• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የትግራይ አበጋዞች ሽኩቻ

September 25, 2024 01:19 pm by Editor 1 Comment

ከበረሃ ውንብድና አገረ መንግሥትን ወደመምራት ሳያስበው የተቀበለው ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር በማለት በነጻ አውጪ ስም አንዲት ሉዓላዊት አገር ጠርንፎ በአናሳዎች በግፍ ሲገዛ የነበረው የወንበዴዎች ቡድን ጎራ ለይቶ በአደባባይ መካሰስ ከጀመረና ውዝግቡም እየተካረረ መጥቶ ትግራይን እንደ አፍጋኒስታን ወይም ኢራቅ በጦር አበጋዞች ከፋፍሎ ወደለየለት ደረጃ እየወሰዳት መሆኑ በቅርቡ የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

የቡድኑ መሪ የሆነው ደብረጽዮን እነ ጌታቸው የሚከሱኝ በፊትም ጦርነት ውስጥ ያስገባንና ሚሊዮኖችን ያስጨፈጨፈው ትህነግ ነው፤ አሁንም መልሶ ጦርነት ውስጥ ሊከተን ነው፤ ጦርነት ናፋቂ ነው እያሉ ነው፤ ነገር ግን ተጨፈጨፈ የተባለው ሕዝብ ማስረጃ የታለ? ባለተጨበጠና ባልተረጋገጠ፤ ማስረጃ በሌለው እኔን መክሰስ ብቻ ስለፈለጉ ባልሞተ ሕዝብ ይከስሱኛል በማለት በየዓለምአቀፍ መድረክ ሁሉ ጄኖሳይድ እያሉ ሲያወሩ የነበሩት ነገር የውሸት ፈጠራ በሬ ወለደ ወሬ መሆኑን አረጋግጧል።

የሰሞኑ ውዝግብ ተዋናዮች ደብረጽዮን፣ ጻድቃን እና ጌታቸው ናቸው። ደብረጽዮን ፃድቃን ቂመኛ ነው፣ ቂሙን ነው እየተወጣ ያለው በማለት በአደባባይ ከስሶታል። ጻድቃን በበኩሉ “እኔ ከማንም ጋር ቂም የለኝም፣ ቂም ይዟል የሚል ካለ ይምጣ” ብሏል። ከጻድቃን ጋር ጌታቸውንም የከሰሰው ደብረጽዮን ”ጌታቸው ውሸታም ነው፤ ውሸት መናገሩን ካላቆመ” ምሥጢሩን ሁሉ እዘረግፈዋለሁ በማለት ዝቷል። ሰሞኑን ወንበዴዎቹ በመካከላቸው የተፈጠረውን አስመልክቶ ሪፖርተር ያጠናቀረውን ከዚህ በታች አስፍረነዋል። 

የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል በትግራይ ጦርነት ወቅት የተፈጠሩ ልዩነቶችን በማስታወስ፣ በአሁኑ ጊዜ ከእሳቸው ተቃራኒ የቆሙ የሕወሓትና የትግራይ ጦር ከፍተኛ አመራሮችን በአደባባይ መውቀስ ጀመሩ።

ከሕወሓት ጠቅላላ ጉባዔ በፊት ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት አስከትሎ በስተመጨረሻ በፕሪቶሪያው ስምምነት የተገታው የትግራይ ጦርነት እንዲገመገም የቀረበውን ጥያቄ ደብረ ጽዮን ውድቅ በማድረግ፣ ጠቅላላ ጉባዔ በማካሄዳቸው ከእሳቸው ተቃራኒ በቆሙ የሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች ሲተቹ እንደነበር ይታወሳል።

ደብረ ጽዮን የሕወሓት ጠቅላላ ጉባዔ አካሂደው የፓርቲውን የሊቀመንበርነት ሥልጣኑን እንደገና ከተቆጣጠሩ በኋላ፣ ከእሳቸው በተቃራኒ የቆሙ የሕወሓትና የትግራይ ጦር ከፍተኛ አመራሮችን “ሥልጣን ለመቆጣጠር ሲያሴሩ ነበር፤” በማለት ሰሞኑን በአደባባይ ሲተቹ ተደምጠዋል።

ሕወሓት የትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁነቶችን አስመልክቶ በተለያዩ የክልሉ ከተሞች ሕዝባዊ ውይይቶችን ከሐሙስ መስከረም 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ እያካሄደ ነው፡፡ ከእነዚህም መካከል አንዱ በሊቀመንበሩ ደብረ ጽዮን ሰብሳቢነት ባለፈው ቅዳሜ በመቀሌ ከተማ የተካሄደው ሕዝባዊ ውይይት ይገኝበታል።

በመቀሌው ውይይት በትግራይ ያለውን ፖለቲካዊ ክፍፍል አስመልክቶ ከሕዝብ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን፣ በሕወሓት ውስጥ የፖለቲካ ልዩነት መፈጠር የተለመደ መሆኑን፣ ለአብነትም ሕወሓትን ከመሠረቱት ሰዎች መካከል አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) ድርጅቱ መጠናከር በጀመረበት የትጥቅ ትግል ወቅት በነበራቸው ልዩነት መሰናበታቸውን አስታውሰዋል። 

ነገር ግን “ህንፍሽፍሽ” ተብሎ የሚጠራው የ1993 ዓ.ም. የሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች ፖለቲካዊ ክፍፍልን ተከትሎ ቂም የቋጠሩ አካላት አሁን ድርጅቱን ለማፍረስ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን፣ ከእነዚህም መካከል ዋነኛው ፃድቃን ገብረ ትንሳይ እንደሆኑ በይፋ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅቱ በሕወሓት ውስጥ ሥር የሰደደው የሥልጣን ሽኩቻ መታየት የጀመረው በሁለት ዓመቱ የትግራይ ጦርነት ወቅት መሆኑን የጠቆሙት ደብረ ጽዮን፣ “ፃድቃን ተከዜ አካባቢ ውጊያ ላይ በነበርንበት ወቅት ደብረ ጽዮን በሱዳን በኩል ከአገር መውጣት አለበት እስከ ማለት ደርሶ ነበር፤” ሲሉ በመቀሌው ሕዝባዊ ውይይት በይፋ ተናግረዋል፡፡ 

በጦርነቱ ወቅት ሥልጣንን ለመቆናጠጥ ሲባል ዘርፈ ብዙ ችግሮች ተፈጥረው እንደነበር ያወሱት ደብረ ጽዮን፣ “ከጦርነቱ ማን በሕይወት ተርፎ ይመለሳል የሚለው እንኳን ባልታወቀበት ሁኔታ ማስተካከያ እናድርግ የሚል ውትወታ ነበር፤” ብለዋል፡፡ 

ጦርነቱ ሲያበቃ እንዲባረሩ ተወስኖባቸው ከነበሩ ሰዎች መካከል አንዱ ፃድቃን መሆናቸውንም አስረድተዋል።

“በክልሉ አንፃራዊ ሰላም መታየት ከጀመረ በኋላ ፃድቃንን በተመለከተ ተወያይተን በጦርነቱ ወቅት ውድ ሕይወቱን ስለሰጠ፣ በአንድ ድክመት ምክንያት ልናባርረው አይገባም ብለን ከአምስት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ውስጥ ሦስታችን ብቻ ይቆይ፣ የሆነ ኃላፊነት ሊሰጠው ይገባል ብለን ወሰንን፡፡ ሌሎቹ ይውጣ፣ ይባረር ብለው ነበር፡፡ ሕይወቱን አሳልፎ ስለሰጠ ጥፋቱ ይሻርለት ብለን ነው ያቆየነው እኛ ነን፤” ብለዋል፡፡ 

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የተቋቋመው ከሕወሓት፣ ከምሁራን፣ ከፀጥታ አካላትና ከተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮችን አካቶ መሆኑን ያስታወሱት ደብረ ጽዮን፣ ፃድቃን በጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ አባል የሆኑት በትግራይ ምሁራን ተወክለው እንደሆነ ገልጸዋል። 

“እኛም አጉል ከሚሆን ኃላፊነት ይኑረው አልን፣ ነገር ግን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕሬዚዳንት ኃላፊነት እንዲሰጠው አልነበረም ያሰብነው፤” ያሉት ደብረ ጽዮን፣ “እንዳላችሁት ፃድቃን ቂመኛ ነው፣ ቂሙን ነው እየተወጣ ያለው፡፡ ግን ደግሞ ቂሙን ከፈለገ እኔ ደብረ ጽዮን ላይ እንጂ የትግራይ ሕዝብ ላይ እንዲወጣ አልፈቅድም፤” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ 

ጦርነቱ እየተካሄደ በተለይም የትግራይ ኃይል ወደ ሰሜን ሸዋ አካባቢ ተቃርቦ በነበረበት ወቅት ከፌዴራል መንግሥት ጋር ተደራድሮ ሰላም የማውረድ ሐሳብ ተነስቶ እንደነበር አስታውሰው በወቅቱ፣ “ከማን ጋር ልንደራደር ነው? ያለቀ ጉዳይ ነው ሲሉ የነበሩ እንደ ፃድቃን ያሉ ሰዎች፣ ዛሬ ተገልብጠው ሕወሓት ጦረኛ፣ እነሱ ደግሞ ሰላም ፈላጊ እንደሆኑ ያስመስላሉ፤” ብለዋል።

ደብረ ጽዮን ይህንን ከመናገራቸው ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ለትግራይ ሚዲያዎች ቃለ መጠይቅ ሰጥተው የነበሩት ፃድቃን ገብረ ትንሳዔ፣ በሕወሓት አመራር ላይ ያልሻረ ቂም እንዳላቸው ተደርገው እንደሚታዩና እንደሚታሙ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።

እሳቸው በሰጡት ምላሽም፣ “እኔ ከማንም ጋር ቂም የለኝም፣ ቂም ይዟል የሚል ካለ ይምጣ፤” ብለው ነበር።

የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን በመቀሌ በነበራቸው ሕዝባዊ የውይይት መድረክ ላይ፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ኃላፊ ጌታቸው ረዳንም ወርፈዋል።

“ጌታቸው ራሱ ከኤርትራ ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝቶ በየሚድያው እየዞረ ሕወሓት ከኤርትራ ጋር እየሠራ ነው ይላል፤” በማለት የተቹት ደብረ ጽዮን፣ “ጌታቸው ሕወሓት ክዶኛልና የፌዴራል መንግሥትን አግዘኝ እያለ ነው፡፡ ሁሉንም ተናግሬ መዘርገፍ ፈልጌ አይደለም፣ ግን ጌታቸው ውሸት መናገሩን ካላቆመ፣ እኔም እውነታውን መናገሬን እቀጥላለሁ፣ እንዲያውም እጨምርለታለሁ” ሲሉም ተደምጠዋል።

“ሁሉንም ነገር ተናግሮ መዘርገፍ ተገቢ ነው ብዬ ባላምንም፣ ብዙ ነገር አውቃለሁና ከዚህ በኋላ መነገር ያለበትን ለሕዝብ ከመናገር ወደኋላ አልልም፣ አቶ ጌታቸው በየሚዲያው እየዞረ ብዙ እያለ ነው፣ ነገሮችን ገልብጦ መናገሩን ከቀጠለ እኔም እውነቱን እናገራለሁ፤” ብለዋል፡፡

የፕሪቶሪያውን ስምምነት በሚመለከት ማብራሪያ የሰጡት ደብረ ጽዮን፣ ስምምነቱን ለመፈጸም የተወከለው ልዑክ ተኩስ የማስቆም ኃላፊነት ብቻ ተሰጥቶት ሳለ ስለጊዜያዊ አስተዳደር ምሥረታ ተነጋግሮና ፈርሞ መመለሱን ተናግረዋል፡፡ 

ይህንን በተመለከተም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የማቋቋም ሐሳብ በፌዴራል መንግሥት በኩል እንዳልነበር፣ ሐሳቡ የተነሳው ከትግራይ ተደራዳሪዎች መሆኑን እንደተናገሩ ደብረ ጽዮን ለውይይቱ ተሳታፊዎች አስረድተዋል፡፡ 

“በዚህ ደረጃ ኃላፊነት ማን ሰጣችሁ ሲባሉ ተኩስ ለማስቆም ኃላፊነት ሰጥታችሁናል ብለው ነው የሞገቱን፣ ብዙ ጥፋት እያጠፉ ነው፡፡ ይህ አደገኛ አካሄድ ነው፤” ብለዋል።

ፃድቃን ከሰሞኑ በሰጡት ቃለ መጠይቅ የፕሪቶሪያው ስምምነት የሕወሓትና የፌደራሉ መንግሥት ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ መሆኑን፣ አደራዳሪዎቹም በአንክሮ የሚመለከቱት ጉዳይ እንደሆነ ተናግረዋል። አፈጻጸሙንም የአውሮፓ ኅብረት፣ የአፍሪካ ኅብረትና ሌሎችም አጋር አካላት እየተከታተሉት እንደሆነ፣ ይህም የውሉ አቅጣጫ በአንድ ወገን እንዲቀየር ተደርጓል የሚለውን ክስ ውድቅ የሚያደርግ እንደሆነ በመጠቆም ከሕወሓት በኩል የሚነሳውን ወቀሳ አጣጥለውታል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, News, Politics Tagged With: debretsion, ethiopian terrorists, getachew reda, operation dismantle tplf, tplf, tplf terrorist, tsadkan gebretinsae

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    October 11, 2024 05:48 pm at 5:48 pm

    ያኔም አሁንም ወደፊትም የሃበሻ ፓለቲካ የመበላላት ፓለቲካ ነው። ከዚህ የተኩላ ክምችት ተርፈው በየስርቻው ተወሽቀው ያሉት እጃቸው በሰው ደም የተነከረ፤ ጭንቅላታቸው የተዛባ፤ በቅሚያና ስርቆት ራሳቸውንና ከሥራቸው ፍርፋሬ ለቃሚዎችና ዘመድ አዝማዳቸውን ጠቅመው እኛ የታገልነው ለህዝብ ነው እያሉ እድሜ ልካቸውን ከበሮና ክራር እየመቱ ዳንኪራ የሚመቱና የሚያስመቱ የቁም ሙቶች ናቸው። ግን ሃገርና ህዝብ ከብሄር ሰካራም ፓለቲከኞች ያተረፈው ሞትና መከራን ብቻ ነው። ለዚህ ዋንኛ ማሳያው ወያኔና ሻቢያ ናቸው። የእነርሱን ፈለግ ተከትለው ያኔም አሁንም ነፍጥ አንግበው ኑና ግጠሙን የሚሉ ሁሉ የህሊና በሽተኞች ናቸው። አሁን ላይ በኦሮሚያና በአማራ ክልል ያለው መሻኮት የዚህ ህልፈት የለሽ የጠባብ ብሄርተኞች የወለደው የመከራ ዶፍ እንደሆነ የገባው ብቻ ይገባዋል።
    ወያኔ በጫካም እርስ በእርስ ተባልቷል አሁንም በመባላት ላይ ይገኛል። ወያኔ ያለ ባሩድ ሽታ መኖር አይችልም። ጦርነትን መዋጋት ብቻ ሳይሆን ፈጣሪም ናቸውና! አሁን ጠ/ሚ አብይን ደጅ የሚጠናው ደብረጽዪን የክፋቱ ሁሉ ቁንጮና በተናገረው ውሎ የማያድር አታላይና ወላዋይ ሰው ለመሆኑ ያለፈ ታሪኩን ከቅርብ ጊዜ አሰልቺ ዲስኩሩ ጋር በማገናዘብ መመዘን ይቻላል። ትግራይ ላይ አዲስ ጦር እያሰለጠነ ያለው ወያኔ የአውሮፓ መንግስታት በተለይም የእንግሊዝ መንግስት ሰራዊቱ ተበትኖ ሰርቶ ጥሮ እንዲበላ በፕሪቶሪያው ውል መሰረት በዚህም በዚያም ገንዘብ በመለገስ ላይ ይገኛሉ። ወያኔ ያለ ሰራዊት አይኖርም። ገንዘቡን ይበላሉ እንጂ የሚበተንም ሰራዊት አይኖርም። የሚገርመው የብልጽግናው መንግስት ዝምታ ነው። ወያኔ ወታደር እያሰለጠነና፤ ኑ ግጠሙን አካኪ ዘራፍ እያሉ እንዴት ባለ ሂሳብ ነው የትግራይ ታጣቂ ፈርሶ በሰላም የሚኖረው? ጀላንፎ ፓለቲካ። ተጨፈኑና ላሞኛችሁ አይነት ፓለቲካ። መንቻኮች!
    ሶስት ጊዜ ከብልጽግና ጋር ተላትሞ የአማራና የአፋርን ህዝብ መከራ ውስጥ የከተተው ወያኔ ያን ሁሉ የትግራይ ወጣት አስፈጅቶ እንደገና አሁን መቀሌ ላይ ታዳጊ ወጣቶችን ሰብስቦ ውትድርና ሲያሰለጥን ማየት ወቸው ጉድ የእነዚህ ሰዎች እብደት ማብቂያ የለም ያሰኛል። መፈክራቸው ራሱ አስደንጋጭ ነው። ” ታንክ በድንጋይ የማረከ” ግን አብደው ለማሳበድ የሚያድርጉት በመሆኑ ፉከራውንና የፓለቲካ ቱልቱላዎችን ከእውነት ጋር ለማስታረቅ አይቻልም።
    ሃገሪቱ በሞቱትና በቋሚዎች የተረገመች ሃገር ናት። አይ አይደለችም የሚል የመቶ ዓመት ታሪኳን ወደኋላ ዞር ብሎ ይመልከት። መግደል፤ መገዳደል፤ማሰርና ማሰቃየት፤ በዘርና በቋንቋ ሃገርን ሽንሽኖ አፓርታይድ አገዛዝ መመስረት ከሰቆቃዎቹ ጥቂቶች ናቸው። ኸረ ምድሪቱ ለም ናት፤ ህዝቡ ደግና የዋህ ነው ይሉናል የደላቸው። እነዚህ ድርቡሾች ከህዝቡ መካከል አይደለም እንዴ የወጡት? መሬቱስ ቢሆን ድርቅና ጠኔ እንጂ ልማቱ የቱ ላይ ነው? አዎን ለመሬቱ መጎሳቆል የእኛም ድርሻ አለ። መቁረጥ እንጂ መትከል አናውቅ። በሚተክሉት ላይ የምናፈዝ፤ መሸታ ቤት ተቀምጦ በሥራ የተጠመደውንና አርቆ የሚያስበውን የሚዘልፍ። እኔን ሁልጊዜ የሚገርመኝ መቼ ነው ህዝባችን እፎይ ብሎ የሚኖረው? መቼ ነው ጦርነትና ረሃብ ከምድሪቱ የሚጠፋው? ያ ጊዜ ይመጣ ይሆን? አይመስለኝም።
    ከዘመን ዘመን ስንፋለም የያኔውን የንጉሱ ወታደር፤ የደርግ ወታደር፤ የወያኔ ወታደር፤ የብልጽግና ወታደር እያልን ለሃገር ለወገን የሚዋደቁ ወገኖችን እንኳን በገዥው ስም በመጥራት ስማቸውን የምናጠለሽ ወንድም ወንድሙን ገድሎ የሚፎክርበት የጨለማ ጊዜ ነው። የቆሰለውና የሞተው እየተረሳ ዛሬም ኑ ለትግራይ ህዝብ እንሙት፤ ለአማራ ህዝብ እንሰዋ፤ የኦሮሞን ህዝብ ነጻ እናውጣ የሚሉን የፓለቲካ ድውያን ጊዜ እንደሚሮጥ አልተረድም። ህዝባችን በበሽታ፤ በረሃብ እያለቀ መሆኑ አይገባቸውም። እነርሱ ዘርፈውና ቀምተው ከርሳቸውን ሞልተው ይኖራሉና! ነጻ እናወጣሃለን የሚባለው ሰፊው ህዝብ ግን በስሙ ይነገድበታል። ማለቂያ የሌለው የመከራ ዶፍ ይወርድበታል። እንግዲህ አሁን ላይ በወያኔ መካከል ያለው የቃላት መወራወር ወደ ግድያና እስራት ከከፋም ወደ ጦርነት እንደሚለወጥ ለመገመት ጠንቋይ መጠየቅ አያስፈልግም። ተኩላ ሲበላላ ቀሬታ አይተውም። የፓለቲካ ውዥንብርም ሲወስድ ውሃ ያለ ልቡ እንደሚነዳው ሰው እያሳሳቀ ነው። እሣቱ ከተለኮሰ እፍ የሚለው ስለማይጠፋ ወያኔ ልብ ገዝቶ ነገሮችን በሰላም ለመፍታት ቢሞክር መልካም ነበር። ግን በግማሽ ምዕተ ዓመት እድሜው ያልተማረውን ነገር አሁን አምጣ ማለት ከለማኝ በራፍ የቆሎ ተማሪ ሆኖ እንደመለመን ይቆጠራል። ጊዜ ሁሉንም ያሳየናል። ችግሩ ጌታቸው አይደለም። ወያኔ በጥቅል እንጂ። ይመስለኛል የአሁኑ እሳት ከተለኮሰ እነርሱንም ጭምር የሚልስ ይሆናል። አይጥ ለሞቷ እንዲሉ…!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የቴሌኮም ጌትዌይ፣ የዳታ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ደህንነት – የዌብስፕሪክስ ጉዳይ ከባለቤትነት ክርክር በላይ ነው! November 17, 2026 11:54 pm
  • “የጫካ ቱጃሮች!”— የፋኖ አመራሮች ስለተሰማሩበት የገንዘብ ዝርፊያ አስደንጋጭ መረጃ November 17, 2026 05:43 pm
  • በየወሩ 4 ሚሊዮን ብር እየተከፈለው ሀገር ሲያፈርስ የነበረው ሪፖርተር November 16, 2026 01:17 am
  • ሻርኮቹ ከውጭ እስከ ሀገር ውስጥ ያደሩት ድር፣ ዌብስፕሪክስን (WebSprix) የመጠቅለሉ ድራማና ብሔራዊ ስጋት November 14, 2026 12:42 am
  • የመለስ ዜናዊን ጭንብል የገፈፈው የትህነግ ሚዲያ (EMF) ምስክርነት November 13, 2026 03:32 pm
  • ትህነግ በወታደራዊና በፖለቲካዊ መስክ እንደሞተ ሁሉ በሪፖርተር በኩል የሚዲያ ግብዓተ መሬቱ ተፈጽሟል November 13, 2026 01:13 am
  • በከባድ ታክስ ማጭበርበር የሚፈለጉት አቶ አበባው ደስታ፣ አማራጭ የቴሌኮም ጌትዌይ ፕሮጀክትን ሊጠቀልሉ ነው November 12, 2026 03:50 am
  • “ፋኖ ወደ ኦሮሚያ ገብቶ ሕዝብ እየገደለ ነው” የኦነግ ሸኔ (OLF/OLA) ተወካይ ጃል ጅረኛ November 10, 2026 05:12 pm
  • ከትህነግ የተማረኩና ከውጭ ሀገራት የገቡ ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች በቃሊቲ ለእይታ ቀረቡ November 6, 2026 03:36 pm
  • የመንግሥት ኃላፊዎች ወደ ሁርሶ የተወሰዱበት ምሥጢር November 5, 2026 12:43 pm
  • መንግሥት ሰማ፤ ሪፖርተር ተዘጋ፤ ግን ለምን? ምሥጢሩ ምንድነው? November 3, 2026 12:09 am
  • ኢትዮጵያ በሰማይ ላይ ነዳጅ የሚሞሉ የኢሉሺን (Il-78) አውሮፕላኖችን ከሩሲያ ልትገዛ ነው October 30, 2026 08:57 am
  • ካይሮ ያጣችውን የሩሲያ ጄቶች አዲስ አበባ የታጠቀችበት ምሥጢር October 29, 2026 10:26 am
  • ኢትዮጵያ ሱ-35 ተዋጊ ጄቶች እና የኤስ-400 ዘመናዊ የአየር መከላከያ ስርአት በመታጠቅ ከሰሃራ በታች ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች October 28, 2026 11:00 am
  • ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በ“ካሚካዜ” ድሮኖች ለመምታትና በዘር ግጭት ለማፍረስ ሰፊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተሰማ October 27, 2026 11:14 pm
  • ጆን መዲድ “ቀዝኖ እና ልብሱ ተበላሽቶ” ነው መከላከያ የማረከው October 27, 2026 08:41 pm
  • በጆን መዲድ መማረክ አደረጃጀቱ እየተፈረካከሰ በመሆኑ እነ ወዲ እምበይተይ፣ ምግበይ፣ ቀጣዮች ሊሆኑ ይችላሉ October 27, 2026 09:17 am
  • ከታክስ ስወራ እስከ ሐሰተኛ ጋብቻ፦ በኢትዮጵያ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊ ዳያስፖራዎችን ለማደን የተዘረጋው አዲሱ የአሜሪካ መረብ October 21, 2026 09:26 am
  • ኔታንያሁ የሶማሊላንድን ሉዓላዊነት ያረጋገጠ አዲስ ቀጣናዊ ካርታ ይፋ አደረጉ October 20, 2026 03:20 pm
  • ትውልደ ሶማሊያዊቷ ናፊሳ በተዘቀዘቀ የአሜሪካ ሠንደቅ ፊት በሶማሊኛ ምርጫ ቅስቀሳ ማድረጓ ቁጣ ቀሰቀሰ October 20, 2026 09:21 am
  • በአሜሪካ የሚገኙ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊዎች ላይ የተደቀነው አዲስ ስጋት October 19, 2026 08:58 pm
  • ዜግነት ሊያሰርዝ በሚችለው የኢልሃን ዑመር ምርመራ ላይ አዳዲስ መረጃ ተገኝቷል October 19, 2026 04:45 pm
  • በትግራይ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ስም በአስቸኳይ ሊቀየር ይገባል! October 19, 2026 02:55 am
  • በትግራይ ሕዝብ ደም የሚደረገው የሥልጣን ቁማር ያብቃ! October 14, 2026 11:04 pm
Copyright © 2026 · Goolgule