ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ወደ ኦህዴድ ከለወጡት የዶክተር መረራ ወጣቶች ክንፍ አባላት መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ታከለ ኡማ አዲስ የትግል ኅብረት በመፍጠር ላይ መሆናቸው ተሰማ። ለዚህ እንቅስቃሴ የሚሆናቸው የመደበኛ ሚዲያና የማኅበራዊ ሚዲያ ትሥሥር ገጽ ሠራዊት እንዳመቻቹም ታውቋል። መነሻቸው ፖለቲካዊ ኩርፊያ ነው ተብሏል።
ጎልጉልን ያነጋገሩ የመረጃው ባለቤቶች እንዳሉት የቀድሞው የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባና የማዕድን ሚኒስትር መንግሥት ላይ አቂመዋል። የለውጡ የምሥጢር ታጋይ እንደነበሩ የሚናገሩት ታከለ አሜሪካ ከተሻገሩ በኋላ በዳያስፖራ ከሚገኙ ዋነኛ አኩራፊዎች ጋር በማበር ጠበቅ ባለ እንቅስቃሴ ተጠምደዋል።
ጥያቄው ከቀረበላቸው መካከል አንዱ የሆኑት የኦህዴድ የቀድሞ አመራር እንዳሉት ታከለ ኡማ ከአማራ፣ ከኦሮሞና የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ካኮረፉ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ) አካላት ጋር ምክክርና ግንኙነት ጀምረዋል።
እንዲህ ያለውን ስብስብ ከጀርባ በመምራት የሚታወቁት ሻለቃ ዳዊት መሆናቸውን በተደጋጋሚ በጎልጉል ድረገጽ የዘገብነው ጉዳይ እንደሆነ ይታወቃል። በወቅቱ አሶሺየትድ ፕሬስ እንደዘገበው ሻለቃ ዳዊት በ1977 ዓም ተከሰተ በተባለውድርቅ ከረሃብተኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ 300,000 ሺህ ዶላር በመዝረፍ አሜሪካ ሁለት ቤት መግዛታቸውን ይታወሳል።
ታከለ ኡማ የአዲስ አበባ ከንቲባ እያሉ በተደጋጋሚ አቶ ጃዋር መሀመድ ቤት ይታዩ እንደ ነበር ድንገት እዚያ ያገኙዋቸው ምስክሮች አሉ። ቀደም ሲል የሆለታ ከንቲባ እያሉ ባልደረቦቻቸው በሙሉ በሌብነት ሲታሰሩ እርሳቸው ብቻ ነጻ መደረጋቸውን ተከትሎ “ሁለት ቦታ መጫወት ይችሉበታል” በሚል በኔትዎርክ አብረዋቸው መሬት ሲያጫውቱ በነበሩ ባልደረቦቻቸው ይታሙ እንደነበር ይታወሳል።
የአዲስ አበባ ከንቲባ ከሆኑ በኋላ በመሬት ጉቦ ሚዲያ በመያዝ ሰፊ ምዝበራ እንዳካሄዱ የሚነገርባቸው ታከለ ኡማ ወደ ማዕድን ሚኒስትርነት ሲዛወሩም በተመሳሳይ ከወርቅ ማዕድን መሬት እደላ ጋር በተያያዘ ስማቸው ከሚታወቁ “ምስለኔዎች” ጋር ተነስቷል።
እዚያው ማዕድን ሚኒስትር እያሉ ምዕራብ ሸዋ ቶኬ አካባቢ አባታቸው በኅዳር ወር 2015ዓም በኦነግ ሸኔ ታፍነው 10ሚሊዮን ብር ክፈሉ ተብለዋል የሚል መረጃ በወጣበት ሰሞን ታከለ በትዊተር ገጻቸው ላይ “አባቴ አርሶ አደርነው፤ አሁን ምግብርና ላይ ነው” (Abbaan kiyya qotee bulla dha. Ammas qonnasaarra jira) ከማለት ሌላ ምንም አልተናገሩም ነበር። ታከለ ይህንን ከለጠፉ በኋላ ምንም ክፍያ ሳይጠየቁ አባታቸው መለቀቃቸውን የሚያውቁ የታከለና የሸኔን ግንኙነት በተመለከ ተከፍተኛ ጥርጣሬ እንዳደረባቸው ገልጸው በድርጅትና በመረጃ ደህንነት በኩል ማጣራት እንዲካሄድባቸው ጥያቄ ቀርቦ እንደነበር ዜናውን ያጋሩት አስታውሰዋል።
የትግራይ ተወላጅ ከሆነች ከቀድሞ ወዳጃቸው አንድ ልጅ ያላቸው ታከለ ኡማ “ሸኔዎችሊገድሉኝሞክረዋል” በሚል መኖሪያ ቤታቸውን ያስቀየሩት ምራሳቸው ከሚታሙበት ጉዳይ ነጻ ለማውጣት ሆነ ብለው የተጠቀሙበት ሥልት እንደሆነ እነዚሁ ወገኖች በርካታ መረጃዎችያቀርባሉ።
አሜሪካ ከገቡ በኋላ ከልጃቸው እናት ጋር ስላላቸው ግንኙነት ብዙም መረጃ እንደሌላቸው የሚናገሩት ወገኖች “አቶ ታከለ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) በሪፖርተርነት ትሠራ የነበረች አንድ ወዳጃቸው የምትመራው ሚዲያ ከፍተዋል። አሁን ወቅቱ ስላልሆነ የሚዲያው እና የሚዲያውን መሪ ስም ለጊዜው መግለጽ አስፈላጊ አይደለም” ሲሉ የሚያውቁትን ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ አመልክተዋል።
አቶ ታከለ በቅርቡ አዲስ አበባ ደርሰው የተመለሱ ሲሆን በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከመንግሥት ሰዎች ጋር ብዙም ግንኙነት እንዳላደረጉ ታውቋል። ከሚኒስትርነት ሥልጣናቸው ሲነሱ ቢያንስ ኦሮሚያ ክልል አለመመደባቸው ክፉኛ ያበሳጫቸው አቶ ታከለ በአቶ ግርማ ብሩ ሽማግሌነት ድርጅታዊ ይቅርታ ተደርጎላቸው ለትምህርት በሚል ወደ አሜሪካ ማምራታቸውን ለጎልጉል መረጃውን ካቀበሉት ለመረዳት ተችሏል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
haileyesus says
ማውራት የፈለከው ስለማን እንደሆነ ገብቶኛል።
ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ነው።