በባድመ ጉዳይ የሰሞኑ የህወሓትና የደጋፊዎቹ የማደናገሪያ ጉንጭ አልፋ ሙግት ብዙዎችን ያሰገረመ ከመሆኑ አልፎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድን በፓርላማ በሚያስጠይቅ መልኩ የቀረበ ትዕይንት ሆኖ አልፏል። ራሱ ህወሓት በቆሰቆሰው እሣት የኢትዮጵያን ሕዝብ በ“ድንበር ተደፈረ” ማጭበርበሪያ ካስማገደ እና የፈንጂ ማምከኛ ካደረገ በኋላ አልጀርስ ላይ የአሸባሪና ወንበዴው ህወሓት መሪ በነበረው መለስ ዜናዊ አማካኝነት ባድመን ለኤርትራ አስረክቧል። ከዚያም አልፎ በሌላው ወንበዴ ስዩም መስፍን የኢትዮጵያን ሕዝብ በመዋሸትና ባድመ የእኛ ሆነች ብሎ በይፋ በመናገር አገር የመክዳት ወንጀል ፈጽሟል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ያኔ መለስ እንደፈለገ ይነዳው በነበረው ፓርላማ አማካኝነት ህግ አርቅቆ በነጋሪት ጋዜጣ አስወጥቶ ባድመን ለኤርትራ አስረክቧል። ከዚህ ሁሉ በኋላ ባድመን አስረክቡ ሲባሉ የህወሓት አሸባሪ … [Read more...] about “ባድመ የኛ አይደለም!” በረከት ስምዖን
badme
ጥፋቱ የማን ነው?
ኤርትራዊ ሆነው በኢትዮጵያ ከፍተኛ የስልጣን ሃላፊነት የተሸከሙት አቶ በረከት ስምዖን በኢትዮጵያ ላይ የሚፈርድ፣ ዜጎችን የሚያሸማቅቅ፣ ለአገራቸው የተሰውትን የሚያናንቅና በተለይም በውድ አገራቸው የሚመኩ ወገኖችን የሚያኮስስ ንግግር ማድረጋቸው በህወሃት ነባር ታጋዮች ዘንድ ቅሬታ ማስነሳቱ ታወቀ። አቶ ስዬ አብርሃ፣ አቶ ገብሩ አስራት፣ እነ አቶ ተወልደን በስም በመጥራት በኤርትራ ጉዳይ ላይ ጥፋተኛ ያደረጉት አቶ በረከት “አንድነትና አንድ አገር” የሻዕቢያ መዝሙር መሆኑን በመናገር ኢትዮጵያ ውስጥ መገንጠል ለሚፈልጉ ጊዜው ሲደርስ እንደ ኤርትራ መገንጠል መብታቸው መሆኑን ተናግረዋል። በሚኒስትር ማዕረግ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ በረከት ይህንን የተናገሩት Eritrean Oppositions Arabic Paltalk በሚሰኝ የኤርትራ ተቃዋሚዎች የፓልቶክ መወያያ ክፍል … [Read more...] about ጥፋቱ የማን ነው?