
በቅርቡ “ሰማይ አንቀጥቅጥ” በሚል ስያሜ ተካሂዶ በቅብብሎሽ “የሻዕቢያ ተቀጣሪዎች” እና አፍቃሪ የትህነግ ሚዲያዎች ያራገቡት የበይነ መረብ ትዕይንት በዋናት የሻዕቢያና የበረከት ስምዖን ሤራ እንደሆነ ተሳታፊዎች አመልከቱ። ርዕዮት ዩቱብ ልዩ ገጸ ባህርይ ተዘጋጅቶለት ድራማውን ከልደቱ ጋር እንዲተውን የተደረገው ሆን ተብሎ እንደሆነም ተጠቁሟል።
በአደባባይ ትህነግና ሻዕቢያን ለጆሮ በሚከብድ ቃላት የሚሳደበው የርዕዮት ዩቱብ ባለቤት ቴዎድሮስ ጸጋዬ ይህንን ገጸ ባህርይ እንዲጫወት የተደረገው ሆን ተብሎ ነው። የዜናው ባለቤቶች እንደሚሉት ቴዎድሮስ ከማንነቱ የተነሳ ለድራማው ተመራጭ አድርጎታል። ይህ ተፈጥሮው ታማኝ ስለሚያስመስለው ድራማውን በደንብ እየተጫወተ መሆኑም ተመልክቷል።
የቴዎድሮስ ገጸ ባህሪ ልክ ልደቱ በ1997 ሕዝብ ጉድ እስኪል ኢህአዴግን እየተሳደበ በመጨረሻ ይፋ ከሆነው ማንነቱ ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ ያስታወሱት የድግሱ ተሳታፊ፣ በረከት ስምዖን የቀረጸው የአየር ላይ ትዕይንት መሬት ሳይነካ አየር ላይ መበተኑን ገልጸዋል።
ሻዕቢያን እና የእነ ደብረጽዮንን ትህነግ ከፍ ዝቅ እያደረገ የሚሳደበው ቴዎድሮስ ጸጋዬ፣ በሁለቱም ላይ በሚያወርደው የስድብ ናዳ ቀድሞውንም የሚጠራጠሩትና ፍጹም የማይቀበሉት ቢኖሩም፣ አምነው የተቀበሉት ጥቂት እንዳልሆኑ መረጃውን ያጋሩን ይናገራሉ። ቴዎድሮስ ግን በገሃድ ሻዕቢያን ከነ ደብረጽዮን ጋር ቀላቅሎ ይወቃና ከመጋረጃው በስተጀርባ ደግሞ ሤራውን ከልደቱ ጋር ይጎነጉናል፤ ሁሉንም በብቃት ይተውናል።
በዚሁ ሚናው አሁን ላይ ለጦርነት ማስጀመሪያ ግብዓት ማሰባሰቢያ ፕሮጀክት ቴዎድሮስ አጀንዳ ተካይ እንዲሆን አግባብ ያለው ሰው ሆኗል። ተመሳሳይ ገጸ ባህርይ ያላቸው ልደቱ አያሌውና ቴዎድሮስ ጸጋዬ ያስተባበሩት “አየር አንቀጥቅጥ” የተባለው የበረከት ስምዖን ፕሮጀክት “አማራን ብሔረተኛ እንዲያደርጉ፤ የአማራን በደል እያጋንኑ አጀንዳ እንዲያደርጉ፤ ቀደም ሲል የተመለመሉና በውጭ አገር ያሉ በብዛት እንዲተገብሩ መመሪ ተሰጥቶአቸዋል፤ አጀንዳው መልኩ ተቀያይሮም ተሰራጭቷል” ሲሉ ዜናውን ያካፈሉን አመልክተዋል።
በዚሁ የሳይበር ላይ ስብሰባ ከተካፈሉት መካከል ውሎ አድሮ ነገሩ የገባቸው ለጎልጉል የዲሲ ተባባሪ እንዳሉት የእነ ጌታቸው ረዳ ደጋፊ በሆኑት ቴዎድሮስ ተቃውሞ ሲሰነዘርበት፣ ነገሩን ወደ ልደቱ ገፍቶቷል። እሱ የአጀንዳ ተካይነት ሚና እንዲጫወት፣ ሌሎች ሻዕቢያ የሚከፍላቸውና በግልጽ የሻዕቢያ ወኪል ሆነው የሚሠሩ ሚዲያዎች እንዲያራግቡት የተደረገው ይህ “የሰማይ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ” በዚሁ ሳቢያ ቀጣይ ዕቅዱ መጨንገፉን ሰምተዋል። ልደቱም ቴዎድሮስም ደጋግመው ቀጣይ ስብሰባ እንደሚኖር የተናገሩት የእምቧይ ካብ ሆኗል፤ ከጠዋት ጤዛ ፈጥኖ ደርቋል።
እነዚሁ ወገኖች፣ የአየር ላይ ሰልፉ የተፈለገው በቅርቡ ሻዕቢያና ትህነግ የአማራ፣ በተለይም የጎጃም አካባቢ ፋኖን በመያዝ በጋራ ሊከፍቱት ላሰቡት ጦርነት ግብዓት እንዲሆን ታስቦ መሆኑን አመልክተዋል።
“ጦርነት ያብቃ፣ ሰላም ይስፈን፣ አገዛዝ ያክትም” የሚል መፈክር ያነገበው ይህ የሳይበር ውይይት “ኢትዮጵያን የሚያስተዳድረው መንግሥት ለሰላም ደንታ የለውም፣ የሰላም ጥሪና ውይይት አይቀበልም፣ በስደት ሆነንም ውይይት ብንል እምቢ አለን፣ ስለዚህ ሁሉንም አማራጭ ጨርሰን ወደ ሌላ አማራጭ ሄድን” በሚል ሻዕቢያ እየተዘጋጀ ላለበት ጦርነት የፕሮፓጋንዳ ግብዓት ለማሰባሰብ ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነ ከተባባሪያችን ለመረዳት ትችሏል።
ልደቱና ቴዎድሮስ ያዘጋጁት የሰማይ ላይ ስልፍ በመቀሌ በተለያዩ አካባቢዎች በተደረጉ ሰልፎች እየታገዘ መሆኑን ለማስረጃ የሚጠቅሱት ወገኖች፣ ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ሕዝብን ለጦርነት ለማነሳሳት የኃጢያት አጠባና የገጽታ ግንባታ ቅድመ ዝግጅት መሠራቱን አስታውሰዋል።
ከመንግሥት ጋር ሲሠሩ የነበሩ ሰዎችን ቃለ ምልልስ በማዘጋጀት በገፊና ጎታች ስልት በተለይ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲህ ብለውኛል፤ በጆሮዬ ሹክ ብለውኛል” የሚሉ አካላት መዘጋጀታቸው ሥራው በዕቅድ ለመሠራቱ ማስረጃ መሆኑን አመልክተዋል። ይህም ሰሞኑን እየተሰማ ያለ ሐቅ ሆኗል።
ታዬ ደንደአ፣ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ወዘተ አደባባይ ወጥተው የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስም የማጥፋት ዘመቻቸውን ከማካሄዳቸው በፊት ሻዕቢያ የትህነግ ሰዎችን ጠርቶ “ሻዕቢያ ጄኖሳይድ ፈጸመብን የሚባል ተረት አቁሙ” የሚለውን ጨምሮ በርከት ያሉ ቀጭን ትዕዛዞች ማስተላለፋቸውን አስታውሰው፣ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲህ አሉን የሚለው የስም ማጥፋት ፕሮፓጋንዳ የሻዕቢያን ኃጢያት ዐቢይ አሕመድ ላይ በመለደፍ ማጽዳት ነው” ሲሉ አድሮ የገባቸውን ጉዳይ በአየር ትዕይንቱ የተገኙ ለዝግጅት ክፍላችን ዘርዝረዋል።
ሻዕቢያን በጠራ ቁጥር “ጄኖሳይደር” የሚለውን ቃል የሚጠቀመው ቴዎድሮስ፤ “አንድ ሰው ሳይቀር ወያኔን ደምስስ፣ ማንም ማምለጥ የለበትም” በሚል ሲቀሰቅስ የነበረውን ገዱ አንዳርጋቸው ይዞ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በማሰደብ የሻዕቢያ ደም አለቅላቂ ሆኖ መታየቱ ከሚሰድበው ሻዕቢያ ደጅ ራሱ የተገረደደ ለመሆኑ ማረጋገጫ መሆኑን ገልጸዋል።
ለተገፉ ሁሉ ድምፅ በሚል ማላዘኛ የዲያስፖራውን ኪስ የሚያወልቀው ቴዎድሮስ “ራሱ በፈጠረው መገርደድ፣ መደፋት፣ ጭንቅላትን ማከራየት፣ የሻዕቢያ ከልት፣ ዘበኝነት፣ ወዘተ በሚሉ ስድቦች ውስጥ ራሱን ሲገልጽ መኖሩ ይፋ ሆኗል” ሲሉ የሳይበር ስብሰባውን ከተካፈሉት መካከል ለጎልጉል የዲሲ ተባባሪ ተናግረዋል።
የርዕዮት ሚዲያ ተመልካች ቁጥር ከፍ እንዲል የሚወጣውን ወጪና ወጪውን ማን እንደሚሸፍን በስፋት ማብራሪያ ለመስጠት ቀጠሮ የያዙት እነዚሁ ምስክሮች “ስብሃት ነጋን አዝሎ፣ የበረከት ስምዖን ሤራ እንደ አጋሰስ ተጭኖ፣ ሻዕቢያን መሳደብ፣ ትህነግን ማንኳሰስ ልክ እሱ እንደሚለው እንደ ትህነግ “ጀኔራሎች” ባህላዊ ማንነት ነው” በማለት የሚያውቁትን ዘርዝረው አስረድተዋል።
ከአየር ላይ ትዕይንቱ በኋላ ስብስቡ በጁን 20 በዝግ ቀጣዩን ስብሰባ ሲያካሄድ በግል ጥያቄ ከቀረበላቸው መካከል ለመገኘት ፈቃደኛ ያልሆኑ እንዳሉ፣ ሴቭ ኢትዮጵያ (Save Ethiopia) የሚባለውና አቶ ከፍያለው ከጀርባ የሚመሩት ስብስብም ነቀፌታ ማሰማቱን የመረጃው ባለቤቶች ጠቁመዋል።
የቪኦኤ አማርኛው ክፍለጊዜ አለቃ የነበረው ንጉሤ አክሊሉ በሰብሳቢነት የሚመራው ሴቭ ኢትዮጵያ የተሰኘው ስብስብ፣ በየሳምንቱ በሚያደርገው ስብሰባ ዘመነ ካሴን ወይም አስረስ አስማረን ከጎጃም ፋኖ በመጋበዝ የሳምንቱን ውሎ ሪፖርት በሚያደምጡበት ስብሰባ ላይ የእነ ልደቱን አካሄድ መከተል እንደማይገባ አንስተው ተወያይተዋል። ይሁን እንጂ የስብስቡ አባል የሆኑት አቶ ዩሱፍ በግላቸው ከእነ ልደቱ ጋር መሰብሰባቸውን በስብሰባው ላይ ለእነ አቶ ንጉሤ አስረድተዋል።
አቶ ዩሱፍ አሰብ ተወልደው ያደጉ የኤርትራ አፋር ሲሆኑ በደርግ መንግሥት አብረው ሠርተው ደርግ ሲወድቅ የተሰደዱ ናቸው። የሚያውቋቸው እንደሚሉት ከሻዕቢያ ዋና ተከፋይ ፕሮፌሰር መሀመድ ሃሰን ጋር በጣምራ የሚሠሩና የቀይ ባህር ጥያቄን በጥብቅ የሚቃወሙና ኢትዮጵያ ጥያቄውን ልታነሳ እንደማይገባ የሚከራከሩ እንደሆኑ በቅርብ የሚያውቋቸው ይናገራሉ።
በበረከት ስምዖን የተጠነሰሰውና “ስልቴዎች” ማለትም ስብሃት፣ ልደቱ፣ ቴዎድሮስ በልዩ ሁኔታ የቀመሩትና ትህነግን በመታደግ ለሻዕቢያ የተሠራው ልዩ የአየር ላይ የነፍስ አድን ሥራ በዚህ መልኩ አየር ላይ ተበትኗል። ስብስቡ “ትዕይንቱን” ከማካሄዱ አንድ ቀን በፊት አገር ቤት ችግሩም ሆነ ትግሉ መሬት ላይ ነው፤ እናንተ ደግሞ የአየር ላይ ናችሁ እንዴት ይሆናል” ተብሎ ለተጠየቀው ልደቱ ሲናገር “አየር ላይም ምድርም ላይ ነን ብሎ ነበር”።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply