የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ስም ሲነሳ አቶ በረከት ስምዖን በግንባር ቀደም ይጠቀሳሉ። የአቶ በረከት ንብረት ሆኖ የመለስን አመራር በታማኝነት ሲያገለግል የኖረው ይህ ተቋም ቆርጦ በመቀጠል፣ የዜጎችን ሃሳብ በማዛባት፣ ወሬን ባለማመጣጠንና የሃሰት ፕሮፓጋንዳ በማስተላለፍ የሚታወቅ ነው። ስለሚጠየፉት የማይመለከቱት እንዳሉ አፍ አውጥተው የሚናገሩም አሉ። ለሙያው ቅርብ የሆኑ አስተያየት ሰጪዎች “ወገንተኛ እንኳን ቢኾን መሰረታዊ የሙያው ግዴታ ሳይጣስ ሊሆን ይገባል። አንድ መገናኛ ማመጣጠን ካልቻለ በራሱ ሙት ነው። እያደር ብቻውን ይቀራል” ሲሉ ኢቲቪን ይገልጹታል። እንደነሱ አባባል ኢቲቪ ከህዝብ ሳይሆን ከራሱ ጌቶችም ጋር ተነጥሎ የአንድ ወገን (ግለሰብ) ሎሌ የሆነ በድርጅት ቅርጽ የሚከላወስ ሱቅ በደረቴ አይነት ነው። ኢቲቪ ሃሳባቸውን፣ ንግግራቸውን፣ አቋማቸውን፣ ጥቆማቸውንና … [Read more...] about ኢህአዴግ ኢህአዴግን ማፈን ጀመረ!
etv
ከሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች
አቶ ግርማ ለጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ዘለፋ መልስ ሰጡ በተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ መድረክ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ መድረክ የምርጫ ስነምግባር ኮዱን ላለመፈረሙ ያቀረቡትን ምክንያትና ዘለፋ አጣጣሉት። አቶ ግርማ ኦክቶበር 22 ቀን 2005 ዓ ም ከሪፖርተር ከጋዜጠኛ ዮሐንስ አምበርብር ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት “ከአይ ዲ ኤ በቀጥታ ተቀዳ የተባለው የምርጫ ስነ ምግባር ኮድ ሁለት ፓኬጆች የተካተቱበት አይደለም” ብለዋል። “ኢሕአዴግ ግን ነጥሎ ያመጣው አንዱን ነው፤ ቀሪ ሁለት ፓኬጆች አሉ፤ እነሱ ይጨመሩ ነው የምንለው፡፡ ምክንያቱም በጣም ጠቃሚ ስለሆኑ ጉዳዮች ነው የሚያስረዱት፡፡ ስለ ምርጫ አስተዳደር የመሳሰሉ፤ ነገር ግን አይፈልጉም፤ ምክንያቱም ምርጫ ቦርድ ወንድማቸውን ሊነካባቸው ነው፡፡ ምርጫ ቦርድ ጠንካራ አስተዳደር … [Read more...] about ከሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች