• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ወቅታዊ መግለጫ

October 8, 2020 11:26 pm by Editor Leave a Comment

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ መስከረም 15/2013 ዓ.ም ባካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባው፣ በከተማዋ የተጀመረውን ትምህርት ተሞክሮ እና አገልግሎቶች በአካታች ልማት (inclusive development) መርህ መሰረት አዲስ አበባ ዙሪያ ልዩ ዞን ወይም የኦሮሞ ብልጽግና “የፊንፊኔ ልዩ ዞን” በሚል መጠሪያ ባካተታቸው አካባቢዎች በሚገኙ 346 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚማሩ አንድ መቶ ሃምሳ ሁለት ሺህ(152,000) ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ፣ የተማሪ ደንብ ልብስ፣ጫማ እና የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችል 669,210,780 (ስድስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሚልዮን ሁለት መቶ አስር ሽህ ሰባት መቶ ሰማንያ ብር) በጀት በመመደብ ለእርዳታ አገልግሎቱ እንዲውል በልዩ ሁኔታ ውሳኔ አሳልፏል።

ፓርቲያችን ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ባሉ የወረዳ ከተሞች የሚገኙ ተማሪዎችን በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ ተማሪዎች ለይቶ አያያቸውም፡፡ ተማሪዎቹ የሚኖሩባቸው  የአዲስ አበባ ሳተላይት የወረዳ ከተሞች ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ከተማ ስር የነበሩ ሲሆኑ፣ ባለፉት የህወሓት አገዛዝ ዘመናት ከአዲስ አበባ ከተማ ተነጥቀው ለኦሮሚያ ክልል የተሰጡ የወረዳ ከተሞች ናቸው፡፡ እነዚህ የአዲስ አበባ ሳተላይት ከተሞች ከአዲስ አበባ ጋር ያላቸው ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ትስስር እንደተጠበቀ ሆኖ፣ መጀመሪያውንም በአዲስ አበባ የቀድሞ ይዞታ በነበረው 122,000 ሄክታር ውስጥ ይገኙ የነበሩ የከተማዋ አካል ናቸው፡፡

ራሳቸውን ችለው በሚያመነጩት ባጀት ይህን አሁን በድጋፍ መልክ ባገኙት ባጀት እነሱም ሆነ የኦሮሚያ ክልል ለመሰብሰብ አለመቻላቸው ቀድሞም ቢሆን እነዚህ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ ሳተላይት የወረዳ ከተሞች ከአዲስ አበባ ከተማ ይዞታ ውጭ እንዲሆኑ መደረጋቸው ትክክል አለመሆኑን የሚያስረግጥ ማሳያ ነው፡፡

በባልደራስ እምነት እነዚህ አሁን ከአዲስ አበባ ከተማ የገንዘብ ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎች በአሁኑ አከላለል በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ቢሆኑም የኢትዮጵያ ዜጎች እንደመሆናቸው የነገዋ ኢትዮጵያ ተስፋ ናቸው፡፡ የኦሮምያ ክልል በክልሌ ውስጥ አሉ ለሚላቸው ለእነዚህ ተማሪዎች የሚያስፈልጋቸውን ማሟላት አቅቶት፣ በአዲስ አበባ ነዋሪ ግብር ከፋይ ገንዘብ ትምህርት ቤቶቹ እና ተማሪዎቹ በመረዳታቸው ደስተኞች ነን፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ግን፣ እንደ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ እምነት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በራሱ አነሳሽነት የከተማዋን ነዋሪ ህዝብ ሳያማክር እና ከፌደራል አስተዳደር የፋይናንስ አሰባሰብና አወጣጥ መርሆ ውጭ በሆነ ሁኔታ የበጀት ሽግግር መደረጉ ትክክል አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ሕግን የጣሰ አሰራር መሆኑን በአጽንኦት ለመግለጽ ባልደራስ ይወዳል፡፡ ሲጀመር የኦሮሚያ ክልል ለተማሪዎቹ ችግር የድጋፍ ጥያቄ ማቅረብ ይገባው የነበረው ለፌደራል መንግስቱ እንጂ ለአዲስ አበባ መስተዳድር አልነበረም፡፡ የኦሮሚያ ብልጽግና አመራሮች አዲስ አበባ ራሱን የቻለ አስተዳደር ያለው መሆኑን የማይቀበሉና ከተማዋን በባለቤትነት ለመሰልቀጥ ስለሚያልሙ፣ የበጀት ድጋፍ ጥያቄ ማቅረቡ አስፈላጊ መሆኑን አያምኑበትም፡፡ የፌደራል መንግስቱ ከኦሮሚያ ክልል ለዚህ የበጀት ርዕስ ጥያቄ አቅርቦ የፌደራል መንግስቱ ጥያቄውን ለማሟላት የበጀት እጥረት ካጋጠመው ትክክለኛው አካሄድ መሆን የነበረበት የበጀት ጥያቄውን የፌደራል መንግስቱ ለአዲስ አበባ መስተዳደር ማቅረብና ማስወሰን ነበረበት፡፡ ይህንንም ትክክለኛ አካሄድ መከተል ባይፈለግ የኦሮሚያ ክልል የበጀት ድጋፍ ጥያቄውን ለአዲስ አበባ መስተዳድር በጽሁፍ ማቅረብ ሲገባው ይህንንም አላደረገም፡፡ እያደረገ ያለው ከአሰራር ውጭ በህገ ወጥ መንገድ የአዲስ አበባ መስተዳድርን በጀት መንጠቅ ነው፡፡ ይህ ማን አለብኝነት፣ ተረኝነት እንዲሁም ሽፍትነት ነው፡፡

ለአዲስ አበባ መስተዳድር የበጀት ድጋፍ ጥያቄ ባልቀረበበት ሁኔታ የከተማው መስተዳድር ካቢኔ የወሰነው ውሳኔ የፌደራል ስርዓት መርህን የጣሰ እና የኦህዴድ/ብልጽግናን ፖለቲካዊ ትርፍ በአዲስ አበባ ሕዝብ ኪሳራ ለማወራረድ ታስቦ እንደሆነ ማሳወቅ እንፈልጋለን፡፡ ባልደራስ ይህን ሕገ-ወጥነት በጽኑ ያወግዛል፡፡

በአዲስ አበባ ልዩ ዞን ዙሪያ ያሉ የወረዳ ከተሞች ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር ባላቸው ኢኮኖሚያዊ ትስስር ከከተማዋ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንደሆኑ ፓርቲያችን ይገነዘባል፡፡ ይህንንም ህጋዊ በሆነ የአሰራር ስርአት ይበልጥ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም እንረዳለን፡፡ ወደፊትም ለተግባራዊነቱ አጥብቀን እንሰራለን፡፡ ሆኖም ግን እነዚህ የተሻለ እንቅስቃሴ አላቸው የሚባሉ የወረዳ ከተሞች (ሰበታ፣ ቡራዩ፣ ሱልልታ፣ ወዘተ…) ተማሪዎቻቸውን በራሳቸው ገቢ መመገብ አቅቷቸው በአዲስ አበባ ገንዘብ መደጎማቸው የሚያመለክተው አጠቃላይ የኦሮሚያ ክልል ከኢኮኖሚ ጥገኝነት ወጥቶ እራሱን በራሱ ማስተዳደር የማይችል መሆኑን ነው፡፡ የኦሮሚያ ብልጽግና “የፊንፊኔ ልዩ ዞን” የሚላቸውን በአንፃሩም ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ደግሞ “የአዲስ አበባ ልዩ ዞን” ብሎ ለሚጠራቸው ሳተላይት የወረዳ ከተሞች ከአዲስ አበባ ከሚያገኙት የኢኮኖሚ ጥቅም አንፃር ለሌላው ረጂ እንኳን ባይሆኑ፣ እስከዛሬ ቢያንስ የራሳቸውን ወጪ መሸፈን ሲገባቸው፣ በአዲስ አበባ ከተማ ወጪያቸው እንዲሸፈን መደረጉ ቀድሞውኑም ቢሆን እነሱን ከአዲስ አበባ ይዞታነት አውጥቶ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ እንዲካለሉ መደረጉ የፌደራላዊ አስተዳደር መርሆዎችን የሚቃረን ነው፡፡ ሲልም አሁን እየተከተልነው ያለው የዘውግ የፌደራል አወቃቀር መክሸፍን የሚያስረዳ የተግባር ማሳያ ነው፡፡

በፌደራል ስርዓቱ ውስጥ የተቋቋሙ ክልሎች፣ በህወሓት/ኦነግ/ ኦህዴድ ሕገ መንግስት ውስጥ ሲዋቀሩ መመዘኛው ፖለቲካዊ የሆነ የብሄር ጽንፈኝነት እንጅ የፌደራል አሃዶች ሲዋቀሩ ጥቅም ላይ ሊውል የሚገባው የግዛቶች በኢኮኖሚ አቅም ራስን የመቻል መመዘኛ ግምት ውስጥ አለመግባቱን የሚያሳይ ነው፡፡

በፖለቲካ ውሳኔ ከአዲስ አበባ ውጭ እንዲሆኑ የተደረጉ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ የወረዳ ከተሞች ከ30 ዓመታትም በኃላ በኢኮኖሚ እራሳቸውን መቻል አለመቻላቸው ቀድሞንም ቢሆን የዘውግ ፖለቲካ መግለጫ የሆነው የቋንቋ መመዘኛ የከሸፈ መመዘኛ እንደነበረና አሁንም እንደሆነ ያስገነዝባል፡፡ በማናቸውም የፌደራል አገሮች ራስ ገዝ አስተዳደሮች ሲመሰረቱ ጥቅም ላይ ሊውል የሚገባው ዋነኛ መመዘኛ በኢኮኖሚ ራስን የመቻል መርህ ነው፡፡ ይህም ደግሞ በህወሃት/ኦነግ/ ኦህዴድ የተዋቀረው ቋንቋን ብቸኛ የፌደራል ስርዓት የአወቃቀር መመዘኛ ሆኖ መቀጠሉ ትክክል ስላልሆነ አወቃቀሩ በአዲስ መፈተሸ እንዳለበት ግልጽ ነው፡፡

ስለሆነም ፓርቲያችን ከላይ ያነሳቸውን ቁምነገሮች መሠረት በማድረግና አዲስ አበባን ራስ ገዝ ለማድረግ ከጀመረው እንቅስቃሴ አንፃር፡-

1ኛ. የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደርን እርዳታ በኦፊሴል ሳይጠይቅ  የከተማውን ህዝብ ገንዘብ በፈለገ ጊዜ ተነስቶ ለራሱ ክልል መንጠቁ የፌደራል ስርዓትን እና ዓለም አቀፍ ተሞክሮን ያልተከተለ በመሆኑ ይህ አይነት አሰራር እንዲታረም እና እንዳይደገም እንጠይቃለን፡፡

2ኛ. የአዲስ አበባ ከተማ ለኦሮሚያ ክልል የሰጠው እርዳታ ከታለመለት ዓላማ ውጪ እንዳይውልና እና እንዳይባክን የቁጥጥር ስርዓት ተዘርግቶ በአፈጻጸሙ ላይ ክትትል እንዲደረግ በአጽንኦት እንጠይቃለን፡፡ የበጀት አፈፃፀሙንም ለአዲስ አበባ ምክር ቤት ሪፖርት እንዲያቀርብ ፓርቲያችን ይጠይቃል፡፡

3ኛ. ለመታዘብ እንደቻልነው በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ከተሞች የሚኖረው ህዝብ “የፊንፊኔ ልዩ ዞን” በሚል ታሪካዊም ሆነ ህጋዊ ድጋፍን ባልተመረኮዘ ሁኔታ፣ ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ይዞታ ውስጥ የነበሩ ወረዳዎችን በኦሮሚያ ክልል ውስጥ እንዲካለሉ መደረጉ አግባብነት እንደሌለው ከግንዛቤ ውስጥ ገብቶ በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ሳተላይት የወረዳ ከተሞች እንደቀድሞው በአዲስ አበባ ከተማ ይዞታ ስር ተመልሰው እንዲዋቀሩ በአጽንኦት  እንጠይቃለን፡፡

4ኛ. በብሔር ፌደራሊዝሙ ውስጥ የተፈጠሩ ክልሎች ከሶስት አስርት ዓመታትም በኃላ ከኢኮኖሚው እይታ አንፃር አሁንም እራሳቸውን ችለው መንቀሳቀስ አለመቻላቸው በአገር አቀፍ ደረጃ የፌደራል አወቃቀሩ የከሸፈ መሆኑን የሚያመላክት ሲሆን፤ በዚያው ልክ የሃገራችን የፌደራል አወቃቀር ብቻ ሳይሆን የአዲስ አበባ ራስ ገዝ አከላለልም በአዲስ መልክ መቃኘት እንደሚኖርበት ፓርቲያችን ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ያምናል፡፡  

5ኛ. ይህን ሕገ-ወጥነት እና ከተረኝነት የሚመዘዝ ማን አህሎኝነት በፌደራል መንግስቱ ሙሉ እውቅና እና ተሳትፎ የተከወነ መሆኑን ለመገንዘብ ከልጅነት እድሜ ክልል መሻገር ብቻ በቂ ነው፡፡ ስለሆነም ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ይህንን የዘረኝነት እድምታ ያለው አካሄድ በሕግ እና በሕጋዊነት ላይ ብቻ በተመሰረተ አሰራር በአስቸኳይ እንዲታረም ያስገነዝባል፡፡

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ!

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions, Right Column Tagged With: balderas

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule