ ተማሪዎች ሲሆኑ አራቱ ደግሞ አርሶ ከደር ናቸው። ጩሃቱን የሰማው የቀበሌው ህዝብ በሙሉ በነቂስ ወጥቶ ከታጠቁት ሸኔዎች ጋር በባህላዊ ጦርና ገጀራ ገጠሙ። ይህንኑ ያላሰቡትን የህዝብ ማዕበልና ቁጣ አይተው የተደናበሩት አሸባሪዎች እግር አውጪኝ ብለው እግራቸው ወደመራቸው አቅጣጫ መሸሽን መረጡ። ነገር ግን የህዝብ ማዕበሉ አንዱን በጦር … [Read more...] about በሆሩ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጉደኔ ጫላ ሲበሬ ቀበሌ ነዋሪዎች በኦነግ ሸኔ ላይ ጀብዱ ፈፀሙ
wollega
“አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና ነው” አቶ ሃንጋሳ
በወለጋ የንፁሃንን ጭፍጨፋ እየተፈፀመ ያለው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ነው ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ሃንጋሳ አህመድ ኢብራሂም ተናገሩ። አክለውም የኦሮሚያ ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ጠ/ሚ አብይ አህመድን በይፋ በፌስቡክ የቀጥታ ስርጭታቸው ጠይቀዋል። ከ 2 ቀናት በፊትም ጠባቂያቸው መገደሉን ተናግረዋል። አቶ ሀንጋሳ ትላንት ሁለት ሰዓት በፈጀውና ከ15 ሺህ በላይ ተመልካቾች በተከታተሉት የፌስቡክ የቀጥታ ስርጭት በኦሮምኛ (የተወሰኑ ቁልፍ ነገሮችን ደግሞ በአማርኛ) አስተላልፈዋል፡፡ የሚከተሉት ዋነኛ ነጥቦች ነበሩ: አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና እቅድና ተግባር ነው፣ አብዲ ኢሌ ሲነሳ ሶማሊያ ሰላም እንደሆነው ሁሉ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ በክልሉ ያሉ ባለስልጣናትን እስር … [Read more...] about “አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና ነው” አቶ ሃንጋሳ
“የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ)ን ማንነት የማያውቅ አንድም በሟቾች ይሸቅጣል፤ በደማቸው የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ይጣጣራል፤ ወይም ያወቀ መስሎት ይለፈልፋል፣ ይዘልፋል፣ ይዘፍናል። ትህነግ ከአፈጣጠሩ ጀምሮ ምህረት የማያውቅ እንደሆነ "ነጻ አወጣሃለው" ባለው ሕዝብ ላይ ለዓመታት የፈጸመውን መመልከት በቂ ነበር። ስለምንረሳና እንደምረሳ ስለሚያውቅ ገድሎ ሙሾ አውራጅ ሆኖ ይመጣል። ጨፍጭፎን ስለ ሰላም ልደራደር ይላል። በወለጋ የተከሰተውንና መቼም የማይረሳውን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ በትህነግ ልክ ያለ አካል እና እርሱ አቡክቶ ጋግሮ የሠራው ኦነህ ሸኔ ካልሆነ ማንም ሊያደርገው እንደማይችል መገመት የማይችል ገና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ያልገባው የፖለቲካ ሕጻን ነውና አርፎ ተቀምጦ ይማር። ሌሎች ግን አሉ አዛኝ መስለው አጀንዳ የሚፈጽሙ። ባደባባይ ከሰቆቃው ሰለባ በላይ … [Read more...] about “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ