የመንግሥት ሥራ አስፈጻሚ አካል የፍርድ ቤቶችን ውሳኔ ማክበር ካልቻለ ሥርዓት ተሰብሯል ማለት እንደሆነ፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ተናገሩ። ላለፉት አራት ዓመታት ሪፖርት ሊያቀርቡ ባለመቻላቸው አፈጉባዔውን ወቅሰዋል። ፕሬዚዳንቷ ይህን የተናገሩት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ፣ ከፍተኛና ጠቅላይ፣ እንዲሁም የሸሪዓ ፍርድ ቤቶችን፣ የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድና የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ ክንውን ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በገመገመበት ወቅት ነው። ምክር ቤቱ ባካሄደው የአንድ ቀን የፍርድ ቤቶች ግምገማ ከምክር ቤት አባላትና ከሲቪክ ማኅበራት ተወካዮች፣ ፍርድ ቤት ከወሰነላቸው በኋላ ውሳኔ የማይከበርላቸውን አካላት በተመለከተ በርካታ ጥያቄዎች ቀርበዋል። የሕግ … [Read more...] about “(ላለፉት 4 ዓመታት) ሪፖርት ባለማቅረባችን ክቡር አፈ ጉባዔውን በግል እወቅሳቸዋለሁ” ወ/ሮ መዓዛ