
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ኢዜማ በአዲስ አበባ እየተደረገ ነው ያለውን የመሬት ወረራና ህገ-ወጥ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እደላ በተመለከተ ሊሰጠው የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ለሁለተኛ ጊዜ ተከለከለ፡፡
የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ እንዳሉት ጋዜጣዊ መግለጫው የተከለከለው መግለጫ የሚሰጥበት ቦታ የሆነው ራስ ሆቴል ከሰላም ሚኒስቴር የተፃፈ ደብዳቤ ስጡኝ በማለቱ፤ የሰላም ሚኒስትር ደግሞ ደብዳቤ ለመፃፍ ባለመፍቀዱ ነው ሲሉ ነግረውናል፡፡
ፓርቲው ለሁለተኛ ጊዜ መግለጫ እንዳይሰጥ ስለተከለከለ፣ መግለጫውን በፅ/ቤቱ ዛሬ ከሰዓት በኋላ እንደሚሰጥ አቶ ናትናኤል ፈለቀ ነግረውናል፡፡
ሸገር ይህንኑ ጉዳይ ለማጣራት ወደ ሰላም ሚኒስትር ቢሮ ደውዬ ተነገረኝ እንዳለው፣ የሚኒስትሯ ፅህፈት ቤት ፈቃዱን የሚሰጠው አካል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚኒስትሮች ኮሚቴ መሆኑን ጠቅሶ፣ ለኢዜማ ደብዳቤው ያልተፃፈለት፣ ሚኒስትሯ ስለሌሉ ነው ብሏል፡፡
ጽሕፈት ቤቱ አክሎም በደብዳቤው ላይ የሚፈርሙት ሚኒስትሯ ስለሌሉ ነው እንጂ፣ኢዜማ ፈቃድ አልተከለከለም ብለዋል፡፡ (ምንጭ፥ ሸገር FM)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply