የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ በመዲናዋ ካይሮና በአጎራባች ከተሞች ዛሬ (ሰኞ) ተካሄደ። በካይሮ ዳርቻ በምትገኘው የጊዛ ከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰልፈኞች የተቃውሞ ትዕይንት ያካሄዱት የፀጥታ ኃይሎችን ማስጠንቀቂያ በመጣስ ነው። ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ካሰሙት መፈክር መካከል “ሲሲ ውጣ” እና “ሕዝብ አገዛዙን መገልበጥ ይፈልጋል” ("Sisi out" and "The people want to overthrow the regime")የሚሉት የማኅበራዊ ሚዲያውን አጨናንቀውት ውለዋል። ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ከመንግሥት ተቃውሞ በላይ አንድ የፖሊስ መኪናን ያቃጠሉ ሲሆን በፖሊስ ላይ ድንጋይ የወረወሩበት ድርጊትን የሚያሳይ ቪዲዮም በማህበራዊ ሚዲያ ተለቋል። አልጀዚራ በዘገባው እንዳመለከተው የአሁኑ ተቃውሞ ከመቀስቀሱ በፊትም የፀጥታ ኃይሎች … [Read more...] about “ሕዝብ አገዛዙን መገልበጥ ይፈልጋል” የአልሲሲ ተቃዋሚዎች
protest
የተቃውሞ ሠልፍ “ሱስ”?!
ሠልፍ፣ ተቃውሞ፣ መፈክር፣ … ያለፉት 50ዓመታት መለያችን ሆኖ ቆይቷል። በተለይ ባለፉት 27ዓመታት ዘመነ ፍዳ ወወያኔ ደግሞ በተለይ በአውሮጳና አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን “ሼም ኦን ዩ …” ሳይሉ የሚያልፍ ወር አልነበረም ቢባል ማጋነን አይሆንም። ለዚህም ይመስላል “አሜሪካ አገር ኋይት ሃውስ ደጃፍ ቆመህ “ኦባማ ይውረድ” ስትል ብትውል ማንም የሚነካህ የለም ሲባል የሰማው ክበበው ገዳ “እኛስ ሃገር ቢሆን አራት ኪሎ ቤተመንግሥት በር ላይ ቆመህ “ኦባማ ይውረድ!” እያልክ ብትጮህ ማን ይነካሃል?” በማለት የቀለደው። ይህ “ማንም አይነካኝም” የሚለው አስተሳሰብ ሊሆን ይችላል በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያውያን የሰልፍ ሱሰኛ እስኪመስሉ ድረስ ለሁሉም ችግር ሰልፍን ብቸኛ አማራጭ ሲያደርጉ የሚታዩት። ያለፉት 27ዓመታት የተወጣው ሰልፍ ውጤት አላመጣም ለማለት አይቻልም። የተወጡም ሰልፎች … [Read more...] about የተቃውሞ ሠልፍ “ሱስ”?!