የራሱ የሆነ ገንዘብ ሳይኖረው “ልማት አከናውናለሁ” በማለት መሬት ሲወስድ፣ አጥር አጥሮ ለዓመታት ባዶ መሬት ከጥቅም ውጪ ሲያደርግ፣ በወሰዳቸውና ፋብሪካ ከፈትኩባቸው በሚላቸው ድርጅቶች አለአግባብ ከመበልጸግ አልፎ ተገቢውን ግብር ባለመክፈል፣ እንዲከፍል ሲገደድ ደግሞ የህወሓት ወንበዴ ሹመኛዎችን በመደለል፣ ኪሳቸውን በማደለብ፣ የሕዝብ ተቀባይነትን ለማግኘት ታዋቂ በሆኑ ግለሰቦችና ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ከሰበሰበው ሃብት ፍርፋሪውን በመጣል “የሕዝብ ልጅ” በመባል፣ በአጠቃላይ የኢትዮጵያን ሐብት በጨበጣ ኪሱ ያስገባው አላሙዲ በለገደንቢ የወርቅ ምርት እንደ ስንዴ በመሰብሰብ የአገርና የሕዝብ ሃብት ሲዘርፍ በወገን ላይ ያስከተለው ጉዳት ትውልድና ዘመን ተሻጋሪ ነው። የአላሙዲ ሚድሮክ ጎልድ የለገደንቢን ምድር ከረገጠ ጊዜ ጀምሮ አካባቢውን የዕርግማን ምድር፤ ቦታውን “የእርም” መሬት … [Read more...] about ለገደንቢ “የእርም” መሬት!
legedenbi
በለገደንቢ “ነፍሰጡር ሴቶች ያስወርዳቸዋል፤ ሕፃናት ሲወለዱ ያለጭንቅላት ይወለዳሉ”
ወ/ሮ ሑጤ ደንቆ የሁለት ልጆቻቸው ሞት እንዲሁም የሴት ልጃቸው አካል መጉደል ካደርሰባቸው የሐዘን ስብራት ጋር በጉጂ ዞን ኦዶ ሻኪሶ ወረዳ ዲባ በቴ ቀበሌ ውስጥ ይኖራሉ። እኚህ እናት የመጀመሪያ ልጃቸውን ሁለት እግሯን አልታዘዝ ከማለት በተጨማሪ በኋላ የወለዷቸው ወዲያውኑ እንደተወለዱ ሞተውባቸዋል። ወ/ሮ ሑጤ ነፍሰጡር በነበሩበት ወቅት ከባድ የጤና እክል አጋጥሟቸው የነበረ ቢሆንም አሁንም የአጥንት ሕመም ህይወታቸውን አቀበት አድርጎባቸዋል። የእሳቸውን እና የልጆቻቸውን ጤንነት ይከታተሉ የነበሩ የህክምና ባለሙያዎች የእሳቸው አጥንት ህመምም ሆነ የልጃቸው እግር አጥንት መልፈስፈስ ምክንያቱ ከፋብሪካው የሚወጣው መርዛማ ኬሚካል መሆኑን እንደነገሯቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ወ/ሮ ሑቴ የሚኖሩበት ዲባ በቴ ቀበሌ የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር ለገደንቢ ወርቅ ማምረቻ … [Read more...] about በለገደንቢ “ነፍሰጡር ሴቶች ያስወርዳቸዋል፤ ሕፃናት ሲወለዱ ያለጭንቅላት ይወለዳሉ”