ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ወደ ኦህዴድ ከለወጡት የዶክተር መረራ ወጣቶች ክንፍ አባላት መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ታከለ ኡማ አዲስ የትግል ኅብረት በመፍጠር ላይ መሆናቸው ተሰማ። ለዚህ እንቅስቃሴ የሚሆናቸው የመደበኛ ሚዲያና የማኅበራዊ ሚዲያ ትሥሥር ገጽ ሠራዊት እንዳመቻቹም ታውቋል። መነሻቸው ፖለቲካዊ ኩርፊያ ነው ተብሏል። ጎልጉልን ያነጋገሩ የመረጃው ባለቤቶች እንዳሉት የቀድሞው የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባና የማዕድን ሚኒስትር መንግሥት ላይ አቂመዋል። የለውጡ የምሥጢር ታጋይ እንደነበሩ የሚናገሩት ታከለ አሜሪካ ከተሻገሩ በኋላ በዳያስፖራ ከሚገኙ ዋነኛ አኩራፊዎች ጋር በማበር ጠበቅ ባለ እንቅስቃሴ ተጠምደዋል። ጥያቄው ከቀረበላቸው መካከል አንዱ የሆኑት የኦህዴድ የቀድሞ አመራር እንዳሉት ታከለ ኡማ ከአማራ፣ ከኦሮሞና የሰላም ስምምነቱን … [Read more...] about ታከለ ኡማ የዳያስፖራ አኩራፊዎችን ሰብስበው ድርጅት እየመሠረቱ ነው፣ ሚዲያም አቋቁመዋል
takele umma
በወርቅ ዝርፊያ የተሰማሩ 28 ቻይናውያን፣ 2 ኢትዮጵያውያንና 1 ሱዳናዊ ተያዙ
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሕገ-ወጥ የወርቅ ምርትና ግብይት ተግባር ላይ ተሰማርተው የተገኙ 29 የውጭ ሀገራት ዜጎች እና ሁለት ኢትዮጵያውያን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ። የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለኢዜአ በላከው መግለጫ መንግሥት በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ የሰላም መደፍረስ እና የጸጥታ ሥጋቶችን ለመቀልበስ ትኩረት እያደረገ በነበረበት ወቅት በሕገ-ወጥ የማዕድን ምርትና ዝውውር የተሰማሩ አካላት በሀገር ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎችና አሸባሪ ቡድኖች ጋር የጥቅም ትስስር በመፍጠር በኢኮኖሚው መስክ አስተዋፅዖ ባላቸው የማዕድን ምርቶች በተለይም በወርቅ ላይ ያተኮረ ዝርፊያ ሲፈጽሙ መቆየታቸውን አስታውቋል፡፡ የማዕድን ዘርፉ በሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ የነበረው ድርሻ እየቀነሰ መምጣቱን ተከትሎ … [Read more...] about በወርቅ ዝርፊያ የተሰማሩ 28 ቻይናውያን፣ 2 ኢትዮጵያውያንና 1 ሱዳናዊ ተያዙ
ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው
በማዕድን ዘርፍ ለማልማት ፈቃድ ከወሰዱ 250 መካከል እየሠሩ ያሉት 8% ብቻ ናቸው ብዙ ሃሜታ የሚነሳበትን የመዐድን ሚኒስቴርን ሲመራ የነበረው ታከለ ዑማ በበርካታ የሌብነት ወንጀል ብዙ ሲባለበት ቢቆይም አገር ለቅቆ መውጣቱ ይታወቃል። የእርሱን ከአገር መልቀቅ ተከትሎ ከመዐድን ሚኒስቴር አካባቢ የሚሰሙት መረጃዎች መሥሪያ ቤቱ ምን ያህል ሲመዘበር እንደቆየ አመላካች ሆኗል። የተያዙት ግለሰቦችም ስለዚህ ጉዳይና እስከ መንግሥት መዋቅር ስለ ዘለቀውን የሌብነት መስተጋብርም የሚሉት ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል። በየቤኒሻንጉል ጉሙዝ በማዕድን ልማት ለመሰማራት ፈቃድ ከወሰዱ ከ250 በላይ አልሚዎች መካከል ወደ ሥራ የገቡት 20 ብቻ እንደሆኑ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ በሕገ ወጥ መንገድ ወርቅ ሲያዘዋውሩ የተገኙ 45 የውጭ አገራት ዜጎች … [Read more...] about ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው
የኢትዮጵያ ወርቅ የት ገባ?
ኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ወራት የወርቅ ምርት “በከፍተኛ መጠን” መቀነሱን የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ ተናገሩ። የባንኩ ገዢ በሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ምክንያት ጥብቅ የፊስካል እና የገንዘብ ፖሊስ መከተል አለመቻሉን ገልጸዋል። ዶ/ር ይናገር ይህን ያሉት የብሔራዊ ባንክን የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ እና የሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት፤ ለፓርላማ የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ ሐሙስ ህዳር 29 ባቀረቡበት ወቅት ነው። የባንኩ ገዢ በዚሁ ሪፖርታቸው፤ በሩብ ዓመቱ የነበረውን የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ሁኔታ ዳስሰዋል። የሩብ ዓመቱ የወጪ ንግድ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር “መጠነኛ ጭማሪ” ማሳየቱን ያነሱት ዶ/ር ይናገር፤ ገቢው “በተወሰኑ ዘርፎች ላይ” የተገኘ መሆኑን ጠቁመዋል። ሀገሪቱ ላገኘችው ገቢ “ከፍተኛውን ድርሻ” የያዙት አበባ እና ቡና መሆናቸውን … [Read more...] about የኢትዮጵያ ወርቅ የት ገባ?