• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ካወጣው ዘገባ በተቃራኒ በወልቃይት ጠገዴ ትግራዮች በሰላም እየኖሩ ነው

June 12, 2023 10:17 am by Editor Leave a Comment

በወልቃይት ጠገዴ ንፁሃን የትግራይ ተወላጆች በሰላምና በፍቅር እየኖሩ መሆናቸውን ምስክርነታቸው ሲሰጡ ቆይተዋል። 

እኚህ እናት ወሮ ፀጋ ካህሳይ ይባላሉ። ከትግራይ ወደ ወልቃይት ጠገዴ ማይካድራ ከተማ ከመጡ 50 ዓመት እንዳስቆጠሩ ይናገራሉ። እሳቸው ሲናገሩም “በእነዚህ ረዥም ዓመታት ውስጥ ሃብትና ንብረት አፍርተን ልጆችን ወልደን ከብደንና ከብረን ከወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጋር ኖረናል። ነገር ግን ጥቅምት 24/02/2013 ዓ.ም ሳምሪ የተባሉ ሰዎች በዕድሚያችን በሙሉ አይተነው ሰምተነው በማናውቀው ዘግናኝ ግፍና ጭፍጨፋ በማይካድራ የአማራ ተወላጆች መፈፀማቸውን በአይናችን አይተን ምስክርነታችንን ሰጥተናል” ብለዋል።

እኚህ እናት እውነትን በመናገራቸው ክብር ይገባቸዋል! በነገራችን ላይ ወ/ሮ ፀጋ ካህሳይ የተባሉት እኒህ እናት የመለስ ብስራት ወላጅ እናት ናቸው። መለስ ብስራት ማለት ኑሮውን በእንግሊዝ አገር አድርጎ የወያኔን የጥላቻ ፕሮፓጋንዳና ሃሰተኛ ውንጀላዎች ቀን ከሌት በማስተጋባት የሚታወቅ ነው።

መለስ ብስራት ቀኑን ሙሉ ተጠምዶ ከሚውልባቸው አጀንዳዎች መካከል አንደኛው “በወልቃይት ጠገዴ ውስጥ በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ ግፍና በደል እየደረሰ እንደሆነ በሚወነጅለው የወያኔ የቀን ተሌት ክሴታ” ዙሪያ ላይ ነው።

ይህ የመለስ ብስራት ሃሳዊ ውንጀላ ወላጅ እናቱ ወ/ሮ ፀጋ በሰጡት በዚህ የእማኝነት ቃላቸው መሠረት ባዶና ተራ ውሸት መሆኑን የሚያሳይ ነው።

መለስ ብስራት በመላው የአማራ ህዝብ ላይ ያለውን ለከት የለሽ የጥላቻ መርዙን የሚተፋው ወላጅ እናቱ ማይካድራ ውስጥ በሰላም እንደሚኖሩ እያወቀ መሆኑ ደግሞ ልጁ ምንም አይነት ኅሊና የሌለው መሆኑን የሚያሳይ ነው።

መለስ ብስራት ይሄን ክሴታውን ከልቡ አምኖበት ቢሆን ኖሮ የገዛ ወላጅ እናቱን ወደ ትግራይ ወይም ሌላ ቦታ ወስዶ ማኖር ይችል ነበር። እውነታው ግን እሱ የሚጮኸው በማያምንበትና የወያኔን ፖለቲካዊ ጥቅም በሚያስጠብቅ አጀንዳ ላይ መሆኑ ነው። ይሄንን ሃቅ የሚያውቀው የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ግን ወ/ሮ ፀጋ ካህሳይን ተንከባክቦና ጠብቆ እዚህ ደርሷል! (Asfaw abreha)

በወልቃይት የሚኖሩ ትግሬዎች ይህንን መሰል ሐቀኛ ምስክርነት እየሰጡ ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ድርጅት ደግሞ በወልቃይት በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ተፈጽሟል እያለ የኢትዮጵያን መንግሥት ይከስሳል። ለዚህ ሃሰተኛ ውንጀላ መንግሥት የሚከለውን ምላሽ ሰጥቷል።

ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ድርጅት እ.ኤ.አ. ግንቦት 1/2023 (ግንቦት 24/2015 ዓ.ም) በሀገራችን በአንዳንድ አካባቢዎች ጉልህ የሆኑ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን የሚገልጽ መሰረተ ቢስ ሪፖርት አውጥቷል።

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የነበረው ግጭት በርካታ አካባቢዎችን ለጉዳት ያጋለጠ ቢሆንም በልዩ ሁኔታ የተወሰነ አካባቢን መርጦ ደጋግሞ ሪፖርት በማዘጋጀት በሰብዓዊ መብት አጀንዳ ሽፋን የተለየ የፖለቲካ ተልዕኮዉን ለማሳካት ዓላማ ያደረገ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም። የመብት ጥሰት ተፈጽሟል ለማለት የቀረበው ሪፖርት ይዘት ሲታይም ተገቢው ምርመራ ያልተደረገበት እና በበቂ ማስረጃ ያልተደገፈ ከመሆኑ አንጻር እምነት የሚጣልበት አይደለም።

በአጠቃላይ በድርጅቱ የቀረበው ሪፖርት የተዛባና በአካባቢው ያለውን ነባራዊ ሁኔታ የማይገልጽ፣ ለዘመናት አብረው የቆዩ ሕዝቦችን አብሮ የመኖር እሴት የሚያጠለሽ፣ በሕዝቦች መካከል ግጭት ቀስቃሽ የሆነና ሀገራችን እያደረገች ያለውን የእርቅ እና ምክክር ሂደት የሚያደናቅፍ አሉታዊ ተፅዕኖ ያለው ሪፖርት ሆኖ አግኝተነዋል።

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የነበረው ግጭት በአፋር፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች ውስጥ የሚኖሩ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ ጉዳት ያደረሰ መሆኑ የሚታወቅ ሆኖ ሳለ ድርጅቱ አንድ አከባቢን ለይቶ በመምረጥ ሪፖርት ማውጣቱና ሪፖርቱም ሀገራችን የእርቅ ሂደቱን በተሟላ መልኩ በመተግበር ላይ እያለች በመሆኑ ድርጅቱ ድብቅ አጀንዳውን በሀገራችን ላይ ለማራመድና የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የተዛባ ዕይታ እንዲኖረው ለማድረግ እየሰራ ለመሆኑ ማሳያ ነው። ሀገራችን ኢትየጵያ የሰብአዊ መብቶችን ለማክበርና ለማስከበር የሚያስችሉ የሕግ እና ተቋማዊ አደረጃጀቶች ያሏት ሀገር ስትሆን ይህንኑ ክትትል ለማድረግም እንደ የኢትየጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ያሉ ነጻና ገለልተኛ ተቋማትን አቋቁማለች።

መንግሥት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ፈጽሞ የማይታገስ በመሆኑ ምክንያት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በነበረው ግጭት ተፈጸሙ የተባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እና የተ.መ.ድ. የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽ/ቤት ጥምር የምርመራ ቡድን እንዲያጣሩ አስፈላጊውን ሁኔታ በማመቻቸትና ሪፖርቱም ሲወጣም በሪፖርቱ የተሰጡ ምክረ-ሃሳቦችን ለመተግበር የሚኒስቴሮች ጥምር ግብረ-ኃይል በማቋቋም መጠነሰፊ የሆኑ ተጎጂዎችን መልሶ የማቋቋም፣ ተፈጸሙ የተባሉ የመብቶች ጥሰቶች ምርመራ እና የሕግ ማሻሻያ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል።

ከዚህ በተጨማሪም በሰሜኑ ሀገራችን ክፍል የነበረውን ግጭት ለማቆም በፕሪቶሪያ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ለማስፈጸም ብሎም በሀገራችን የሚታዩ አለመግባበቶችን በዘላቂነት ለመፍታት የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ አማራጮችን በማዘጋጀት በሀገር አቀፍ ደረጃ በርካታ ውይይት እየተደረጉ ይገኛሉ።

የቀረቡ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ አማራጮች ላይ ከመንግስታዊ ተቋማት፣ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች እና ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ አባላት ጋር ሰፊ ምክክሮችና የግብአት ማሰባሰቢያ ስራዎች ተሰርተዋል፤ እየተሰሩም ይገኛሉ፡፡ የሽግግር ፍትህ ሂደቱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የፈጸሙ ወገኖች ላይ ተገቢው ማጣራትን በማድረግ ተጠያቂነትን ማስፈንን ጨምሮ እውነትን የማፈላለግ እና ተጎጂዎችንም መልሶ ለማቋቋም የሚያስችል ማእቀፍ ይፈጥራል። በተጓዳኝ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በሀገራችን የሚታዩ ግጭት እና አለመግባባቶችን ከስር መሰረታቸው በመለየት በዘላቂነት ለመፍታት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

በሀገራችን ያሉ ችግሮችን ከመሰረቱ ለመቅረፍ በራስ አቅም እየተሰሩ ካሉ ስራዎች በተጨማሪ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እና የተ.መ.ድ. የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት ጥምር የክትትል ቡድን ተደራጅቶ ግጭቱ በነበረባቸው አካባቢዎች ያለውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል እንዲያደርጉ በመጋበዝ መንግስት በሀላፊነት መንፈስ እየሰራ ባለበት ወቅት ይህንን ከግንዛቤ ሳያስገባ እና በቂ ማስረጃ በሌለበት ከላይ በተጠቀሰው ድርጅት የወጣው ሪፖርት ገንቢ ያልሆነና ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ነው።

ግንቦት 29 ቀን 2015 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Left Column, Politics Tagged With: ethiopian terrorists, meles bisrat, operation dismantle tplf, tplf terrorist, wolkayit

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule