• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ የተቋረጠባቸው ሶስት የክስ መዝገቦች ላይ መግለጫ ሰጠ

January 13, 2022 04:03 am by Editor 2 Comments

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ የተቋረጠባቸው ሶስት የክስ መዝገቦች የስነ-ስርዓት ሂደቶች ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

ባለፈው ሶስት ዓመት ተኩል የፌደራል ፍርድ ቤቶች በሕገ መንግስቱ የተሰጣቸውን ሃላፊነት በተገቢው ደረጃ ለማከናወን በርካታ የለውጥ ተግባራትን ሲያከናውኑ ቆይተዋል፡፡

እነዚህ የለውጥ እርምጃዎች ትኩረት ያደረጉት በተቋማዊ እና በግለሰብ ዳኞች ደረጃ የፍርድ ቤቱን ነጻነት እና ገለልተኝነት ማስከበር ነው፡፡ በተጓዳኝም ለተጠያቂነት ተቋማዊ ስርዓቶች ተዘርግተዋል፡፡

በፍ/ቤቱ አመራሮች እና ዳኞች በኩል ሲደረግ የነበረው ጥረት ዋናው ግብ የሚሰጠው የዳኝነት ዘርፍ ቀልጣፋ፣ ተገማች እና ተደራሽ በማድረግ በፍርድ ቤቱ አገልግሎት ላይ የሕዝብ አመኔታ እንዲጨምር ነው፡፡

በዚህ ወር መጨረሻ በሚዘጋጀው “የፍርድ ቤቱ አሁናዊ ሁኔታ” ጉባዔ እንደሚገልጸው በተለያየ ደረጃ የፍርድ ቤቱ አገልግሎትም ሆነ ተደራሽነት እያደገ የመጣ ለመሆኑ ፍርድ ቤቱ በገለልተኛ የጥናት ተቋም የሰራው የሕዝብ አስተያየት ሰርቬይ “public perception survey” አመልክቷል፡፡

ይህም ሆኖ የዳኝነት ዘርፉ አገልግሎት በርካታ ሰብዓዊ ግብዓቶች ያሉበት የስራ ዘርፍ ከመሆኑ አኳያ እና እንደሌሎች ተቋሞቻችን ሁሉ ተግዳሮቶቹ በርካታ በመሆናቸው ስራችን በውሱን ዓመታት የሚጠናቀቅ ሳይሆን እያደገ የሚሄድ ውጤት እያመጣ ያለ ዘርፍ ነው፡፡

ፍርድ ቤት እንደ ሶስተኛው የመንግስት ዘርፍ አገራችን በጦርነት እና በተለዋዋጭ የፖለቲካ ዓውድ በማለፍ ላይ የምትገኝ ቢሆንም በሃገራችን ዘላቂ ልማት እና ሰላም እንዲረጋገጥ የህግ የበላይነት በማክበርና በማስከበር ረገድ የሚጫወተው ሚና እየተጠናከረ እንዲሄድ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ድጋፋቸው እንደሚቀጥል ሙሉ እምነት አለን፡፡

ለዚህ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት የፕሬስ መግለጫ ምክንያት በቀን 28/4/2014ዓ.ም ዐቃቢ ሕግ ክስ እንዲነሳ ለፍ/ቤት ማመልከቻ በማቅረብ ክስ የተነሳባቸው ሶስት መዝገቦች የስነ-ስርዓት ሂደቶች አካሄድ ላይ የፍ/ቤቶች ሚና ምን እንደነበረ ሕዝቡ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው ማድረግ በማስፈለጉ ነው፡፡

ግለሰቦች መብታቸውን ለመጠየቅ ወደ ፍርድ /ቤት የሚያመጧቸው የፍትሐብሔር ጉዳዮችም ሆኑ በዐቃቤ ሕግ በኩል የሚቀርቡ የወንጀል ጉዳዮች ሁሉ በፍ/ቤቶቻችን እና በዳኞቻችን በልዩ ጥንቃቄ የሚታዩ ናቸው፤ መታየትም አለባቸው፡፡

በሌላ በኩል ግን የህዝብ ፍላጎት ያለባቸው ጉዳዮች “በሕዝብ እይታ ውስጥ ያሉ” በማለት በተቻለ ቅልጥፍና እንዲታዩ፣ ሂደታቸውም የስነ-ስርዓትም ሆነ ዋና ሕጎችን ተከትለው እንዲከናወኑ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡

ከዚህ አኳያ የአመልካቾች የምርጫ ጥያቄን በተመለከተ፣ የተጠርጣሪዎች ሰብዓዊ እና የሕክምና አገልግሎት ጥያቄ በተመለከተ፣ እንዲሁም የምስክሮችን ከመጋረጃ ጀርባ ይሰሙ/ አይሰሙ የሚሉትን እና ሌሎች አስቸጋሪ ክርክሮችን ዳኞቻችን ተገቢ ነው ያሏቸውን ብይን አሳርፈውባቸዋል፡፡

እነዚህ እና መሰል ጉዳዮች ለጥናት እና ምርምር እንዲሁም የሕግ ፍልስፍና ማደግ ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉ ናቸው፡፡ ፍ/ቤቱ በነጻነት የመስራት ደረጃ ላይ ለመድረሱ አመላካች ውሳኔዎች ተደርገው ሊወሰዱ ይችላሉ፡፡

ታህሳስ 28/2014 ዓ.ም በሙሉ ወይንም በከፊል በተከሳሾች ላይ በሶስት መዝገቦች የቀረቡ ክሶችን እንዲቋረጡ የፍትህ ሚኒስትሩ ለሚመለከተው ችሎት ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ሕጋዊ ስርዓቱን ተከትለው ተስተናግደዋል፡፡

ጉዳዮቹም የሚከተሉት ናቸው፡፡

– በከሳሽ ዐቃቤ ሕግ እና በተከሳሾች እነ ጀዋር ሲራጅ መሀመድ (በድምሩ 20 ተከሳሾች)

– በከሳሽ ዐቃቤ ሕግ እና በተካሾች እነ እስክንድር ነጋ (በድምሩ 7 ተከሳሾች) እንዲሁም

– በከሳሽ ዐቃቤ ሕግ እና በተከሳሾች እነ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (በድምሩ ስድስት ተከሳሾች ላይ የቀረበው ክስ) የሚመለከቱ ክሶች እንዲቋረጡ ጥያቄ ቀርቧል፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሕገ-መንግስት እና ሽብር ጉዳዮች አንደኛ ወንጀል ችሎት የፍትህ ሚኒስትሩን ማመልከቻ በመመርመር በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀጽ 6(3)ሠ መሰረት ክሱን ያነሱ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ ተከሳሾቹ እንዲለቀቁ “ተከሳሾች በሌላ ወንጀል የማይፈለጉ ከሆነ” ከእስር እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ለማረሚያ ቤት አስተላልፏል፡፡

አሁን በስራ ላይ ባለው ሕግ መሰረት ከሳሽ ዐቃቢ ሕግ በተለያዩ ምክንያቶች ክሱን መቀጠል እንደማይፈልግ ሲያመለክት ፍ/ቤቱ የክስ ይቋረጥ ጥያቄውን በመቀበል በእስር ላይ የሚገኙት ተጠርጣሪዎች እንዲለቀቁ የታዘዘ መሆኑ ሕጋዊ አሰራር መሆኑ ግንዛቤ እንዲፈጠር ይህ የፕሬስ መግለጫ ወጥቷል፡፡

የፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Law, Right Column Tagged With: balderas, eskinder, Ethiopia, federal supreme court, jawar massacre, sebhat nega

Reader Interactions

Comments

  1. gi says

    January 13, 2022 01:23 pm at 1:23 pm

    ሕወኣት በለፉት ዘመናት በሕገመንግስቱ ወይም በተለያዩ የሕግ አዋጆች ላይ ሊመጣ ያለውን ነገሮች ስለሚያውቅ ለራሱ የወንጀል ስራ ያመቻቸው የሕግ ተቋማት ሕወኣትንና ኢሕኣደግ ኣባላትን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ የወጣ፣የተጨመረ፣ሲሆን ከዶር ኣቢይ በኋላ የተደረገው ኣንዳንድ የሕግ ተቋሙ ሪፎርም ማሻሻያ ቢደረግም ደ/ር ኣቢይ በሕዝብ ከተመረጠ በኋላ የፍርድ ቤት ተቋሙ ለአገር አንድነት፣ለፍትሕ፣ለብሔረሰቦች ዕኩልነት፣የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መርዕ መሰረት የሚከተላቸው የሕግ ማሻሻያዎች ብዙ ሕጋዊ ውይይትና ጥናት የሚፈልጉ በየወቅቱ ሊሻሻሉ የሚገቡ ናቸው። በነ ደብረፅዮን መዝገብ የተያዙ ሰዎች ኣንድም በጦር ወንጀል፣ኣንድም በዘር ማጥፋት፣ኣንድም በግል ለሰሩት ነገር በቂ መረጃና በቂ ሰነድ ቀርቦ በመረጃ የተደገፈ ክስ ለፍትሕ ሲባል የሚወሰኑ ናቸው። ለምሳሌ የ80 እና የ90 ኣመት ወንጀለኛ በማሰር የእስረኛው ጤንነት በካንሰር፣በደም ብዛት፣በስኳርና በተለያዩ በሽታ የሚሰቃይ ከሆነ እስረኛውን በእስር ቤት እንዲሰቃይ ማድረግ በሰብ ዓዊ መብት መሰረት ግለሰቡ በመንግሰት ጥበቃ ስር ሆኖ ቢሞት የሚያስከትለው ፓለቲካዊም ሆነ ማዕበራዊ ቀውስ ይኖራል መንግስት ከባድ ትችት ይገጥመዋል። እነዚህ ሽማግሌዎች በግል እየታከሙ በቁም ዕስር ቢቆዩ መንግስት የፍርድ ሂደቱ ሳያልቅ ሰዎች ሊሞቱም ይችላሉ። ያ ማለት መጣራት ያለበት የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ዝም ብለው ይታለፋሉ ማለት ኣይደለም። መሻሻል የሚገባው የሕግ ተቋምና ሕጉ በትክክል እስኪጨመርና የአገሪቱ ሕግ እስኪሆን ድረስ ክስ ማቋረጥ የተገባ ነው። የኘገሪቱን ሕግ በተለይም በሽብር፣በዘር ማጥፋት ፣በጥላቻ፣የሕዝብን ንብረትና የመንግስት ንብረት የሚያወድሙትን ግለሰቦች ቡድኖች በሕግ የመክሰስ መብት ኣሁንም የክልሎችና የፌዴራል መንግስት ነው። የፌዴራል መንግስት ያቋረጠውን ክስ የክልል መንግስት ሊቀጥል ይችላል። በክልል የተሰራውን ወንጀል ማጣራትና ለፌዴራል የማቅረብ ጉዳይ የክልሉ የፍትሕ ተቋም ግዴታና መብትም መሆን ኣለበት። ሕወኣት በኣፋር፣በሃማራ፣በቤንሻጉል ለሰራው ወንጀል ማጣራት ያለበት የክልሉ የፍትሕ ተቋም ሲሆን የፌዴራል ተቋሙም ቴክንካዊ ዕርዳታ ከተጠየቀ ማድረግ ይችላል። የሶስቱም ተከሳሾች ክስ የተለያዩ ቢሆንም በሽብር ኣዋጅ ኣንድ ማድረግ ተገቢ ኣይደለም። በግል የሰሩት ወንጀል በግል መጠየቅ ኣለባቸው።
    በጋራ በተሰራው ወንጀል ቀጋራ የወሰኑት ነገር ቢኖርም ወንጀሉ የተሰራው በሌላ ሶስተኛ ክፍል ከሆነ ወንጀል የሰራው ሰው ሊገደል፣ሊሰወር፣ወይም ከአገር ሊሸሽ ይችላል በዚህ ጊዜ ምንም ማድረግ ኣይቻልም። መንግስት ክስ ሊያቋርጥ ይገደዳል ያ ማለት ግለሰቦቹ ኣሁንም በፌዴራል መንግስቱ ወንጀለኛ ሆነው መከሰሳቸው እስከ ሕይወት ዘመናቸው ይቆያል።

    Reply
  2. Ashebir says

    January 13, 2022 02:51 pm at 2:51 pm

    1. እኔ በመጀመሪያ የስማሁት እስረኞቹ በይቅርታ ተለቀዋል የሚል – ከጠቅላይ ሚንስትሩ፤

    2. ክፍርድ ሚስትሩ ክሳቸ ተቋርጦ ተለቀቁ፤

    3. ኡለተኛው ትክክል ስለመሆኑ ምስክረነት መስጠቱን፤

    ጥያቄ፤ – ጠቅላይ ሚንስትሩ ልክ አደሉም ማለት ነው? ወይስ

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule