
የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በክልሉ ታጥቆ ለሚብቀሳቀሰው የኦነግ ሸኔ ቡድን የሰላም እና የእርቅ ጥሪ አቀረቡ። ጨፌ ኦሮሚያ በዛሬው እለት መደበኛ ስብሰባውን እያደረገ ይገኛል። አቶ ሽመልስ አብዲሳ መንግሥት የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል።
ጨፌ ኦሮሚያ በዛሬው እለት መደበኛ ስብሰባውን ማድረግ የጀመረ ሲሆን፣ የክልሉ ርእሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የክልሉ መንግሥት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።
በዚህም አቶ ሽመልስ፣ “ሰላም ለሁሉም ነገር መሰረት ነው፣ ሰላም በሌለበት ስለ ልማት ማሰብ አይቻልም” ያሉ ሲሆን፣ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል።
ርእሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ በንግግራቸው፣ “በዚህ በተከበረው ጨፌው ፊት በክልላችን ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት ማለትም ኦነግ ሸኔ በእርቅ ወደ ሰላማዊ መንገድ ተመልሶ እንዲገባ በክብር ጥሪ አቀርባለሁ” ብለዋል።
አቶ ሽመልስ አክለውም መንግሥት ለሰላም ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ኦነግ ሸኔ እና መሰል የጥፋት ሃይሎች ትክክለኛውን መንገድ እንዲይዙ እየሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል።
በክልሉ ሰላም እንዲሰፍን እስከ ህይወት መሰዋእትነት እየከፈሉ ላሉ የጸጥታ አካላትም ምስጋናቸውን ያቀረቡት ርእሰ መስተዳደሩ፣ ለክልሉ ሰላም የሰሩት ስራ ሁሌም በታሪክ ስዘከር ይኖራል ብለዋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2013 ግንቦት ወር ላይ በኦሮሚያ ክልል ታጥቆ የሚንቀሳቀሰውን “ኦነግ ሸኔ” ቡድንን በሽብርተኝትነት መፈረጁ ይታወሳል።
በተለምዶ “ሸኔ” ተብሎ የሚጠራውና በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሰዉ ቡድን በርካቶችን ህይወት እንዲጠፋ፣ እንዲፈናቀሉ እና ንብረት እንዲያወድም ከማደረግ በዘለለ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ማጥቃቱንም መንግሥት በወቅቱ ገልጸዋል።
“ሸኔ” በ2013 ዓ.ም ብቻ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ 463 ሰዎች ላይ አደጋ ማድረሱ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህ ጥቃት እየተባባሰ መምጣቱም ሪፖርቶች ያመለክታሉ።
ቡድኑ ባሳለፍነው ጥር ወር በምስራቅ ወለጋ በፈጸመው ጥቃት ከ50 በላይ ንጹሃን ዜጎችን መግደሉንም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባወጣው ሪፖርት አመላክቷል። (AlAin)
ይህ የሽመልስ አብዲሣ ጥሪ ሕገ ወጥ ብቻ ሳይሆን በሕግም የሚያስጠይቅ ነው የሚሉ ድምፆች እየተሰሙ ነው። በክልል ደረጃ በይፋ ይህንን መሰል ጥሪ ማቅረብ የፖለቲካ ዓላማ ከሌለው ወይም በሰላም ሽፋን እንዳይገለጥ የተፈለገ ምሥጢር ከሌለ በስተቀር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን (የፓርላማውን) ሥልጣን የሚጋፋ ነውና ፓርላማው በግልጽ ጥያቄ ሊያቀርብ ይገባል።
ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች ትህነግም አሸባሪ ተብሎ የሰላም ስምምነት ፈርሟል በማለት ለሚያነሱት ያኛው ቢያንስ በፌዴራል ደረጃ የተከናወነና በሌሎችም አገራት ሲሠራበት የቆየ ልምድ ነው የሚል የማጣፊያ አስተያየት ሲሰጥ ይደመጣል። ወደ ሸኔ ስንመጣ ግን ኦሮሚያ እንደ አገር፤ ጨፌው እንደ ፌደራል ፓርላማ፤ ሽመልስም እንደ ርዕሰ ብሔር ካልተቆጠሩ በስተቀር በይፋ የፓርላማውን ሥልጣን አልፎ ይህንን መሰሉ ውሳኔ ማሳለፍ ክልላዊ ዕብጠት ነው።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ሸሌ ለሸኔ ያቀረበው ድራማ !
ሸሌ ለሸኔ ያቀረበው አስቂኝ አሳፋሪ ቀሽም ድራማ ! የሚያበሳጭ !! በእርግጠኝነት እግዚአብሔር የንፁሃንን ደም ቁማርተኛውን…ይፋረዳቸዋል ! ሸኔ ሸሌ ሸሌ ሸኔ !!