በግብጹ ፕሬዘዳንት አልሲሲ ላይ የተነሳው ቁጣ በመላው ግብፅ ተቀጣጥሏል፤ የአልሲሲን አገዛዝ ተቃውመው የሚደረጉ ሰልፎች በመላው ግብፅ መደረጋቸውን ቀጥለዋል።
የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አልሲሲ በግብፅ አለመረጋጋትና ትርምስ ለመፍጠር ጥረት የሚያደርጉ ሁሉ ከድርጊታቸው ቢታቀቡ ይሻላቸዋል ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን አልጀዚራ ዘግቧል። ተቃዋሚዎች አልሲሲ ስልጣን እንዲለቁ ይፈልጋሉ፤ እንደ ዋና ምክያት የሚያነሱት ደግሞ ሙሰኝነታቸውን ነው።
ሲሲ ለአመታት ከጦር ኃይሉ ጋር በመሆን ለፕሬዝዳንቱ ቤተሰብ እና ጓደኞች ይሆኑ ዘንድ ከተገነቡ ቅንጡ ቤቶችና ከሌሎች በርካታ የግንባታ ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል እያሉ ነው።
ተቃውሞው ቁጣቸው እየጨመረ በሚመጣ አመፀኞች ተቀጣጥሏል። በተለይ በገጠርና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አካባቢዎች በርትቷል። ህገ ወጥ ግንባታዎች ይቁሙ የመሰሉ መፈክሮች እየተሰሙ ነው።
እየወጡ እንዳሉ ዘገባዎች በመላው ግብፅ 40 መንደሮች ላይ የተቀሰቀሰው አመፅ የፖሊስ የኃይል እርምጃ ሊገታው አልቻለም። ኤል ሲሲ ለአመፅ የተጠሩትን ጥሪዎች ግብፃውያን ባለመስማታችሁ አመሰግናለሁ ብለዋል።
በህዝቡ እየተነሱ ያሉ ጥያቄዎችን የሪፎርሙ አካል አድርጎ መንግስት እንደሚተገብራቸውም ገልፀዋል።በስደት ላይ በሚገኘው በግብፃዊው የንግድ ሰው ሞሀመድ አሊ በተደረገው ጥሪ ተቃዋሚዎች በአልሲሲ መንግስት ላይ በማመፅ ጎዳናዎችን እንደ አውሮፓውያኑ ከ መስከረም 20 ጀምሮ እያጥለቀለቁ ነው።
ፖሊስ አመፆቹን ለመበተን አስለቃሽ ጭሶችን ተጠቅሟል። እንደ ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘገባ የግብፅ የፀጥታ ሀይሎች 400 ሰዎችን ሲያስሩ 3 ሰዎች ደግሞ ተገድሏል።
አመጹ ከተጀመረ ጀምሮ የተያዙ እድሜያቸው ያልደረሰ 60 ህፃናትም ከእስር እንዲፈቱ እየተጠየቀ ነው።ህፃናቱ ከ 10 እስከ 15 ዕድሜ ሲሆኑ ሁሉም አመፁ በብዛት ከሚደረግበት ላይኛው ግብፅ ናቸው።
አብዛኞቹ አመፆች በመንደሮችና በገጠራማ አካባቢዎች እየተደረጉ ያሉት ካይሮንና አሌክሳንድርያን በመሰሉ ከተሞች የፀጥታ ሀይሉ ጥብቅ ጥበቃ እያደረገ ስለሆነ ነው።
ባለፈው አመት መስከረም መጨረሻ ላይ ስደት ላይ ያለው ሞሀመድ አሊ ስፋት ያለው አመፅ በጠራ ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ ግብፃውያን በተለያዩ ትላልቅ የግብፅ ከተማ ጎዳናዎች በመውጣት የሲሲ መንግስት ስልጣኑን እንዲለቅ ጠይቀው ነበር።
በስፔን በስደት ላይ የሚገኘው ሞሀመድ አሊ፤ ሲሲ በአሁኑም አመት በአገዛዙ ላይ ግብፃውያን እንዲያምፁ ጥሪ በማድረጉ ግብፅ በአመፅ ታምሳለች። በጥሪው ሰልፈኞች በተለያዩ ግዛቶች በመውጣት ያለፉትን አመታት አመፆችንም አስታውሰዋል።
አል ሲሲ በሐምሌ 2013 ነበር በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት የሀገሪቱን የመጀመርያ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡትን ሞሀመድ ሙርሲን አስወግደው ስልጣን ላይ የወጡት። (በሔኖክ አስራት፤ Ethio Fm 107.8)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply