አዲስ አበባ ላይ ታላቅ ለውጥ ያመጣል ተብሎ በብዙዎች ተስፋ የተጣለበት ባልደራስ ባለፈው በተካሄደው ምርጫ የአዲስ አበባ ሕዝብ ድምጽ ነፍጎት አንድም ወንበር በአዲስ አበባ ምክር ቤትም ይሁን በተወካዮች ምክርቤት ሳያገኝ መቅረቱ ደጋፊዎቹን ተስፋ ያስቆረጠና አንገት ያስደፋ ክስተት ነበር። ከሁሉ በላይ በአድናቂዎቹ “ታላቁ እስክንድር“ እየተባለ የሚጠራውና በትንሹ ለ10 ጊዜ ያህል በዘመነ ትህነግ እየተከሰሰ እስርቤት ሲንገላታ የኖረው እስክንድር ነጋ እስርቤት እያለ ምርጫውን እንዲወዳደር ቢደረግም በብልፅግና ተወዳዳሪ ተሸንፎ ሳይመረጥ መቅረቱ ብዙዎችን ያነጋገረ ጉዳይ ሆኖ አልፏል። በኢትዮጵያ ሕግ በፓርቲነት ተመዝግቦ ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ አደርጋለሁ የሚለው ባልደራስ ከፓርቲ ፖለቲካ ወጣ ባለ መልኩ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ የጠላትን ሃሳብ የሚደግፍና የሚያበረታታ፣ የወገንን … [Read more...] about ባልደራስ የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ በመጣል ሊጠየቅ ይገባዋል ተባለ
bereket simon
ኢህአዴግ ኢህአዴግን ማፈን ጀመረ!
የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ስም ሲነሳ አቶ በረከት ስምዖን በግንባር ቀደም ይጠቀሳሉ። የአቶ በረከት ንብረት ሆኖ የመለስን አመራር በታማኝነት ሲያገለግል የኖረው ይህ ተቋም ቆርጦ በመቀጠል፣ የዜጎችን ሃሳብ በማዛባት፣ ወሬን ባለማመጣጠንና የሃሰት ፕሮፓጋንዳ በማስተላለፍ የሚታወቅ ነው። ስለሚጠየፉት የማይመለከቱት እንዳሉ አፍ አውጥተው የሚናገሩም አሉ። ለሙያው ቅርብ የሆኑ አስተያየት ሰጪዎች “ወገንተኛ እንኳን ቢኾን መሰረታዊ የሙያው ግዴታ ሳይጣስ ሊሆን ይገባል። አንድ መገናኛ ማመጣጠን ካልቻለ በራሱ ሙት ነው። እያደር ብቻውን ይቀራል” ሲሉ ኢቲቪን ይገልጹታል። እንደነሱ አባባል ኢቲቪ ከህዝብ ሳይሆን ከራሱ ጌቶችም ጋር ተነጥሎ የአንድ ወገን (ግለሰብ) ሎሌ የሆነ በድርጅት ቅርጽ የሚከላወስ ሱቅ በደረቴ አይነት ነው። ኢቲቪ ሃሳባቸውን፣ ንግግራቸውን፣ አቋማቸውን፣ ጥቆማቸውንና … [Read more...] about ኢህአዴግ ኢህአዴግን ማፈን ጀመረ!
ጥፋቱ የማን ነው?
ኤርትራዊ ሆነው በኢትዮጵያ ከፍተኛ የስልጣን ሃላፊነት የተሸከሙት አቶ በረከት ስምዖን በኢትዮጵያ ላይ የሚፈርድ፣ ዜጎችን የሚያሸማቅቅ፣ ለአገራቸው የተሰውትን የሚያናንቅና በተለይም በውድ አገራቸው የሚመኩ ወገኖችን የሚያኮስስ ንግግር ማድረጋቸው በህወሃት ነባር ታጋዮች ዘንድ ቅሬታ ማስነሳቱ ታወቀ። አቶ ስዬ አብርሃ፣ አቶ ገብሩ አስራት፣ እነ አቶ ተወልደን በስም በመጥራት በኤርትራ ጉዳይ ላይ ጥፋተኛ ያደረጉት አቶ በረከት “አንድነትና አንድ አገር” የሻዕቢያ መዝሙር መሆኑን በመናገር ኢትዮጵያ ውስጥ መገንጠል ለሚፈልጉ ጊዜው ሲደርስ እንደ ኤርትራ መገንጠል መብታቸው መሆኑን ተናግረዋል። በሚኒስትር ማዕረግ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ በረከት ይህንን የተናገሩት Eritrean Oppositions Arabic Paltalk በሚሰኝ የኤርትራ ተቃዋሚዎች የፓልቶክ መወያያ ክፍል … [Read more...] about ጥፋቱ የማን ነው?