• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“በኢትዮጵያዊያን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ሀገሪቱን ማተራመስ አለብን” አይማን አብድልአዚዝ ግብጻዊው ፖለቲከኛ

July 5, 2022 12:57 pm by Editor Leave a Comment

በግብጽ በጣም ታዋቂ ፓለቲከኛ ነው። በአገሪቷ የ2005ቱ ምርጫ የቀድሞውን ፕሬዘዳንት ሆስኒ ሙባረክን የተገዳደረ ብቸኛው ሰው ሲሆን የግብጽ ፓርላማ አባልም ነበር።

የኤል ጋህድ ፓርቲ መስራችና ለሊቀመንበር ሲሆን በግብጽ ካሉ ከባድ ሚዛን ፓለቲከኞች አንዱ ነው፤ አይማን አብድልአዚዝ ኑር።

ይህ ግብጻዊ ፓለቲከኛ በይፋ በሚናገርበት አንድ ቪዲዮ ያስተላለፈው መልዕክት አሁን በኢትዮጵያ ላይ ከሚታዩት የጽንፈኞችና አሸባሪዎች ድርጊት ጀርባ ግብጻዊያን የደህንነት ሰዎች እጃቸው እንዳለበት አመላካች ነው።

ግለሰቡ በዚሁ ስብሰባ ላይ “ይህንን ጉዳይ በግል መናገር ይኑርብኝ አይኑርብኝ አላውቅም፤ ነገር ግን ከእኔ በፊት እንደተናገሩት ጓደኞቼ ሁሉ እኔም የምለው በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን የሚታዩ ለውጦችን መጠቀም አለብን” ሲል ይናገራል።

በአትዮጵያ ውስጥ በርካታ የፖለቲካ ተፎካከሪዎች አሉ በማለት እነዚህን ሃይሎች መጠቀም እንደሚገባ የሚጠቅሰው አይማን አብድልአዚዝ፤ “ኢትዮጵያ ውስጥ ኤምባሲ አያስፈልገንም ይልቁንም የሚያስፈልገን በፖለቲካ እና በደህንነት ጉዳዮች ላይ የሚሰራ ግብረ ሃይል ነው” ሲል እቅዳቸውን በግልጽ አስቀምጧል።

በኢትዮጵያ ሁሉም ጉዳዮች ላይ የራሳችንን ሚና መጫዎት አለብን፤ እኔ እንደማስበው ስጋታችንን ለመቀልበስ በጣም አዋጭና በትንሽ ዋጋ የምንጠቀምበት አማራጭ ይህ ነው፤ በኢትዮጵያዊያን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ሀገሪቱን ማተራመስ አለብን” ሲልም ነው አይማን አብድልአዚዝ ኢትዮጵያን ስለማተራመስ መልዕክቱን በግልጽ ያስተላለፈው።

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈጸሙ የንጹሀን ግድያዎች በአሸባሪዎቹ ሸኔ እና ህወሓት የሚፈጸሙ ቢሆንም በዋናነት ከእነዘህ ግድያዎች ጀርባ መንግስት እና የተለያዮ የፓለቲካ ተንታኞች በተደጋጋሚ የውጭ አገራት እጅ እንዳለበት እያስታወቁ ይገኛሉ።

በተመሳሳይም ሱዳን የፈጸመችው የድንበር ወረራና ትንኮሳ የሶስተኛ አገር አጀንዳን ለማስፈጸም እንደሆነ ሲነገር ሰምተናል።

በቅርቡ አስተያየት የሰጡ ረ/ፕሮፌሰር ጌትነት አልማው እንደሚሉት የኢትዮጵያ እድልና ፈተና ከሶት ነገሮች ጋር የተያያዘ ነው። ቀይ ባህር፣ አባይ እና አድዋ ናቸው።

እነዚህ ሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ስለኢትዮጵያ እድልም ተስፋም ናቸው የሚሉት ረ/ፕሮፌሰሩ አሁን ላይ የሚያጋጥሙን ፈተናዎች ከነዚህ ጉዳዮች ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንዳላቸው እና ግብጽን ጨምሮ በቀጠናው የበላይነት ለመያዝ የሚጥሩ ሃይሎች የፈተናዎቻችን ምንጮች እንደሆኑ ያብራራሉ።

ይህንን የረ/ፕሮፌሰሩን ሃሳብ የሚያጠናክረው ደግሞ “በኢትዮጵያ ኤምባሲ ከፍተን የምናደርገው ድርድር በአባይ ላይ ያለንን ጥቅም አያስጠብቅልንም፤ ይልቁንም ኤምባሲያችንን ዘግተን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የደህንነት ስራችንን በማጠናከር ሀገሪቱን ማተራመስ አለብን” የሚለው የግብጻዊያን ፓለቲከኞች ምክክር ነው። (ኢ ፕ ድ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Left Column, Politics Tagged With: Egypt, GERD, operation dismantle tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule