• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ህወሓት፤ “ቆሞ ቀር” ብቻ ሳይሆን “ቆሞ ሙት”

June 7, 2018 11:01 am by Editor 3 Comments

እንደ ህወሓት ያለ አስገራሚ የፖለቲካ ቡድን ያለ አይመስለኝም። በጣም ገራሚ ነው። ከአመታት በፊት ያስቀመጥከው ቦታ ቁጭ ብሎ ይጠብቅሃል። በራሱ ምንም ዓይነት ለውጥ እንዲመጣ አይሻም። ከራሱ ባለፈ በሌሎች ዘንድ ምንም ዓይነት ለውጥና መሻሻል እንዲኖር አይፈቅድም። ከሁለት አመት በፊት ህወሓት “ቆሞ-ቀር” እንደሆነ የሚገልፅ ፅሁፍ አውጥቼ ነበር። ዛሬም ቢሆን ከነበረበት ቦታ ንቅንቅ አላለም። ህወሓት ፀረ-ለውጥ ድርጅት ከመሆኑ በተጨማሪ ሥር የሰደደ የአመራር ችግር አለበት። በመሆኑም ህወሓት ራሱን ለለውጥ ማንቀሳቀስ ሆነ መምራት አይችልም።

በተለይ የመለስ ዜናዊ ህልፈትን ተከትሎ ህወሓት “በቁሙ መሞት” ጀምሯል። ከመለስ ዜናዊ ቀጥሎ የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት አባይ ወልዱ ናቸው። ሰውዬው እንደ መለስ ዜናዊ ሸርና አሻጥር መጎንጎን አልቻሉበትም። በመሆኑም የመለስ ዜናዊ የነፍስ አባት የሆኑት አባይ ፀሓዬ ወደፊት መጡ። ምን ያደርጋል ታዲያ አባይ ከኋላ ሆኖ ነገር መጎንጎን እንጂ ፊት-ለፊት መናገር አይችሉም። የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም በኦሮሚያ የተነሳውን አመፅና ተቃውሞ በመቀስቀስና በማቀጣጠል ረገድ ከጃዋር መሃመድ ያልተናነሰ አስተዋፅዖ አበርክተዋል። እሳቸውን ወደኋላ ጎተት አድርጎ ጌታቸው ረዳ ወደፊት ብቅ አለ። “እሳትና ጭድ” ቅብርጥስ ብሎ አባይ ፀሓዬ ባቀጣጠሉት እሳት ላይ ቤንዚን ጨመረ። በኦሮሚያና አማራ ክልል የተጀመረው ሕዝባዊ ተቃውሞ ይበልጥ ተቀጣጠለ፣ እስር-በእርስ መጣመርና መተባበር ጀመረ።

ከዚያ በመቀጠል ለ35 ቀናት መቐለ ላይ ያደረጉት ስብሰባ “የመለስ ዜናዊ ራዕይ ውጣ! የስብሃት ዘመድ ግባ!” በሚል ተጠናቀቀ። ባሉበት ለመቆም ያላቸውን ምኞት ዕውን ለማድረግ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅን ዳግም ለማወጅ ስልት ነደፉ። በስብሰባው መሃል ስብሃት ነጋ የወታደር ሽማግሌዎች አስከትለው ወደ ጎንደር ከሄዱ በኋላ “የኦሮማራ ጥምረት ዓላማው ምንድነው?” በሚል አምባጓሮ አስነሱ። በመጨረሻም ከብአዴኖች ጋር “አንቺ-አንተ” ተባብለው ተሰዳደቡ። በዚህም ለእርቅ ሄደው ፀብ ሸምተው ገቡ።

በተቃራኒው በባህር ዳር የተጀመረው የኦሮማራ ጥምረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ስብሃት የድርሻቸውን ተወጡ። ከእሳቸው ቀጥሎ ደግሞ ዘርዓይ አሰግዶም መጡ። በኦሮሚያና አማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ባለው አመፅና ተቃውሞ፣ እንዲሁም በብዓዴንና ኦህዴድ መካከል የተፈጠረው ጥምረት በህወሓቶች ስነ-ልቦና ላይ ያሳደረውን ተፅዕኖ እንደ ዘርዓይ አሰግዶም አሳምሮ ያወጣ ሰው ከቶ ከወደየት ይገኛል? ድሮ አባይ ወልዱ እያለ ህወሓት ራሱን ከውድቀት የመታደግ ዕድል ነበረው። ሌላው ቢቀር የንቅናቄው ፊትአውራሪ ከሆኑት ኦቦ ለማ መገርሳ ጋር ስልክ ደውሎ ማናገር ይችል ነበር። ከዚያ በተረፈ ያሉት የህወሓት ባለስልጣናትና ጄኔራሎች ፊትአውራሪውን በስልክ የማናገር ዕድል ተነፍጓቸው ነበር።

አሁን ላይ የድርጅቱ ሊቀመንበር የሆኑት ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል ጠንካራ የፖለቲካ ክርክር ማድረግ ቀርቶ ሃሳባቸውን እንኳን በግልፅ ማስረዳት አይችሉም። ለምሳሌ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ምርጫን አስመልክቶ ከፋና ቴሌቪዥን ጋር ያደርጉትን ቃለ ምልልስ ተመልከቱ። በዚህ ቃለ ምልልስ ደብረፂዮን “ለሊቀመንበርነት ሦስት ተወዳዳሪዎች እንደነበሩና እሳቸውም ከእነዚህ ውስጥ አንዱ መሆናቸውን በመጥቀስ ምርጫው በጣም ዴሞክራሲያዊ እንደነበር ይገልፃሉ። እኔ ግን “እንዳትመርጡኝ ብዬ ስቀሰቅስ ነበር” ብለዋል። በመጨረሻም መራጮቹ ያልኩትን ሰምተው ስላልመረጡኝ አመሰግናለሁ” ብለዋል። እንዲህ ያለ የምርጫ ቅስቀሳ በዓለም ታይቶም-ተሰምቶም የሚያውቅ አይመስለኝም። ያም ሆነ ይህ ነገሩ የሚያሳየው በህወሓት ውስጥ ያለው የአመራር አቅም ማነስ ነው።

ከላይ የተጠቀሱት መሪዎች በሙሉ አንድ ነገር በተናገሩ ቁጥር የህወሓትን መቃብር የሚቆፍሩ ናቸው። በዚህ በመማረር የህወሓት መስራችና በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት ስዩም መስፍን በተራቸው ወደፊት መጡ። ግንቦት 20ን አስመልክቶ በመቐለ ከተማ በተካሄደው የውይይት መድረክ ስዩም በወቅታዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በዚህ መድረክ “ፖለቲካዊ ስርዓቱ ያጋጠመው መሰረታዊ ችግር በአብዮታዊ ዴሞክራሲ እና በኪራይ ሰብሳቢነት መካከል የተፈጠረ ግጭት” መሆኑን ገልፀዋል።

እንደሚታወቀው የአብዮታዊ ዴሞክራሲ አጀንዳ ዋና አራማጆች ህወሓቶች ናቸው፣ በሀገሪቱ ለተንሰራፋው ኪራይ ሰብሳቢነት ግንባር ቀደም ተጠያቂዎቹ ራሳቸው ህወሓቶች ናቸው። ምክንያቱም ሀገሪቱን ለቀውስ የዳረጋት የህወሓትን የበላይነት በማረጋገጥ ላይ የተመሰረተው የጠነዛ ፖለቲካዊ አቋምና አመለካከት ነው። ሆኖም ግን፣ ስዩም መቐለ ድረስ ሄደው የተናገሩት ነገር ሌላ ነው። ስዩም በህወሓት የበላይነትና የጠነዛ የፖለቲካ አመለካከት ምክንያት የተፈጠረውን ችግር በብዓዴንና ኦህዴድ ላይ ለማላከክ ጥረት ሲያድጉ ተስተውለዋል። ውይይቱ በአማርኛ የተደረገበት ምክንያት ደግሞ ከትግራይ ውጪ ላለው ማህብረሰብ “አለን፥ አልሞትንም” ለማለት ነው።

የፖለቲካ ቡድን ሕልውና የሚረጋገጠው ከወቅቱና ከሕዝቡ ፍላጎት ጋር አብሮ መለወጥና መሻሻል ሲችል ነው። ለአራት ዓሥርተ ዓመታት አንድ ዓይነት የፖለቲካ አቋምና አመለካከት እያመነዠከ፣ ለለውጥና መሻሻል እንቅፋት የሆነ የፖለቲካ ቡድን “ቆሞ ቀር” ብቻ ሳይሆን “በቁሙ መሞት” የጀመረ ነው። ስለዚህ በዚህ አቋሙ ህወሓት ከሞት ወይም ውድቀት አፋፍ ላይ መሆኑ እርግጥ ነው።

(በዚህ ጽሁፍ ውስጥ አንዳንድ አባባሎችና ርዕሱ በጎልጉል ተለውጧል)

ምንጭ፤ Ethiopian Think Thank Group by Seyoum Teshome

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions, Politics Tagged With: abay, debretsion, Full Width Top, getachew, meles, Middle Column, seyoum, sibhat, tplf, zeray

Reader Interactions

Comments

  1. ስዩም says

    June 7, 2018 10:55 pm at 10:55 pm

    እውነት

    Reply
  2. Ayalew Shebeshi says

    June 8, 2018 07:26 am at 7:26 am

    Thank you so much GOLGULE.
    Let all (US-Ethiopians) stop blaming the past and do FORGIVE and FORGET approach to make peaceful transition from current Ethiopian Administration system to new, equal, modernized and based or supported by Skilled knowledgable HR + Info/data + HighTech that specially create job for our young Ethiopian to have them at least bread. I am sure if we concentrate or focus on peaceful transition, bloodless power transfer from EPRDF to Ethiopian people then we will achieve and bring fast radical changes to both political and economical situations that will serves free and fair go to all Ethiopians. Let us do it our brothers & sisters

    Reply
  3. Ayalew Shebeshi says

    June 19, 2018 05:15 am at 5:15 am

    So sad gave land and water for nothing.
    Now Eritrea must pay compensation not only to all 70,000 people who died and displaced during Badmie conflicts but also both for over 30 years war victims those who lost their loved once and the looting of wealth from Ethiopians from both ports Asab and Metsewa after 1990.
    The Best option for Eritrea is give Asab and Metsewa ports to use Ethiopia for free or small payment.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule