ሽመልስ አብዲሣ በድብቅ የተናገረውና ለዓላማቸው ሲሉ በቅርቡ አፈትልኮ እንዲወጣ ያደረጉ ወገኖች በለቀቁት መረጃ አዲስ አበባን አስመልክቶ ሽመልስ ይህንን ብሎ ነበር፤ “አዲስ አበባ ላይ መፍትሄ የሚያመጣው ሶስት ነገር ነው፣ “አንደኛው ሰውን ማስፈር ነው፣ በስራ፣ ከማውራት በስራ፣ አትጠይቁን የምንችለውን እያደረግን ነው። “ሁለተኛው አዲስ አዲስ አበባን irrelevant ማድረግ ነው። አዲስ አበባን irrelevant ለማድረግ እየሰራን ነው። ከተሳካልን ከምርጫ በኋላ የፌዴራል መንግስቱን መቀመጫ፣ አራት አምስት ቦታ ለመክፈል እንፈልጋለን። “ዝም ብሎ አዲስ አበባን በስራችን እናስገባለን ብሎ መለፍለፍ አይደለም። እንዴት ታደርገዋለህ ፣ ፈንጂውን እንዴት ታፈነዳዋለህ? አሁን እኛ ኦሮሚያ ከልክ በላይ እየለማች ነው፣ ሌላው ክልል ከልክ በላይ እየተጎዳ ነው። ይህ ደግሞ እየሆነ … [Read more...] about አዲስ አበባን “irrelevant” በማድረግ ሥራ የሽመልስና የታከለ መናበብ
takele uma
የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው?
በቡራዩ ብር የማይሰጥ አገልግሎት አያገኝም በአዲስ አበባ ዙሪያና ውስጥ የባዶ መሬትና የኮንዶሚኒየም ቤቶች ገበያ ደርቷል። በርካቶች እንደሚሉት ይህ የደራ ገበያ ምሥጢር ባለመሆኑ ከከንቲባ ታከለ ኡማ አስተዳደር የተሰወረ አይደለም። ምን አልባትም የአዲስ አበባ መሬትና የኮንዶሚኒየም ቤቶች የጠራራ ጸሃይ ገበያና የባለቀንነት ሽሚያ፣ በማኅበራዊ ጉዳዮች ባላቸው ተሳትፎ ሰፊ ተቀባይነት ላላቸው ታከለ ኡማ ጉዞ ጋሬጣ እንዳይሆንባቸው የሚፈሩም አሉ። በተመሳሳይ በቡራዩ ነዋሪዎች ከመሬት ጋር በተያያዘ ሰፊ ቅሬታ ያሰማሉ። በቡራዩ ብር የማይጠበቅበት አገልግሎት እንደሌለም አመልክተዋል። የአየር ጤና ነዋሪ መሆናቸውን የገለጹ ለጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ እንዳስታወቁት ለውጡን ተከትሎ በርካታ ቦታዎች ታጥረውና ሳይታጠሩ ባለቤት አልባ ሆነዋል። እንደ እነሱ ገለጻ ባለቤቶቻቸው ጠፍተዋል፣ … [Read more...] about የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው?