በአዲስ አበባ በአምስት ክፍለ ከተሞች ብቻ ከ210 ሺህ ካሬ ሜተር በላይ መሬት መወረሩን ኢዜማ አስታወቀ። ፓርቲው አደረኩት ባለው ጥናት በ2012 በጀት ዓመት መስከረም ወር ላይ ለባለዕድለኞች ወጥተዋል ያላቸው ከ95 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቤቱ ለማይገባቸው ሰዎች መተላለፉንም አስታውቋል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ በአዲስ አበባ ህገወጥ የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች እደላን በሚመለከት ለአንድ ወር አደረኩት ያለውን የጥናት ግኝት ዛሬ ይፋ አድርጓል። እንደ ፓርቲው ጥናት መሰረት ከሆነ በአዲስ አበባ አምስት ክፍለከተሞች ማለትም የካ፣ ቦሌ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች ከ210 ሺህ በላይ ካሬ ሜትር ቦታዎች በመንግስት አመራሮች ድጋፍ ተወረዋል። ይህ መሬት ገሚሱ በመንግስት ተቋማት ድጋፍ ጭምር ካርታ … [Read more...] about ኢዜማ፡ በአዲስ አበባ 210ሺህ ካሬሜትር በላይ መሬት ተወርሯል፥ 95ሺህ በላይ ኮንዶ ለማይገባቸው ተሰጥቷል