• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢዜማ በአዲስ አበባ አስተዳደር ላይ ክስ መሠረተ

October 12, 2020 11:38 pm by Editor Leave a Comment

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሰሰ። ፓርቲው ክሱን የመሰረተው የከተማው አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት በሰጠው ትዕዛዝ፤ የፓናል ውይይት እንዳያደርግ መከልከሉን በመቃወም ነው።    

በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ፍትሐ ብሔር ችሎት ባለፈው አርብ መስከረም 30፤ 2013 የተከፈተው የክስ መዝገብ፤ በፓርቲው ላይ የደረሰው “የሁከት ተግባር እንዲታገድ” የሚጠይቅ ነው። ኢዜማ ይህን ክስ ለማቅረብ የተገደደው ሕገ መንግስታዊ የሆነው “የመሰብሰብ መብት” በተከሳሽ መስሪያ ቤት በተሰጠ ትዕዛዝ በመገደቡ መሆኑን ገልጿል። 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ለክስ ያበቃውን ትዕዛዝ ለፓርቲው የጻፈው ባለፈው ሳምንት ሰኞ መስከረም 25፤ 2013 ነበር። በከተማይቱ ከንቲባ ጽህፈት ቤትና ካቤኔ ጉዳዮች ኃላፊ በሆኑት አቶ ኤፍሬም ግዛው ፊርማ የተላከው ደብዳቤ፤ ፓርቲው ለመስከረም 28 የጠራውን የፓናል ውይይት እንዲሰረዝ ያሳስባል። 

ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የኢዜማ የፓናል ውይይት ትኩረቱን ያደረገው፤ በአዲስ አበባ ከተማ በከፍተኛ ሁኔታ ተንሰራፍቷል በተባለው ሕገወጥ የመሬት ወረራ እና ፍትሃዊ የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) ዕደላ ጉዳይ ላይ ነበር። ፓርቲው የፓናል ውይይት ለማድረግ የተነሳው በጉዳዩ ላይ ያደረገውን ዝርዝር ጥናት ባለፈው ነሐሴ ወር መጨረሻ ለህዝብ ይፋ ካደረገ በኋላ ነው። 

በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኖ የሰነበተውን ይህን ጥናት እንዲካሄድ የወሰነው፤ የኢዜማ ብሔራዊ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንደነበር ፓርቲው በክሱ ማብራሪያ ላይ ጠቅሷል። የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በጉዳዩ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እንዲደረግ ተጨማሪ ውሳኔ ማስተላለፉን ተከትሎ ፓርቲው ለመስከረም 15 በፓርቲው ጽህፈት ቤት ውይይት ጠርቶ እንደነበር አስታውሷል።  

ሆኖም ከከተማ አስተዳደሩ እና ከጸጥታ አካላት ጋር በተደረገ ውይይት፤ ዕለቱ የመስቀል በዓል ደመራ መሆኑንና በሳምንቱም የኢሬቻ በዓል የሚከበር ስለሆነ “በቂ የጸጥታ ጥበቃ እንደማይኖር” እንደተገለጸለት ፓርቲው በክሱ ዝርዝር ላይ አስረድቷል። በዚህም ምክንያት የፓናል ውይይቱን የሚካሄድበትን ቀን ለመስከረም 28 ማስተላለፉን እና ይህንኑም ለከተማው አስተዳደር፣ ለጸጥታ አካላት እና ለተሳታፊዎች ማሳወቁን አብራርቷል። 

ኢዜማ ውይይቱን ለማድረግ ዝግጅቱን አጠናቅቆ በሚጠባበቅበት ወቅት፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ውይይቱን ማድረግ እንደማይችሉ በደብዳቤ ማሳወቁን አመልክቷል። ፓርቲው ጽህፈት ቤቱ የሰጠውን ይህን ማሳሰቢያ “ህገ ወጥ ትዕዛዝ” ሲል በክሱ ላይ ጠርቶታል። 

“በሕገ መንግስቱ መብት የማክበርና የማስከበር ግዴታና ኃላፊነት የተሰጠው ተከሳሽ መስሪያ ቤት፤ ግዴታውን ካለመወጣት አልፎ የመብት አደናቃፊ መሆኑ በጣም አሳሳቢ እና እንደ ፓርቲም ሆነ እንደ ሀገር ልንገነባው የምናስበውን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት እንቅፋት የሚሆን የመብት ረገጣ ተግባር በከሳሽ ፓርቲ ላይ ፈጽሟል” ሲል ኢዜማ በክሱ ላይ አትቷል። 

ሕገመንግስታዊ የመሰብሰብ መብቱን “በፍርድ ኃይል እንዲከበር” በማሰብ ክሱን ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ለማቅረብ መገደዱን የገለጸው ፓርቲው፤ ክሱ ከቀረበለት ፍርድ ቤት በሁለት ጉዳዩች ላይ ዳኝነት ለማግኘት ጥያቄ አቅርቧል። የመጀመሪያው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት በሕግ ከተሰጠው ስልጣን ውጪ ፓርቲው ሊያደርግ የነበረውን ውይይት መከልከሉ “ሕገ ወጥ ድርጊት ነው” በማለት ውሳኔ እንዲሰጥ ያመለከተበት ነው።

ሁለተኛው ደግሞ ፓርቲው ስብሰባ እና ውይይት እንዳያደርግ፤ ተከሳሽ መስሪያ ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ እንዲያነሳ እና ወደፊትም ተመሳሳይ የመብት ጥሰቶችን ከማድረግ እንዲቆጠብ፤ ፍርድ ቤቱ ግልጽ ትዕዛዝ እና ውሳኔ እንዲሰጥ የጠየቀበት ነው። ፓርቲው ጉዳዩን የሚያስረዱለት ሁለት የሰው ማስረጃዎችን በክስ መዝገቡ ላይ የጠቀሰ ሲሆን ሶስት የሰነድ ማስረጃዎችንም አያይዞ አቅርቧል። 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ለፓርቲው የጻፈው ደብዳቤ በሰነድ ማስረጃነት ከቀረቡት ውስጥ አንዱ ነው። ጽህፈት ቤቱ በዚሁ ደብዳቤው፤ ኢዜማ ከመሬት ወረራና ከጋራ መኖሪያ ቤቶች አንጻር ያነሳቸውን ጉዳዮች የከተማው አስተዳደር “በጥሞና” መመልከቱን ገልጿል። አስተዳደሩ “የመረጃውን ወይም ጥቆማውን ተገቢነት በመመርመር ተገቢውን አስተዳደራዊና ህጋዊ ውሳኔዎችን ለመስጠት በተግባራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ መሆኑን”፤ የፓርቲው የበላይ አመራሮች ከምክትል ከንቲባ አዳነች አበቤ ጋር በተገናኙበት ወቅት መግለጹንም አስታውሷል። 

በፓርቲው አመራሮች እና በከተማው የስራ ኃላፊዎች ዘንድ “መግባባት” እንደነበር የሚጠቅሰው ጽህፈት ቤቱ፤ መረጃው እየተጣራ በሚገኝበት ወቅት ኢዜማ የፓናል ውይይት ማዘጋጀቱን የሚገልጽ ደብዳቤ እንደደረሰው አመልክቷል። አስተዳደሩ ቀደም ሲል ደርሰንበታል ባለው መግባባት እና በሶስት ምክንያቶች መሰረት የፓናል ውይይቱ መሰረዝ እንዳለበት በደብዳቤው አሳስቧል። 

የመጀመሪያው ምክንያት “አስተዳደሩ የጀመራቸውን ስራዎች መጨረስ ስለሚገባው” የሚል ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ “እንደዚህ አይነት የማጥራት ተግባራት የመንግስት ኃላፊነት ሆኖ ሳለ በሌላ መንገድ መሄዱ ተገቢነት ስለሌለው” መሆኑ በደብዳቤው ተጠቅሷል። ለፓናል ውይይቱ መሰረዝ የከተማይቱ አስተዳደር በመጨረሻነት የጠቀሰው “የማጥራት ስራውን አስተዳደሩ ባለጠናቀቀበትና በትጋት እየሰራ ባለበት ወቅት ውይይት መጥራት ወደ ሌላ አተካራና ምናልባትም ወደ ግጭት የሚወስድ ነው” የሚል ነው። 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ባሰረዘው የፓናል ውይይት ምክንያት የቀረበበትን ክስ ለመመልከት ገና ቀጠሮ እንዳልተሰጠ የኢዜማ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። ፍርድ ቤቱ በቀጣዩቹ ቀናት ቀጥሮ ሊሰጥ ይችላል ተብሎ እንደሚጠበቅም አስረድተዋል። (በተስፋለም ወልደየስ፤ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, News, Politics Tagged With: addis ababa land grab, addis condo, ezema

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule