ሰሞኑን ለጥገኝነት ማመልከቻቸው ደጋፊ ነው የተባለለትን ዘለግ ያለ ጽሑፍ ያቀረቡት ገዱ አንዳርጋቸው በትግራይ ማኅበረሰብ ዘንድ የተከፋፈለ ዕይታ የፈጠሩ መሆናቸው ተነገረ። ““የዘር ማጥፋት ወንጀለኛ ነው፤ እጃችን ገብቷል እንክሰሰው” ባዮች በርተተው የታዩ ቢሆንም “ባለውለታችን ነውና አሁንም እንጠቀምበት” የሚሉ በሌላ ወገን ድምጻቸውን እያሰሙ ነው። በዘመነ ትህነግ የሥርዓቱ ተላላኪና ጉዳይ ፈጻሚ የነበሩት ገዱ አንዳርጋቸው የዚያን ጊዜው አለቆቻቸውን ለማስደሰት ያልታዘዙትን፣ ያልተጠየቁትን እላፊ በመሄድ በመፈጸም አለቆቻቸውን እጅ በመንሳት ይታወቃሉ። ለዚህ ታማኝነታቸው በአማራ ሕዝብ ላይ የመጨረሻውን ሥልጣን እንዲያገኙና ሎሌነታቸውን የበለጠ በደስታ እንዲፈጽሙ አድርጓቸዋል የሚሉ ጥቂት አይደሉም። እንደማሳያም የወልቃይትን ጉዳይ ይጠቅሳሉ። ገዱ አንዳርጋቸው ከዚህ በታች ያለው … [Read more...] about ገዱ: “የዘር ማጥፋት ወንጀለኛ ነው እንክሰስው”፤ “ባለውለታ ነው እንጠቀምበት”