የራሱ የሆነ ገንዘብ ሳይኖረው “ልማት አከናውናለሁ” በማለት መሬት ሲወስድ፣ አጥር አጥሮ ለዓመታት ባዶ መሬት ከጥቅም ውጪ ሲያደርግ፣ በወሰዳቸውና ፋብሪካ ከፈትኩባቸው በሚላቸው ድርጅቶች አለአግባብ ከመበልጸግ አልፎ ተገቢውን ግብር ባለመክፈል፣ እንዲከፍል ሲገደድ ደግሞ የህወሓት ወንበዴ ሹመኛዎችን በመደለል፣ ኪሳቸውን በማደለብ፣ የሕዝብ ተቀባይነትን ለማግኘት ታዋቂ በሆኑ ግለሰቦችና ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ከሰበሰበው ሃብት ፍርፋሪውን በመጣል “የሕዝብ ልጅ” በመባል፣ በአጠቃላይ የኢትዮጵያን ሐብት በጨበጣ ኪሱ ያስገባው አላሙዲ በለገደንቢ የወርቅ ምርት እንደ ስንዴ በመሰብሰብ የአገርና የሕዝብ ሃብት ሲዘርፍ በወገን ላይ ያስከተለው ጉዳት ትውልድና ዘመን ተሻጋሪ ነው። የአላሙዲ ሚድሮክ ጎልድ የለገደንቢን ምድር ከረገጠ ጊዜ ጀምሮ አካባቢውን የዕርግማን ምድር፤ ቦታውን “የእርም” መሬት በማድረግ ትውልድ አምክኗል። ሃብት በመዝረፍ ብቻ ሳይሆን ህይወትን እና የወደፊት ተስፋንም ጭምር በመዝረፍ ለመስማትና ለማየት እጅግ የሚሰቀጥጥ ግፍ ሰርቷል፤ እየሠራም ነው።
ለመሆኑ የአላሙዲ ሚድሮክ የለገደንቢን የወርቅ ማምረቻን እንዴት እጁ አስገባ? ለዚህ የውንብድና ሥራ ተባባሪዎቹ እነማን ነበሩ? የጨረታው ድራማስ ምን ይመስል ነበር?
ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ “የለገደንቢ ወርቅ ሽያጭ ድራማ!! ወርቃችን እንዴት አላሙዲ እጅ ገባ?” በሚል ርዕስ የዛሬ ስድስት ዓመት አካባቢ አንድ ጽሁፍ አስነብቦ ነበር። ሰሞኑን በዚሁ በለገደንቢ የወርቅ ምርት ጋር ተያይዞ የሚወጡት ዘገባዎችን አስመልክቶ ሚድሮክ እንዴት ይህንን የአገር ሃብት በግፍ በእጁ እንዳስገባው መለስ ብሎ ማየቱ ጠቃሚ ሆኖ ስላገኘነው በድጋሚ አትመነዋል።
የለገደንቢ ወርቅ ሽያጭ ድራማ!!
እ.አ.አ በ1997 በጨረታ ወደ ግል ንብረትነት ተዛወረ የተባለው የኢትዮጵያውያን ሀብት የተሸጠው 172 ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡ሽያጩ ተግባራዊ ከሆነ በኋላ ሽያጩን ተከትሎ በርካቶች አርረዋል፤ ተቃጥለዋል። “ዋይ ዋይ ወርቃችን” ብለው አንብተዋል። ህዝብ የፈለገውን ቢል ደንታ የሚሰጠው አካል ስለሌለ የለገደንቢ ወርቅ ማዕድን ከኢትዮጵያ ህዝብ እጅ በአዋጅ ተነጠቀ።
ሽያጩን እውን ያደረገው የኢትዮጵያ የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት የወቅቱ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሀሰን አሊ ሲሆኑ፣ የአቶ ስዬ አብርሃ ወንድም አቶ አሰፋ አብርሃ የኤጀንሲው ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ነበሩ። ሁለቱም ባለስልጣናት ዛሬ ሃላፊነት ላይ የሉም። ስለ እውነትና ስለ አገር ሲሉ የሚያውቁትን ለመተንፈስ እስከዛሬ ቢጠበቁም ያሉት ነገር የለም። ሃሰን አሊ ሲኮበልሉ፣ አቶ አሰፋ አብርሃ ከወንድማቸው ጋር በሙስና ተወንጅለው የወህኒ ቤት ጊዜያቸውን አጠናቀው እየኖሩ ነው።
ምዕራብ ሃረርጌ አሰበ ተፈሪ መምህር የነበሩትና ኢህአዴግን መንገድ ላይ የተቀላቀሉት ሀሰን አሊ ካገር መኮብለላቸውን ተከትሎ የተለያዩ መረጃዎች ይወጡ ነበር፡፡ በርካቶች ጉዳዩን ከኦነግ ጋር ቢያያይዙትም “ካገር ውጡ ተብለው፣ ሀብትና ንብረት ተዘጋጅቶላቸው ኮብልለዋል” የሚል መረጃ ለባለስልጣናትና ለባለሃብቱ ቅርብ ነን ከሚሉ ወገኖች እንሰማ ነበር። በወቅቱ ኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ውስጥ በነበረኝ ሃላፊነት ሳቢያ ከሰማኋቸው መረጃዎች ውስጥ ሃሰን አሊ “ውጡ” ተብለው እንደ ኮበለሉ የሰማሁት መረጃ ካለኝ ሃላፊነት ጋር ተዳምሮ እንዳጣራው ወሰንኩና ጊዜ ሰጥቼ አነፈንፍ ገባሁ።
የሌሎችን ባላውቅም እንደ ኦሮሞነቴ የለገደንቢ ወርቅ ማዕድን ውድ ንብረት ለሼኽ መሃመድ ሁሴን አላሙዲ መሸጡ ሁሌም ያንገበግበኛል። ሽያጩን አስመልክቶ የተለያዩ ጽሁፎች ቢወጡም እኔ ካሰባሰብኩት መረጃና እውነት ጋር የሚመጣጠን መስሎ ስላልታየኝ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ለመተንፈስ ወሰንኩ።
ሼኽ መሐመድ አላሙዲና ሃሰን አሊ እንዴት ተዋወቁ?
ሼኽ መሀመድ አላሙዲና ሀሰን አሊን እንዳስተዋወቃቸው የነገረኝን ሰው ባንድ አጋጣሚ የማወቅ እድል አጋጥሞኝ ነበር። ተግባሩ ብዙም ደስ ስለማያሰኝ ፊት እነሳው ነበር፡፡ ባለስልጣናትን በገንዘብ እየደለለ ሲሰርቅ ብዙ ጊዜ ስለማውቅ አልወደውም ነበር። የራሱን ትልቅነት ለመግለጽ ድንገት ቢሮዬ በመጣበት ወቅት የነገረኝ ፍንጭ ትዝ ሲለኝ ላገኘው ወሰንኩ። ይህ ሰው ባለኝ ሃላፊነት እንደፈለገኝ ላገኘው ስለምችል፣ እሱም ለሚሰራው ድለላና አየር ባየር ንግድ እኔ ከፈለኩት ቅር ስለማይለው ፊት ነስቼው ያቋረጥኩትን ግንኙነት እንደገና መቀጠል ብቸኛ አማራጬ ሆነ። ይህን ሰው ከተጠቀሙበት በኋላ ወርውረውት በነበረበት ወቅት ላይ ስላገኘሁት የፈለኩትን ለማግኘት አጋጣሚው ተመቻቸልኝ።
ቀደም ሲል ሃሰን አሊን ያውቃቸው እንደነበር፣ አብረው ሃድራ እንደሚያሞቁ፣ የፈለገውን ነገር ማድረግ ከፈለገ ሃድራው በሚሞቅበት ወቅት እዛው በሙቀት እንደሚያከናውኑ አውግቶኛል። ለዚህ ጽሁፍ ስለማይጠቅም እንጂ በርካታ ታላላቅ ጉዳዮች ቢሮ ውስጥ ሳይሆን በተፈረሸ መደብ ላይ እንደሚከናወን በስፋት ስም እየጠቀሰ ነግሮኛል። እንግዲህ ይህ ሰው የ“ባለሃብቱ” ወዳጅ ነበር። ለዚያውም የመጀመሪያ!
በዚሁ ሽርክናቸው ሰውየው ሃሰን አሊን መተዋወቅ እንደሚፈልጉ ባሳወቁት መሰረት ሃሰን አሊን በመያዝ ሳር ቤት አካባቢ አገናኛቸው። ባለሃብቱ በወቅቱ ብዙም የሚያውቃቸው ባልነበረበት ወቅት ሃሰን አሊን አስቀድመው ተወዳጁ። በመኖሪያ ቤት ሃድራ ላይ የተመሰረተው ወዳጅነት ጠበቀ። በኦሮሚያ በኩል አድርገው ዋናውን ሳሎን ወረሱ።
ሀሰን አሊ ከኦሮሚያ ፕሬዚዳንትነታቸው ለቀው ስደትን ለምን መረጡ?
አሰበ ተፈሪ የሁለተኛ ደረጃ መምህር እያሉ ወያኔ ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ በረዣዥም በአለም የምግብ ድርጅት ሽንጣም የጭነት ተሽከርካሪዎች በሸራ ተሸፍነው ቀለሃ ሳያባክኑ ወደ ሃረርና ድሬዳዋ ሲተሙ ቆቦ የምትባል የመስመር ከተማ ላይ ሆኜ የመከታተሉ እድል ነበረኝ። ወያኔ የሀረርንና የድሬዳዋን ከተማ ለመያዝ ስትሮጥ አሰበ ተፈሪ ከተማ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከአቶ ሀሰን አሊ ጋር ተገናኙ። ብዙም ሳይቆይ ሀሰን አሊ የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆኑ። አስተማሪው ፕሬዚዳንት በስልጣን በቆዩባቸው ጊዜያት ከሚታሙባቸው ከፍተኛ ሙስናዎች መካከል፣ ባሌ ውስጥ ተከስቶ በነበረው የዋና ከተማነት ጥያቄ ተከትሎ የተቀበሉት ብር ነው። የባሌ ሮቤ ነጋዴዎች ሮቤ በዋና ከተማነት እንድትቀጥል ያሰባሰቡትን አንድ ሻንጣ ብር በስጦታ አቅርበውላቸው ነበር። ያረፉበት ቤት ድረስ የቀረበላቸው ስጦታ ሮቤን በዋና ከተማነት ጸንታ እንድትቆይ ወሰነ። ገንዘብ ተናገረ። ከአገር የመኮብለላቸው ጉዳይ ከዚሁ ጋር ተያያዥ ነው ቢባልም በፖለቲካው መስመር ደግሞ ኦነግ ናቸው የሚል ሰፊ ሃሜት ነበረባቸው። እኔ ባካሄድኩት ማጣራትና በሰበሰብኩት መረጃ መሰረት ቀደም ሲል የጠቀስኩዋቸው ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው፣ አቶ ሀሰን አሊ በለገደንቢ ወርቅ ሽያጭ በሙስና መጨመላለቃቸው ለመኮብለላቸው ዋናው ምክንያት ስለመሆኑ ሚዛን የደፋ ምርመራ አካሂጃለሁ።
የለገደንቢን ወርቅ ማዕድን ለመሸጥ ወጥቶ በነበረው ጨረታ የተለያዩ ኩባንያዎች ቢሳተፉም ሼክ መሀመድ አላሙዲ ያሸነፉበት ድራማና የሀሰን አሊ ወደ አሜሪካ መኮብለል በተመለከተ ያሰባሰብኩትን መረጃ ከዚህ እንደሚከተለው አቀርባለሁ። ለራሴና ለወዳጆቼ ደህንነት ስል ስም ከመጥቀስ ግን እቆጠባለሁ።
ሃሰን አሊ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የሚመሩት የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ የለገደንቢን ወርቅ ሽያጭ ጨረታ ከማስፈጸሙ በፊት ለገደንቢን አስመልክቶ ከፍተኛ የማባበል ስራ ተሰርቷል። በየጊዜው ሲደረጉ የነበሩ ማባበሎችን ይከታተል የነበረው የመረጃ መነሻ እንዳስረዳኝ ለገደንቢ እንደ መስቀል ሰንጋ ጠልፎ የተበለተው አስቀድሞ ነው። ኢህአዴግ በተለይም ህወሃቶች ከኢትዮጵያ ኪስ የሚወስዱትን ንብረት ህጋዊ ለማስመሰል ያቋቋሙት ይህ ኤጀንሲ በቁንጮ አመራሩ መመሪያ ሰጪነት ባካሄደው ጨረታ የደቡብ አፍሪካ ኩባንያዎችም ተሳትፈው ነበር።
አንድ ቀን እዛው ቤት ውስጥ እንደተለመደው ሃድራው እየሞቀ በጨረታው የተሳተፈ የደቡብ አፍሪካ ኩባንያ የተሻለ ገንዘብ ማስገባቱ ባለሃብቱ ጆሮ ይደርሳል። ኩባንያው ያስገባው ገንዘብ መጠን ይገለጽላቸዋል። መጀመሪያ ያስገቡት ሰነድ ተቀይሮ ሌላ ሰነድ እንዲያስገቡ በተነገራቸው መሰረት አዲስ ሰነድ እንዲዘጋጅ ያደርጋሉ፡፡ በዚህ ድራማ ለገደንቢ ወርቅ ማዕድን ከኢትዮጵያ ህዝብ ሀብትነት ወደ ሼክ መሀመድ አላሙዲ ንብረትነት በ1997 ለስምንት ዓመት ተዛወረ።
በዓመት 3.5 ቶን ወርቅ በአማካይ ሲያመርት ቆይቶ ምርቱን በማሳደግ በአሁኑ ሰዓት ከ4.0 ቶን በላይ ማሳደጉን ይፋ ያደረገው ሚድሮክ ጎልድ በዚህ ዓይነት አሳፋሪ ድራማ ወደ ግል ይዞታነት ከተዛወረ በኋላ ሀሰን አሊ አገር ጥለው እንዲወጡ ተወሰነባቸው። የሽያጩ ድራማ ደብዛ መጥፋት ስላለበት ሀሰን አሊ በኦነግ ስም ካገር እንዲኮበልሉ ሁሉም ነገር ተዘጋጅቶ ከተጠናቀቀ በኋላ አሜሪካ ለስራ በሚል ሰበብ እንዲሄዱ ተደርጎ በዛው ቀሩ። አሜሪካን አገር ሱፐር ማርኬትና ነዳጅ ማደያ ተገዝቶላቸው ስለነበር ከነቤተሰቦቻቸው ወደ ንግድ ዓለም መግባታቸው ተሰማ። አሜሪካ ተገኝቼ ማጣራት ባልችልም አደራውን እዚያው ለምትኖሩ ታጣሩትና ትጎለጉሉት ዘንድ አሳስባለሁ። ምንም በሉ ምን የኢትዮጵያው “ለገደንቢ” የግለሰብ “ሚድሮክ” የሆነው በተፈረሸ ፍራሽ ላይ ነው – በምርቃና!!
ከ2005 በኋላ ለገደንቢ ወርቅ የማን ይሆናል?
ሚድሮክ ጎልድ ይፋ እንዳደረገው ሃያ ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ዘመናዊ መሳሪያ ተገዝቶ ወርቅ የማምረቱ ስራ እየተከናወነ ነው፡፡ በማስፋፊያ በተከለሉ ቦታዎች ላይ ከ4.7 እስከ 6.52 ቶን የሚደርስ ወርቅ በዓመት ለማምረት የተጀመረው ስራ ውጤት ማሳየት ጀምሯል፡፡ ስለማስፋፊያ ስራው አዲስ ስምምነት መንግስትም ሆነ ማዕድን ሚኒስቴር ያሉት ነገር የለም። ሚድሮክ ከኮንትራት ዘመኑ (2005) በማለፍ እስከ 2020 በያዘው ዕቅድ ከ70 ቶን በላይ ወርቅ ለገበያ በማቅረብ ለመሸጥ ማቀዱን በመንግስት ሚዲያ ይፋ አድርጓል። 1.6 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ትርፍ እንደሚያገኝም አፉን ሞልቶ ተናግሯል። ይህ ሁሉ ሲሆን አገር ምን ታገኛለች በሚለው ጉዳይ ላይ ጥያቄ ማንሳት ሃጢያት ነው። ያስገድላል፣ ያሳስራል፣ ያስደበድባል …
ለመሆኑ ከ1997 ለስምንት ዓመት ኮንትራት የተሰጠው ለገደንቢ ወርቅ እስካሁን በአላሙዲ እጅ እንዲቆይ የተደረገበት ውልና የውሉ ዝርዝር ለምን ምስጢር ሆነ? በምን ዓይነት አዲስ ውልና ክፍያ ተጨማሪ ቦታ ተከለለ? በምን ያህል ዶላር የሽያጭ ውልና መግባቢያ ባለሃብቱ ወርቁን እንዲዝቁ ተወሰነ? ማዕድን ሚኒስቴር አለሁ ቢል ወይም ራሱ ሚድሮክ በግልጽ በድረ ገጹ ቢያሰፍረው ቢያንስ ቂማችን ይቀንስ ነበር።
ለወትሮውም በብድር እንደተሸጠ የሚነገርለት ለገደንቢ ወርቅ ማምረቻ ብድሩ ሙሉ በሙሉ መከፈሉ በይፋ ባይገለጽም ሀብቷን በድራማ ጨረታ በብድር የሸጠችው ኢትዮጵያና ህዝቧ ከሃብታቸው ድርሻቸው 2% ብቻ ነው። ከሮያሊቲ ክፍያ ማግኘት የሚገባትን ሚጢጢ ገንዘብ እንኳን ባግባቡና በወቅቱ አታገኝም። የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር አቶ ሱፍያን የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሃላፊዎችን ሰብስበው ሲያነጋግሩ ‘’ለመሆኑ ሚድሮክ ጎልድ ላይ ያለን ድርሻ ስንት ነው? ማስገባት ያለባቸውን ገንዘብስ ይከፍላሉ?” በማለት መጠየቃቸው በወርቅ ማዕድኑ ዙሪያ ያለውን እንቆቅልሽ ወለል አድርጎ እንደሚያሳይ ስብሰባው ላይ የተሳተፉ በወቅቱ የተናገሩት ነው።
ይህ ብቻ አይደለም ከለገደንቢ ከርስ የሚጣራው የኢትዮጵያ ደም /ወርቅ/ ወደገበያ ሲሄድ ቁጥጥር አለመደረጉ ሌላው አስገራሚ ድራማ ነው። አገርና ህዝብ እመራለሁ የሚለው ኢህአዴግ ሚድሮክ በቀጠራቸው ባንዳዎች አማካይነት ወርቁን በሉፍትሐንሳ አውሮፕላን ብቻ የሚያመላልሱት ለምንድነው? ለሚለው ጥያቄ መልስ የለውም። በሌላ አነጋገር አገር የሚገባትን የሽያጥ ታክስም ወደ ውጪ በሚላከው መጠን መሰረት እየተሰላ አይከፈልም። በእንዲህ ዓይነት መልኩ በአገራችን ኢኮኖሚና ህልውና ላይ ይጋለብበታል። ሚድሮክ ወርቅ አንዱ ማሳያ እንጂ ማጠቃለያ ግን አይደለም፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወርቁን ወደሚላክበት ስፍራ በማመላለስ የትራንስፖርት ንግድ ለመነገድ ጠይቆ “አይሆንም” ነው የተባለው ለምን? ኢህአዴግና ባለስልጣናቱ ለዚህም መልስ የላቸውም። አገር ወዳዶች ግን መልሱን ያውቁታል። ልባቸው እየደማ፣ ኅሊናቸው እየቆሰለ፣አገራቸው ስትታረድ የሚመለከቱ ወገኖች ለምንና እንዴት ብለው ሲጠይቁ አሁንም ይገደላሉ፣ ይታሰራሉ፣ ይገረፋሉ፣ ህዝብን በማነሳሳትና በሽብርተኛነት ወንጀል ይከሳሳሉ። እስከ ህልፈታቸው ወህኒ እንዲጣሉ የተሸጡ ወንድሞቻቸው ይፈርዱባቸዋል። በሃገረ ማሪያምና በቡሌ ሆራ ወረዳ የሆነው ይኸው ነው!
ሚድሮክ ወርቅ እያግበሰበሰ ያለው ሃብት ስለጣፈጠው በግልጽ ባልተቀመጠ ውል ግዛቱን እያስፋፋ የአካባቢውን አርሶ አደሮች ሲያፈናቅል የቡሌ ሆራና የሀገረ ማሪያም ነዋሪዎች ከልማቱ ተጠቃሚ አለመሆናቸውንና ባካባቢው ላይ እየደረሰ ያለው ብክለት ጉዳት እያደረሰባቸው መሆኑን ገልጸው በመቃወማቸው በሽብርተኛነት ወንጀል ተከሰዋል።
ጥር 5 ቀን 2002 በሻሸመኔ ምድብ ችሎት በሽብርተኛነት ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው የአካባቢው ተወላጆች ላይ የደረሰውን መከራ የሰብአዊ መብት ጉባኤ 34ኛ መደበኛ ጉባኤ ህዳር 8 ቀን 2003 ዓም ስም በመዘርዘር ይፋ አድረጓል። ከሳምንት በላይ ትምህርት ተቋርጦ በርካታ ተማሪዎችና ነዋሪዎችም ታስረው እንደነበር የሚታወስ ነው።
የፌዴራሉን እንተወውና ኦሮሚያና ሼኽ መሃመድ አላሙዲ በምን ምክንያት ተጣሉ? በወቅቱ የተቀሰቀሰው ተቃውሞና ኦህዴድ፣ ወደፊት የባለሃብቱና የኦሮሚያ እጣ ፈንታ ምን ይመስላል? በሚሉት ርዕሶች ዙሪያ ተጨማሪ ዘገባ ይዤ እመለሳለሁ። በመግቢያዬ እንዳልኩት ዋይ ዋይ ወርቃችን!!
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።
እዝራ says
በጣም ያበሳጫል። በጣምም ያቃጥላል።
የእነ አረጋዊ በርሄ፡፤ ስዬ አብርሃ ፣ ገብሩ አስራት፣ አስፋ አብርሃ((የስዬ ወንድም) ጻዳቃን ገብረ ትንሳይ፣አረጋሽ አዳነ፣ አበበ ተክለ ሃይማኖት(ጆቤ) ግደይ ዘርዓጺዮን ፣ አባይ ወልዱ፣ስብሃት ነጋ፣ ለገሠ ዜናዊ ወዘተ…የትግሬ ወያኔ የማፊያ ቡድን እንዴት የእነ ዱቼ መስሎኒ ተቀጣሪ ሆነው ፣ የተወለዱባትን አገር ኢትዮጵያን እንደሽጡና ምን ያህል ኢትዮጵያን እንደሚጠሉ ከዚህ በላይ ፣ ማስረጃ አይገኘም። ለስሙማ ያለእኛ “”ኢትዮጵያዊነት” ላሳር ነው ባዮች ናቸው። ዛሬም ድረስ ኢትዮጵያን እያደሙ፡ ሃብቷን እየዘረፉ ፤ ሁሉም ነገር ወደ ትግራይ በሚል ከሰማይ በታች ያለ የኢትጵያ ሃብት ሲዘርፉ የሚታይ፤ የሚዳሠስ ሀቅ ሆኖ ሳለ “ትግሬ ታዲያ ኢትዮጵያዊ አይደልም በሚል ምፀት ይሄንን ፍታሃዊ ያልሆነ ዝርፊያ የተቃውመን ሁሉ ፀረ-ኢትዮጵያ ነው” አልፎ ተርፎ ወያኔ ብላችሁ መጥራት በራሱ፣ ትግሬን መሳደብ ነው እስከማለት ደረሰው ነበር። ዛሬ ደግሞ አዲስ ለቅሶ ፈጥረው በ “ትግሬነታችን” የምንገደል ከሆነ ትግራይን እንገነጥላለን እስከ ማለት ሊያሰፈራሩንም ሞክረዋል- የሚፈራ ያለ መስሏቸው።ምነው ባደረጉት እና ባዬን። ትግሬ ወያኔዎች ያልገባቸው ትናንት ኤርትራን ሲያስገነጥሉ ኢትዮጵያዊያኖች እንደተቆጨነው መስሏቸው ነው- ደናቁርቶቹ የወያኔ መንጋዎች እንደማሰፈራራት ሊጠቀሙበት የሞከሩት ። ይህ ብቻ አይደለም፤ እነርሱ ኢትዮጵያን ክደው ከሃዲነታቸው ሳያንስ ፤ ኢትዮጵያን ከመጥላታቸው የተነሳ ለእነ ዱቼ መስሎኒዎች ሸጠው “ከትግሬ በላይ ኢትዮጵያዊ ላሳር” በማለት ወርቅ ህዝብ ነን እስከማለትም ደረሱ። ይሄ ሁሉ ግን ከነበራቸው የማንነት ቀውስና ከበታችነት ስነ ልቡናቸው የተነሳ እንናቃለን ከሚል ጭንቀት ነው። ለዚህ እንደ መረጃ የሚያገልግለን ኤርትራን ከኢትዮጵያ ሲያስገነጥሉ ከኢሳያስ አፈወርቂ በላይ ኤርትራዊ ሆነው ፤ ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ናት ብለው…ለዓለም እስከ ማስተዋውቅ መደረሳቸዉ የአደባባይ ምስጢር ነው። ይሄም በኤርትራዊያኖች በኩል ይንቁናል ብለው ያምኑ ስለነበረ ያንን የንቀት እይታቸዉን እንዲያነሱላቸው (ደግሞም የሚንቋቸው ይመስላል) በኢሳያስ አፈወርቂ ጫማ ስር ወድቀው እንደ ቅጠረኛ ለኤርትራዊያን ሁሉ እስከ መዋጋት ደረስ ሄደው እንደነበር አቶ ገብረ መድህን አርአያ በተደጋጋሚ በመረጃ እያስደገፉ ፅፈዉልናል። በእርግጥም ይሄንን እዉነታ አሁን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በተደጋጋሚ ሲናገር “እኛ ነን ወደ አዲስ አበባ እጃቸውን ይዘን እንዲገቡ ያደረግናቸው” በማለት ዛሬ ግን የሚቆጭበት የታሪክ ጠባሳ መሆኑን የሚገልፀው። ፡ኢሳያስ አፈወርቂ እንዲህም ሲል ይጨምራል፤ እኛ በዚህ መልክ ኢትዮጵያን በጎሳ ሸንሽነው ለጨረታ ያቀርቧታል ብለን አስበን፤ ጠበቀንም አልነበረም – ይሄም በጣም ይቆጨኛል በማለት ደጋግሞ ሲናገር ተደምጧል።። አዎ የኢሳያስ ቁጭት ከኢትዮጵያ አንፃር ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን ተጨንቆ ባይሆንም የኢትዮጵያ ሠላም ማጣት ግን የኢሳያሷን ኤርትራንም ሰላም የሚነሳ በመሆኑ ነው። በአጠቃላይ የትግሬው ወያኔ ተግባርና ባህሪ አደገኛና ለምስራቅ አፈሪቃም አጠቃላይ ጠንቅ የሆነ ማፊያ ነው። ለዚያዉም ኋላቀር ማፊያ። ይሁንና የእነ አረጋዊ በርሄ ድርጀት እንደ ድርጅት፣ የትግሬ ህዝብ እንደ ማህብረሰብ በአጠቃላይ፣ ኤርትራዊያን ይንቁናል የሚል ስነ ልቦናና የበታችነት እንዳላቸው ብዙ ማስረጃዎችን በተግባር ማቅረብ ይቻላል። ለምሣሌ አንዱን ለማሳዬት በአስመራ ከተማ አሠራር ከድሮ ጀምሮ ይቅኑ ስለነበር ሥልጣን ሲይዙ ዛሬ የኢትዮጵያን ህዝብ ሃብት ጨለማን ተገን አድርገው መብራት እያጠፉ፤ ጣሊያን ትቶት የሄደውን የጥነት ጄኔሬተር እንኳ ሳይቀር ነቅለው ወደ ትግራይ በ መውሰድ፣ ዛሬ መቀሌን የአፍሪካ “ሮማ” እስከማለት ደርሰዋል። ምክንያቱም ድሮ አሥመራ ከተማን ኤርትራዊያን የአፍሪካ ሮማ ብለው ይጠሯት ነብርና ነው። ስለዚህ ህወኃት/ወያኔ እስከዚህ ድረስ በነበራቼው የበታችነት ስሜት ከኢሣያስ ጫማ ስርም ወደቀው ኤርትራን እስከማስገንጠል ድረስ የተዋደቁበት አንደኛው ምክንያት፤ በኤርትራዊያኖች ዘንድ እንናቃለን ከሚል የበታችነት ስሜት ተነስተው በትግሬነታቸው ብቻ ለኤርትራዊያን ታማኝ አገልጋይ እስከመሆን ሄደው ነበር። በኋላም የዛሬን አያድርገውና ያኔ “ኤርትራ የግል -ኢትዮጵያ የጋራ”፡በሚል ፖሊሲ አብረው ለመዝረፍ ተስማምተው አብረው ተሠለፉ። ዛሬ ያ ፖሊሲ ተቀይሮ “ትግራይ የግል የትግሬዎች፣ ኢትዮጵያ ግን የጋራ በዋናነት ደግሞ የትግሬዎች ርስት” ትሆን ዘንድ በኢትዮጵያ ላይ ፈርደው በተግባር ኢትዮጵያን እየዘረፉ ይገኛሉ። እነ አረጋዊ በርሄ በኤርትራዊያን እንናቃለን የሚለው የበታችነት ስሜታቸው በእርግጥም እዉነት አለው። ዛሬ ሁሉም ኤርትራዊያን ማለት ይቻላል ትግሬዎችን ሲጠሯቸው አጋመ/ዓጋሜ እያሉ በንቀት ነው፡፡ ዓጋሜ ማለት በኤርትራዊያኖች ዘንድ ዝቅተኛ፣ ከሃዲ፤ የማይታምን፣ የበታች አገላጋይ ማለት ነው። ይህ ብቻ አይደለም – ዛሬ ኤርትራዊያን “በአጋሜ” ተክደናል ባዮች ናቸው። ያም ሆነ ይህ ግን የበታችነት ስነ ልቡና መድኅህኒት የማይገኝለት ፣ እንኳን በተዘረፈና በሚዘረፍ ሃብት ቀርቶ እንደ ዱባይ በነዳጅ ሃበት ተሠርቶ በሚገኝ ገንዘብ እንኳ የማይሽፈን፣ የማይደበቅ የትንሽነት ወይም የባርነት mentality ማለት ነው። ለዚህም ነው የትግሬው ወያኔ ሰዎች በሙሉ ፣ራሳቸዉን የነጭ አገልጋይ አድርገው በገንዘብ ስብዕናቸዉን መሸጣቸዉን እንደ ብልጠት እና እንደ “ኩራት” የሚቆጥሩት። የተወለዱባትን አገር ኢትዮጵያንም እጅግ ከመጥላታቸው የተነሳ ከላይ በጎልጉሎች እንደ ቀረበው ፅሁፍ ኢትዮጵያን ለማንም ሲቸበችቧት ይሄ የዕድገታችን ናሙና ነው ብለው መሸጦነታቸዉን መመጻቂያ አድርገው የሚቆጥሩት። መቼም ለኢትዮኦጵያ እግዚአብሄር አላት። የትግሬ ወያኔዎችን ሜጨረሻ ግን አምላክ ያሳዬን። ከኤርትራዊያን እንኳ ለማማር አልፈለጉም በድንቁርና እብሪታቸውና ጥጋባቸው ምክንያት። በኤርትራዊያን እንዴ ከሃዲ ሲቆጠሩ ፤ በቀሪው ኢትዮጵያዊ ደግሞ እንደ ዘራፊና በልቶ የማይጠገብ ቀዳዳ በርሚል ተደርገው ይቆጠራሉ። እንደዚህ ከመሆን መቼም አምላክ ይሰውረን መጥኔ!
Mulugeta Andargie says
ከሚሠራ ሰው ስህተት አይጠፋም። ቂቂቂ
እዝራ says
Mulugeta Hagos!
ሙሉጌታ ሐጎስ ከሚሠረቅ ሰው ወንጀል አይጠፋም በል። ምክኒያቱም የሚሰረቅ ሰው ወንጀል የሚሠራው ሲጀመር የበታችነት ስለሚሰማው ነው። ሙሉጌታ ሃጎስና የሙሉጌታ ሐጎስ አለቃዎች በሙሉ ከፍተኛ የሆነ የበታችኝነት ሰሜት እንዳላቸው ብዙ መረጃዎች አሉ። ወዲ ሐጎስ