• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የፌደራል መንግሥቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ንቀት እያሳየ ነው፤ ህወሓትን ያለበት ድረስ ሂዶ ማጥፋት አለበት” – ባልደራስ

January 13, 2022 11:14 am by Editor 3 Comments

“ባልደራስ የራሱን ሚሊሻ አዘጋጅቶ ትህነግን ይግጠም” አስተያየት ሰጪዎች

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ፤ ማዕከላዊ መንግስት ህወሓትን “ያለበት ድረስ ሂዶ ማጥፋት አለበት” ሲል አስታወቀ። ፓርቲው የኢትዮጵያ መንግሥት የመከላከያ ሰራዊቱን ባለበት ጸንቶ እንዲቆይ ያስተላለፈውን ውሳኔንም ነቅፏል። የባልደራስን አቋም የተቃወሙ አስተያየት ሰጪዎች ባልደራስ ውጊያ ከፈለገ ራሱ ሄዶ ትህነግን ይግጠም ሲሉ መግለጫውን ነቅፈዋል

ፓርቲው “መንግሥት ‘ምዕራፍ አንድ’ ያለውን ዘመቻ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሳያረጋግጥ ማቆሙ፤ ትልቅ አደጋ ያዘለ ነው” ሲል ስጋቱን ገልጿል። ህወሓት አሁንም የሀገሪቱን አንድነት ሊፈታተን በሚችል ወታደራዊ ቁመና ላይ ይገኛል” ያለው ባልደራስ፤ መንግሥት “ዘመቻውን ያቆመበትን ምክንያት በተመለከተ በቂ ምላሽ አልሰጠም” ሲል ተችቷል። የፌደራል መንግሥቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ “ንቀት እያሳየ ነው” ሲልም ነቅፏል፡፡

ፓርቲው በመግለጫው እንዳስታወቀው አሸባሪው ህወሓት በጀመረው ጦርነት ምክንያት ሀገራችን ኢትዮጵያ የህልውና ትንቅንቅ ላይ እንደምትገኝ ጠቁሟል፡፡

በዚህም አገርን ለማስቀጠል በተደረገው መስዕዋትነት ፓርቲው ግንባር ድረስ በመሄድ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱንም አስታውቋል፡፡

የሰሜኑ ጦርነት መነሻ አሸባሪው ህወሓት በጀመረው የቅድመ-ማጥቃት እርምጃ መሆኑን እንረዳለን ያለው መግለጫው፣ የፌደራል መንግስት ጥቃቱን ለመከላከል ያደረገው ሀገር አቀፍ ዘመቻ ትክክለኛና ፍትሃዊ እንደነበርም ጠቁሟል፡፡

አሸባሪው ህወሓት አሁንም የአገሪቱን አንድነት ሊፈታተን በሚችል ወታደራዊ ቁመና ላይ ይገኛል ያለው መግለጫው፣ የዘመቻው ፍፃሜ የኢትዮጵያን አንድነት አደጋ ላይ የሚጥለውን የህወሓት ወታደራዊ አቅም በመስበር መቋጫት ይገባል ብሏል፡፡

ከምክክር ኮሚሽኑ ጋር በተያያዘ መንግስት እያካሄደ ያለው እንቅስቃሴ የአገራችንን ፖለቲካዊ ጥያቄዎች በውይይትና በምክክር ለመፍታት ትልቅ እድል እንደሚፈጥር የጠቆመው መግለጫው፣ የምክክር ሂደቱ አትዮጵያን አሸናፊ በሚያደርግ መልኩ እንዲጠናቀቅ እና ግልፀኝነት የተሞላበት ምክክር እንዲሆን ፓርቲው የበኩሉን አስታዋፅኦ እንደሚያደርግ አስታወቋል፡፡

የባልደራስን መግለጫ ተከትሎ አስተያየት የሰጡ መግለጫውን በመደገፍ የተናገሩ ሲሆን ሌሎች ግን ራሳቸው ሄደው የማይዋጉትን ጦርነት መከላከያው ይሂድ ብለው መወሰን አግባብ አይደለም በሚል ነቅፈዋል። በአማራና አፋር የመንደር ሚሊሻዎች ሳይቀሩ ትህነግን ሲዋጉ እንደነበር ባልደራስም እንዲሁ የራሱን ሚሊሻ አስተባብሮ ትህነግን መግጠም ይችላል በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Left Column, News Tagged With: balderas

Reader Interactions

Comments

  1. gi says

    January 13, 2022 12:42 pm at 12:42 pm

    ኣሁንም ባልደራስ የጦርነትና የዕልቂት እንጂ የሰላምና የዕርቅ ወይም ሌላ ኣማራጭ የለውም። ትንሽ ተንፈስ ተብሎ ነበር ኣሁንም ሌላ የሽብርና የከፋፋይነት ዘመቻ በሕዝብ ስም ዕልቂት እንዲፈጠር መወትወት ኣያዛልቅም። በአንድ ክልል ውስጥ ያለ ክልሉ መንግስት ፈቃድ ገብቶ ጦርነት መግጠም ሕገመንግስታዊ ስለ መሆኑ ባልደራስ መረዳት ወይም መጠየቅም ኣልቻለም። የፌዴራል መንግስት የደርግ ዓይነት መንግስት ኣይደለም። እንደፈለገ በክልል መንግስት ውስጥ ጦር አዞ የፈለገውን ለማድረግ ሕገመንግስት ኣይፈቅድም። የትህነኣግ ጦር ከትግራይ ክልል ወጥቶ ሌላውን ክልል ቢወጋ የፌዴራል ጦር ኣስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል። በኣፋር በሃማራ ክልል ወይም ቤንሻጉል በኩል ትህነኣግ ሊዋጋ ቢሄድ መከላከያና የክልል ሚሊሺያ ሊዋጉ ይችላሉ። ትህነኣግ ከሁሉም ክልሎች ከወጣ ግን ያለበት ቦታ ሄዶ መዋጋት መንግስት ኣለበት ብሎ ባልደራስ የመጠየቅ ስልጣን ወይም መብት የለውም። ይህ የባልደራስ ኣካሄድ ከፌዴራሊዝም የራስ መስተዳድሩ መርዕ ጋር ሊጠረስ ስለሚችል ባልደራሶች የሕገመንግስት ሀሁ… ሊማሩ ይገባል።

    Reply
    • Teklebirhan says

      January 16, 2022 04:17 pm at 4:17 pm

      BALDERAS is a legal opposition party fully committed to peaceful struggle only.The primary responsibility to defend the country when attacked by foreign or internal enemies is that of the government in power through the national army and through the mobilization of the entire Ethiopian people including members of BALDERAS.As such,BALDERAS does not have the popular mandate to replace the government in respect .

      Reply
  2. Ashebir says

    January 13, 2022 02:31 pm at 2:31 pm

    ከዚህ በላይ ባለው አጎልጉል ጽሁፍ መጨረሽ ላይ “….. ሌሎች ግን ራሳቸው ሄደው የማይዋጉትን ጦርነት መከላከያው ይሂድ ብለው መወሰን አግባብ አይደለም በሚል ነቅፈዋል።” የሚል ይገኛል። ጉድ እኮ ነው! መክላከያ ያልተላከ ማን ሊላክ ነው? የመከላከያ ሥራውስ ምንድን ነው? በርግጥ መክላከያ ከሌለ ሌላው ሰው መሄዱ የማይቀር ነው። በነገራችን ላይ ባልደራስ የመወሰን መብት የለውም። የማዘዝ/የመውሰን ሥልጣን ያለው ጠ/ሚንስትሩ ነው።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule