በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሕገ-ወጥ የወርቅ ምርትና ግብይት ተግባር ላይ ተሰማርተው የተገኙ 29 የውጭ ሀገራት ዜጎች እና ሁለት ኢትዮጵያውያን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ። የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለኢዜአ በላከው መግለጫ መንግሥት በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ የሰላም መደፍረስ እና የጸጥታ ሥጋቶችን ለመቀልበስ ትኩረት እያደረገ በነበረበት ወቅት በሕገ-ወጥ የማዕድን ምርትና ዝውውር የተሰማሩ አካላት በሀገር ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎችና አሸባሪ ቡድኖች ጋር የጥቅም ትስስር በመፍጠር በኢኮኖሚው መስክ አስተዋፅዖ ባላቸው የማዕድን ምርቶች በተለይም በወርቅ ላይ ያተኮረ ዝርፊያ ሲፈጽሙ መቆየታቸውን አስታውቋል፡፡ የማዕድን ዘርፉ በሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ የነበረው ድርሻ እየቀነሰ መምጣቱን ተከትሎ … [Read more...] about በወርቅ ዝርፊያ የተሰማሩ 28 ቻይናውያን፣ 2 ኢትዮጵያውያንና 1 ሱዳናዊ ተያዙ
gold
በቦሌ ኤርፖርት 3.4 ሚሊዮን ብር የሚገመት ወርቅ በቁጥጥር ሥር ዋለ
አንድ ነጥብ አራት ኪሎ ግራም መጠን ያለው ወርቅ አዲስ አበባ ከሚገኘው የካሜሮን ኤምባሲ ወደ ካሜሮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተላከ መልዕክት በማስመሰል ከሀገር ለማስወጣት ሲሞከር በቁጥጥር ስር ዋለ። በአዲስ አበባ ኤርፖርት ወደ ካሜሮን ለመጓዝ ዝግጅት ሲያደርግ የነበረ መንገደኛ የዲፕሎማቲክ መልዕክት በማስመሰል ለማሳለፍ ሲሞክር በማሽን በታገዘ ፍተሻ ሊያዝ ችሏል። የተያዘው ወርቅ በወቅታዊ የብሔራዊ ባንክ የመግዣ ዋጋ ሶስት ሚሊዮን አራት መቶ ሺህ (3,400,000) ብር ግምታዊ ዋጋ ወጥቶለታል። የገቢዎች ሚኒስቴር የሀገርን ሀብት ከምዝበራ የታደጉ የጉምሩክ ሰራተኞች እና የፀጥታ አካላት ምስጋናውን አቅርቧል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በቦሌ ኤርፖርት 3.4 ሚሊዮን ብር የሚገመት ወርቅ በቁጥጥር ሥር ዋለ
ለገደንቢ “የእርም” መሬት!
የራሱ የሆነ ገንዘብ ሳይኖረው “ልማት አከናውናለሁ” በማለት መሬት ሲወስድ፣ አጥር አጥሮ ለዓመታት ባዶ መሬት ከጥቅም ውጪ ሲያደርግ፣ በወሰዳቸውና ፋብሪካ ከፈትኩባቸው በሚላቸው ድርጅቶች አለአግባብ ከመበልጸግ አልፎ ተገቢውን ግብር ባለመክፈል፣ እንዲከፍል ሲገደድ ደግሞ የህወሓት ወንበዴ ሹመኛዎችን በመደለል፣ ኪሳቸውን በማደለብ፣ የሕዝብ ተቀባይነትን ለማግኘት ታዋቂ በሆኑ ግለሰቦችና ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ከሰበሰበው ሃብት ፍርፋሪውን በመጣል “የሕዝብ ልጅ” በመባል፣ በአጠቃላይ የኢትዮጵያን ሐብት በጨበጣ ኪሱ ያስገባው አላሙዲ በለገደንቢ የወርቅ ምርት እንደ ስንዴ በመሰብሰብ የአገርና የሕዝብ ሃብት ሲዘርፍ በወገን ላይ ያስከተለው ጉዳት ትውልድና ዘመን ተሻጋሪ ነው። የአላሙዲ ሚድሮክ ጎልድ የለገደንቢን ምድር ከረገጠ ጊዜ ጀምሮ አካባቢውን የዕርግማን ምድር፤ ቦታውን “የእርም” መሬት … [Read more...] about ለገደንቢ “የእርም” መሬት!
በለገደንቢ “ነፍሰጡር ሴቶች ያስወርዳቸዋል፤ ሕፃናት ሲወለዱ ያለጭንቅላት ይወለዳሉ”
ወ/ሮ ሑጤ ደንቆ የሁለት ልጆቻቸው ሞት እንዲሁም የሴት ልጃቸው አካል መጉደል ካደርሰባቸው የሐዘን ስብራት ጋር በጉጂ ዞን ኦዶ ሻኪሶ ወረዳ ዲባ በቴ ቀበሌ ውስጥ ይኖራሉ። እኚህ እናት የመጀመሪያ ልጃቸውን ሁለት እግሯን አልታዘዝ ከማለት በተጨማሪ በኋላ የወለዷቸው ወዲያውኑ እንደተወለዱ ሞተውባቸዋል። ወ/ሮ ሑጤ ነፍሰጡር በነበሩበት ወቅት ከባድ የጤና እክል አጋጥሟቸው የነበረ ቢሆንም አሁንም የአጥንት ሕመም ህይወታቸውን አቀበት አድርጎባቸዋል። የእሳቸውን እና የልጆቻቸውን ጤንነት ይከታተሉ የነበሩ የህክምና ባለሙያዎች የእሳቸው አጥንት ህመምም ሆነ የልጃቸው እግር አጥንት መልፈስፈስ ምክንያቱ ከፋብሪካው የሚወጣው መርዛማ ኬሚካል መሆኑን እንደነገሯቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ወ/ሮ ሑቴ የሚኖሩበት ዲባ በቴ ቀበሌ የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር ለገደንቢ ወርቅ ማምረቻ … [Read more...] about በለገደንቢ “ነፍሰጡር ሴቶች ያስወርዳቸዋል፤ ሕፃናት ሲወለዱ ያለጭንቅላት ይወለዳሉ”
የአላሙዲ ኪስ በወርቅ ሲታጨቅ፤ አዶላ ኑሮ በጭንቅ!
ከሳምንታት በፊት የለገደንቢ ወርቅ ሽያጭ ድራማ!! ወርቃችን እንዴት አላሙዲ እጅ ገባ? በሚል ርዕር ላቀረብነው ጽሑፍ የድረገጻችን አንባቢ አሥራደው የሚከተለውን በግጥም የተከሸነ መልዕክት ልከውልናል፡፡ ተናገር መጋዶ ተናገር ሻኪሶ፤ ወርቅ ወዴት ተጋዘ ላንተ አፈሩ ደርሶ፤ ተናገር ሃዲማ ደግሞም ኡላኡሎ፤ እነማን ዘረፉት የወርቁን አሎሎ?! የወርቁን ቡችላ የለገ ደንቢውን፤ ደብዛውን ንገሩን የደረሰበትን?! እነማን ዘረፉት ? ማንስ ከበረበት?! እነማን ተዝናኑ? ማንስ ጨፈረበት?! ድሃ በደከመ ድሃ በሞተበት፤ ጦሙን እንደዋለ አፈር ተንዶበት:: አካፋና ዶማ ይዘው ሳይቆፍሩ፤ ጨለማ መግፈፊያ ሻማ ሳያበሩ፤ ጠብ ሳይል ላባቸው ባቋራጭ ከበሩ፡ ያገር አንጡራ ሃብት እየመዘበሩ:: በገዛ መሬቱ በተወለደበት፤ ዕትብቱ ተቆርጦ ለተቀበረበት፤ ለወርቁ ባለቤት ምንም ሳይሰሩለት … [Read more...] about የአላሙዲ ኪስ በወርቅ ሲታጨቅ፤ አዶላ ኑሮ በጭንቅ!