• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ

April 7, 2025 10:22 pm by Editor Leave a Comment

ትላንት የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የቀድሞ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ “UMD” ለተባለ ሚድያ ዘለግ ያለ ቃለመጠይቅ ሰጥተዋል።

በርካታ ጉዳዮች ባነሱበት ቃለ-መጠይቃቸው “አሁንም ትግራይ መላ ቅጡ በማይታወቅ ሁኔታ ላይ ናት ፤ በርካታ የትግራይ ህዝብ በከፍተኛ ጭንቅና መከራ ውስጥ ይገኛል” ብለዋል።

ጥያቄ – በሁለት አመቱ የፕሬዚዳንትነት ቆይታህ ያልጠበቅከውና በጣም መጥፎ ነበር ብለህ የምትገልፀው አጋጣሚ አለ?

የጌታቸው ምላሽ – አዎ በጣም ያልጠበቅኩትና መጥፎ ነበር የምለው አለኝ። እኔን እስከማስወገድ ድረስ ፍላጎት እንደነበራቸው አላውቅም ነበር። መጨረሻ ላይ ግን ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ወደ ኤርፖርት ሳመራ እኔን አግቶ ለማስቀረት ሙከራ አደረጉ። ለማገት መሞከራቸው አይደለም እኔን ያበሳጨኝ። እኔ የተበሳጨሁት ሊገድሉኝ አቅደው እንደነበር ያወቅኩኝ ጊዜ ላይ ነው። ኋላ ላይ በደረሰኝ መረጃ መሠረት ሁለት የማከብራቸው ወታደራዊ አዛዦች “እንዴት አመለጠን ቀድመን ነበር እኮ ማስወገድ የነበረብን” ብለው በቁጭት እንዳወሩ አወቅኩኝ። ለነገሩ የሚታወቅ ባህሪ ነው። ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም።

ኬላ ጥሎ እኔን ለማገት ተልዕኮ ተሰጥቶት የነበረው አወጣኸኝ የተባለ የኮር አዛዥ ነው። እንደውም ኋላ ላይ ተልዕኮውን ባለመፈፀሙ አስረውታል። እኔን ለመግደል ዝርዝር ፕላን ያወጡትን ሰዎችን ሳይቀር አውቃቸዋለሁ። (ከአስፋው አብርሃ ቴሌግራም ገጽ የተወሰደ)

“በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ጊዚያዊ አስተዳደሩ ሲመሰረት የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ጦርነቱ በመምራት ከፍተኛ ሚና የነበረን 5 ስራ አስፈፃሚዎች ወደ ፕሬዜዳንት የኋላፊነት ቦታ እንዳንመጣ ፍላጎት ነበረቸው” በማለት ወደ ኋላ ተመልሰው አስታውሰዋል።

ይህን ሃሳብ እሳቸው ቢቀበሉትም የተቀሩት አራቱ ስራ አስፈፃሚዎች የጠቅላይ ሚንስትሩን ሃሳብ ውድቅ ማድረጋቸው ተናግረዋል።

“ጊዚያዊ አስተዳደሩ ለማቋቋም በአላስፈላጊ ክርክር አራት ወራት ፈጅተናል፤ በብዙ ውጣ ውረድ መጋቢት 21/2015 ዓ.ም ተቋቁሞ ፕሬዜዳንት ሆኜ መምራት ስጀምር በቀናት ውስጥ ‘ባንዳ’ የሚል ስያሜ ተለጠፈብኝ ” ሲሉ ተደምጠዋል።

አቶ ጌታቸው “በዚያው ዓመት ወርሃ ግንቦት የባሰውኑ ‘ከሃዲ’ ተባልኩኝ” በማለት ተናግረዋል።

“አራቱ የህወሓት ስራ አስፈፃሚዎች በየሦስት ወሩ ለማድረግ የሚፈቅደውን የድርጅቱ ውስጠ ደንብ በመጣስ በየሦስት ቀኑ ፍሬ በሌለው ስብሰባ በመጥመድ ከመንግስታዊ ስራ ውጭ እንድሆን አበክረው ሰርተዋል፤ በዚሁ ተማርሬ ኃላፊነቴ በራሴ ፍቃድ መልቀቅ ባለመቻሌ ተናደው እኔን ጨምሮ 16 የድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴ አባላትን ‘ከሃዲዎች ከጂዎች’ ብለው በመፈረጅ አላሰራ አሉን” ብለዋል።

“የተቀረው የህወሓት የስራ አስፈፃሚ በፕሪቶሪያው የተኩስ ማቆም ስምምነት እንደ ሽንፈት የሚቆጥር፣ በተፈናቃዮች እጣ ፈንታ የሚቆምር፣ ጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሰጡት ተልእኮዎች እንዳይፈፅም ከላይ እስከ ታች በእቅድ የሰራ አደናቃፊ” ብለውታል አቶ ጌታቸው።

አቶ ጌታቸው “ለውጥ የማይቀበሉ ፤ የተቸከሉ” ሲሉ የገለፁዋቸው የህወሓት 4ቱ ስራ አስፈፃሚዎች እሳቸው ወደ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት በመጡበት ማግስት የሚሰራ በሌለበት 55 የድርጅቱ ሰዎች በምክትል የስራ ኃላፊ ደረጃ እንዲሾሙ ፕሮፓዛል እንዳቀረቡላቸው፤ ይህንን ያህል ቁጥር ያለው ስራ ሳይሰራ ደመወዝ የሚከፈለው አመራር ለመመደብ ቢቸገሩም ከክርክር በኋላ 35 በግድ መመደባቸው ገልጸዋል።

ድርጅታዊ ውስጥ ደንብ በመጣስ የ65 እና የ70 ዓመት ዕድሜ ያላቸው የማእከላይ ኮሚቴ አመራር እንዲሆኑ መመረጣቸው በርካታ ቁጥር ያለው አመራር ከሃላፊነት ምድብ ውጭ ሆኖም ቁጭ ብሎ በፊት የነበረው ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም እንዲያገኝ የሚያደርግ እጅግ ዘግናኝ አሰራር ክልሉን ጠልፎ መጣሉ አቶ ጌታቸው ገልፀዋል።

“ጡረታ የማይፈቀድበት ክልል ቢኖር ትግራይ ነው”  ያሉት አቶ ጌታቸው፤ ከጦርነቱ በፊት በ2012 ዓ.ም 800 ሚሊዮን ብር የነበረው የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ተቋቁሞ ስራው በ2015 ዓ.ም ሲጀምር ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ ማሻቀቡ በክልሉ ያለው ቅጥ ያጣ በልሹ አሰራር የሚያሳይ ነው ብለዋል።

“በትግራይ ያለው አሁናዊ ፓለቲካዊ ቀውስና ችግር ህወሓት ብቻውን ስልጣን እንዲቆጣጠር ያለው ያልተገራ ፍላጎት የፈጠረው ነው” ያሉት አቶ ጌታቸው “ይህንን ሁሉንም ነገር በብቸኝነት የመያዝ ያልተገራ የህወሓት ፍላጎት የማይሸከም በተግባር የተደገፈ ለውጥ በትግራይ መፈጠሩ ማሳያዎችን በመጥቀስ አስረድተዋል።

ከትናንት ወዲህ መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከዱባይ ‘bird story agency’ ለተባለ ሚድያ በሰጡት ቃለመጠይቅ “በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ እመለሳሎህ ማለታቸው” ተከትሎ እሁድ ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸው በአንዳንድ የማህበራዊ የትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች ቢፃፍም ፤ ፕሬዜዳንቱ ለUMD ሚድያ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ ስለዚሁ ጉዳይ ያሉት የለም።

NB. አቶ ጌታቸው ረዳ አራቱ ስራ አስፈጻሚዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሃሳብ ውድቅ እንዳደረጉ በገለጹበት አውድ ስም ባይጠቅሱም በይፋ የሚታወቁት ስራ አስፈጻሚዎች ፦

1. ደብረፅዮን (ዶ/ር)

2. ወ/ሮ ፈትለወርቅ

3. አቶ ኣለም ገብረዋህድ

4. አቶ ጌታቸው ኣሰፋ ናቸው። (ቲክቫህ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: News, Politics, Right Column Tagged With: debretsion, getachew assefa, getachew reda, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule