“እናንተ የመለስናችሁ ለእረፍት እንጂ ጥያቂያችን መቋጫ አግኝቶ ትግል ስላበቃ አይደለም ። የወልቃይት-ጠገዴ ነፍጥ ገና ይጠብቃል እንጂ አይወርድም። እኔ በዚህ እድሜዬ ጋቢ ለብሼ ከዘራ ይዤ ቤተክርስቲያን ሲሄድ ነበር የሚያምርብኝ። ነገር ግን አሁንም በዚህ እድሜዬ ጠበንጃ ተሸክሜ የምታዩኝ የወልቃይት-ጠገዴ ትግል መቋጫው ገና ስለሆነ ነው። ጥያቄው እልባት ሲያገኝ እናንተም በሙሉ ልብ ወደ ልማታችሁ እኔም ገዘራ ይዤ ጋቢ ለብሸ የምሄድ ይሆናል”
ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ
የወ/ጠ/ሰ/ሁ/ዞን ም/አስተዳዳሪና ሰላምና ደህንነት ሃላፊ
“የወልቃይት-ጠገዴ ህዝብ ሲኖርም በምክንያት ሲሞትም በምክንያት ነው። አሁን እየተዳደርን ያለነው በምንፈልገው የቤጌምድር አማራ ማንነት ነው። በዚህም እንቀጥላለን። በህግ ጥያቄ ያለው ካለ በህግ ይጠይቀን።በህዝብ ፍላጎት መሰረት እስከሆነ ድረስ አስተዳደራችንም ድሮም በነበረው አሁንም ባለው ይቀጥላል።”
አቶ አሸተ ደምለው
የወ/ጠ/ሰ/ሁ/ዞን ዋና አስተዳዳሪ
ሌላኛው “በፌዴራል ተዳደሩ ያለ አካል አለ ወይ?” ተብሎ ከተሳታፊዎች ለተነሳ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የዞኑ የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ዋኘው ደሳለኝ “ፌደራል የመንግስት አወቃቀር እንጂ ማንነት አይደለም። እኛ ፌደራል የሚባል ማንነት የለንም። ከጥንትም ጀምሮ የመጣና ያደገ ማንነታችን የቤጌምድር አማራ ስለሆነ በዛ ፍላጎታችን ነው መተዳደር የምንፈልገው። ስለዚህ ቀጥታ በፌዴራል ስር ሁኑ ያለን የለም። በቀጣይም ያለ ህዝብ ፍላጎት የሚለነ አይኖርም ብዬ አስባለሁ”
“የወረዳችን ዘማቾች፣መንግስት ሰራተኞችና መላው ህዝባችን ከሗላ ደጀን እስከ ፊት ዘመቻ በመሳተፍ ሁለት አመት ሙሉ ያለ መሰልቸት በፈፀማችሁት ገድል ኮርተናል። ቀጣይም እናንተን ይዘን ብዙ ታሪክ እንሰራሪ”
አቶ ጌታሁን ብርሃኔ
የጠገዴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ
በ06/02/15 በወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ግንባር ለቆዩ የጠገዴ ወረዳ ዘማቾች በማ/ገቢያ ከተማ አቀባበል ተደርጓል። በአቀባበሉም ከዘማቾችና ከተመረጡ የህዝብ ተወካዮች ጋር በጋራ የዞንና የወረዳ አመራር ባሉበት ስለወቅቱ የሃገራችን ሁኔታ በተለይ ስለ ወልቃይት-ጠገዴ የቀጣይ ትግል ውይይት ተደርጓል። (Eyachew Teshale)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply