
አንድ ነጥብ አራት ኪሎ ግራም መጠን ያለው ወርቅ አዲስ አበባ ከሚገኘው የካሜሮን ኤምባሲ ወደ ካሜሮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተላከ መልዕክት በማስመሰል ከሀገር ለማስወጣት ሲሞከር በቁጥጥር ስር ዋለ።
በአዲስ አበባ ኤርፖርት ወደ ካሜሮን ለመጓዝ ዝግጅት ሲያደርግ የነበረ መንገደኛ የዲፕሎማቲክ መልዕክት በማስመሰል ለማሳለፍ ሲሞክር በማሽን በታገዘ ፍተሻ ሊያዝ ችሏል።
የተያዘው ወርቅ በወቅታዊ የብሔራዊ ባንክ የመግዣ ዋጋ ሶስት ሚሊዮን አራት መቶ ሺህ (3,400,000) ብር ግምታዊ ዋጋ ወጥቶለታል።
የገቢዎች ሚኒስቴር የሀገርን ሀብት ከምዝበራ የታደጉ የጉምሩክ ሰራተኞች እና የፀጥታ አካላት ምስጋናውን አቅርቧል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply