የመንግሥት ሥራ አስፈጻሚ አካል የፍርድ ቤቶችን ውሳኔ ማክበር ካልቻለ ሥርዓት ተሰብሯል ማለት እንደሆነ፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ተናገሩ። ላለፉት አራት ዓመታት ሪፖርት ሊያቀርቡ ባለመቻላቸው አፈጉባዔውን ወቅሰዋል። ፕሬዚዳንቷ ይህን የተናገሩት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ፣ ከፍተኛና ጠቅላይ፣ እንዲሁም የሸሪዓ ፍርድ ቤቶችን፣ የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድና የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ ክንውን ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በገመገመበት ወቅት ነው። ምክር ቤቱ ባካሄደው የአንድ ቀን የፍርድ ቤቶች ግምገማ ከምክር ቤት አባላትና ከሲቪክ ማኅበራት ተወካዮች፣ ፍርድ ቤት ከወሰነላቸው በኋላ ውሳኔ የማይከበርላቸውን አካላት በተመለከተ በርካታ ጥያቄዎች ቀርበዋል። የሕግ … [Read more...] about “(ላለፉት 4 ዓመታት) ሪፖርት ባለማቅረባችን ክቡር አፈ ጉባዔውን በግል እወቅሳቸዋለሁ” ወ/ሮ መዓዛ
federal supreme court
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ የተቋረጠባቸው ሶስት የክስ መዝገቦች ላይ መግለጫ ሰጠ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ የተቋረጠባቸው ሶስት የክስ መዝገቦች የስነ-ስርዓት ሂደቶች ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡- ባለፈው ሶስት ዓመት ተኩል የፌደራል ፍርድ ቤቶች በሕገ መንግስቱ የተሰጣቸውን ሃላፊነት በተገቢው ደረጃ ለማከናወን በርካታ የለውጥ ተግባራትን ሲያከናውኑ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ የለውጥ እርምጃዎች ትኩረት ያደረጉት በተቋማዊ እና በግለሰብ ዳኞች ደረጃ የፍርድ ቤቱን ነጻነት እና ገለልተኝነት ማስከበር ነው፡፡ በተጓዳኝም ለተጠያቂነት ተቋማዊ ስርዓቶች ተዘርግተዋል፡፡ በፍ/ቤቱ አመራሮች እና ዳኞች በኩል ሲደረግ የነበረው ጥረት ዋናው ግብ የሚሰጠው የዳኝነት ዘርፍ ቀልጣፋ፣ ተገማች እና ተደራሽ በማድረግ በፍርድ ቤቱ አገልግሎት ላይ የሕዝብ አመኔታ እንዲጨምር ነው፡፡ በዚህ ወር መጨረሻ በሚዘጋጀው “የፍርድ … [Read more...] about የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ የተቋረጠባቸው ሶስት የክስ መዝገቦች ላይ መግለጫ ሰጠ