በግብጹ ፕሬዘዳንት አልሲሲ ላይ የተነሳው ቁጣ በመላው ግብፅ ተቀጣጥሏል፤ የአልሲሲን አገዛዝ ተቃውመው የሚደረጉ ሰልፎች በመላው ግብፅ መደረጋቸውን ቀጥለዋል። የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አልሲሲ በግብፅ አለመረጋጋትና ትርምስ ለመፍጠር ጥረት የሚያደርጉ ሁሉ ከድርጊታቸው ቢታቀቡ ይሻላቸዋል ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን አልጀዚራ ዘግቧል። ተቃዋሚዎች አልሲሲ ስልጣን እንዲለቁ ይፈልጋሉ፤ እንደ ዋና ምክያት የሚያነሱት ደግሞ ሙሰኝነታቸውን ነው። ሲሲ ለአመታት ከጦር ኃይሉ ጋር በመሆን ለፕሬዝዳንቱ ቤተሰብ እና ጓደኞች ይሆኑ ዘንድ ከተገነቡ ቅንጡ ቤቶችና ከሌሎች በርካታ የግንባታ ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል እያሉ ነው። ተቃውሞው ቁጣቸው እየጨመረ በሚመጣ አመፀኞች ተቀጣጥሏል። በተለይ በገጠርና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አካባቢዎች በርትቷል። ህገ ወጥ ግንባታዎች ይቁሙ … [Read more...] about “አልሲሲ የፈጣሪ ጠላት ነው፤ አገራችንን ለቅቀህ ውጣ” የተቃውሞ ሰልፈኞች
Egypt
“ሕዝብ አገዛዙን መገልበጥ ይፈልጋል” የአልሲሲ ተቃዋሚዎች
የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ በመዲናዋ ካይሮና በአጎራባች ከተሞች ዛሬ (ሰኞ) ተካሄደ። በካይሮ ዳርቻ በምትገኘው የጊዛ ከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰልፈኞች የተቃውሞ ትዕይንት ያካሄዱት የፀጥታ ኃይሎችን ማስጠንቀቂያ በመጣስ ነው። ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ካሰሙት መፈክር መካከል “ሲሲ ውጣ” እና “ሕዝብ አገዛዙን መገልበጥ ይፈልጋል” ("Sisi out" and "The people want to overthrow the regime")የሚሉት የማኅበራዊ ሚዲያውን አጨናንቀውት ውለዋል። ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ከመንግሥት ተቃውሞ በላይ አንድ የፖሊስ መኪናን ያቃጠሉ ሲሆን በፖሊስ ላይ ድንጋይ የወረወሩበት ድርጊትን የሚያሳይ ቪዲዮም በማህበራዊ ሚዲያ ተለቋል። አልጀዚራ በዘገባው እንዳመለከተው የአሁኑ ተቃውሞ ከመቀስቀሱ በፊትም የፀጥታ ኃይሎች … [Read more...] about “ሕዝብ አገዛዙን መገልበጥ ይፈልጋል” የአልሲሲ ተቃዋሚዎች
የትራምፕ ለግብፅ መወገን የውስጥ ክፍፍል ፈጥሯል
አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን ዕርዳታ ለመከልከል እያሰበች ነው በአባይ ግድብ ጉዳይ ከጅምሩ ለግብፅ ወገንተኛ መሆኗን ስታሳይ የነበረችው አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የዕርዳታ ዕቀባ ለማድረግ እያሰበች መሆኑን ፎሪይን ፖሊሲ (Foreign Policy) ዛሬ (ረቡዕ) ባወጣው ዘገባ ገለጸ። ይህ የፕሬዚዳንት ትራምፕ አቋም በአስተዳደራቸው ውስጥ ክፍፍል መፍጠሩ አብሮ ተዘግቧል። አባይን በተመለከተ “ማድረግ የምችለውን መንገድ ሁሉ እጠቀማለሁ” በማለት ስትናገር የነበረችው ግብፅ የፕሬዚዳንት ትራምፕን እጅ በመጠምዘዝ በኢትዮጵያ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ በርትታ እየሠራች ነው። ግብፅና አሜሪካ ለዘመናት የቆየ የጥቅም ተጋሪዎች ናቸው። እኤአ ከ1980ዓም ጀምሮ አሜሪካ ለግብፅ $40 ቢሊዮን ዶላር የሚሊታሪና $30 ቢሊዮን ዶላር የኢኮኖሚ ዕርዳታ ማድረጓን የስቴት ዲፓርትመንት መረጃ … [Read more...] about የትራምፕ ለግብፅ መወገን የውስጥ ክፍፍል ፈጥሯል