ከሳምንታት በፊት የለገደንቢ ወርቅ ሽያጭ ድራማ!! ወርቃችን እንዴት አላሙዲ እጅ ገባ? በሚል ርዕር ላቀረብነው ጽሑፍ የድረገጻችን አንባቢ አሥራደው የሚከተለውን በግጥም የተከሸነ መልዕክት ልከውልናል፡፡ ተናገር መጋዶ ተናገር ሻኪሶ፤ ወርቅ ወዴት ተጋዘ ላንተ አፈሩ ደርሶ፤ ተናገር ሃዲማ ደግሞም ኡላኡሎ፤ እነማን ዘረፉት የወርቁን አሎሎ?! የወርቁን ቡችላ የለገ ደንቢውን፤ ደብዛውን ንገሩን የደረሰበትን?! እነማን ዘረፉት ? ማንስ ከበረበት?! እነማን ተዝናኑ? ማንስ ጨፈረበት?! ድሃ በደከመ ድሃ በሞተበት፤ ጦሙን እንደዋለ አፈር ተንዶበት:: አካፋና ዶማ ይዘው ሳይቆፍሩ፤ ጨለማ መግፈፊያ ሻማ ሳያበሩ፤ ጠብ ሳይል ላባቸው ባቋራጭ ከበሩ፡ ያገር አንጡራ ሃብት እየመዘበሩ:: በገዛ መሬቱ በተወለደበት፤ ዕትብቱ ተቆርጦ ለተቀበረበት፤ ለወርቁ ባለቤት ምንም ሳይሰሩለት … [Read more...] about የአላሙዲ ኪስ በወርቅ ሲታጨቅ፤ አዶላ ኑሮ በጭንቅ!