የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ በመዲናዋ ካይሮና በአጎራባች ከተሞች ዛሬ (ሰኞ) ተካሄደ። በካይሮ ዳርቻ በምትገኘው የጊዛ ከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰልፈኞች የተቃውሞ ትዕይንት ያካሄዱት የፀጥታ ኃይሎችን ማስጠንቀቂያ በመጣስ ነው። ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ካሰሙት መፈክር መካከል “ሲሲ ውጣ” እና “ሕዝብ አገዛዙን መገልበጥ ይፈልጋል” ("Sisi out" and "The people want to overthrow the regime")የሚሉት የማኅበራዊ ሚዲያውን አጨናንቀውት ውለዋል። ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ከመንግሥት ተቃውሞ በላይ አንድ የፖሊስ መኪናን ያቃጠሉ ሲሆን በፖሊስ ላይ ድንጋይ የወረወሩበት ድርጊትን የሚያሳይ ቪዲዮም በማህበራዊ ሚዲያ ተለቋል። አልጀዚራ በዘገባው እንዳመለከተው የአሁኑ ተቃውሞ ከመቀስቀሱ በፊትም የፀጥታ ኃይሎች … [Read more...] about “ሕዝብ አገዛዙን መገልበጥ ይፈልጋል” የአልሲሲ ተቃዋሚዎች