በትግራይ የተኩስ ማቆም ስምምነት መደረጉን ተከትሎ ያኮረፈው ሻዕቢያ ከግብጽ በወሰደው ውክልና “አንጃ” ከሚባለው የትህነግ ውስን ኃይልና በአማራ ኦሮሚያ ክልል ጠብ መንጃ ካነሱ ኃይሎች ጋር ግንባር ገጥሞ ኢትዮጵያ ምድር ላይ ሊከፍት ያሰበውን ውጊያ በአቅም ማነስና ምድር ላይ ባሉ እውነታዎች አስገዳጅነት ለማራዘም መወሰኑ ተሰማ። የኤርትራን የጦርነት ዝግጅት ከውስጥና ከውጭ የሚከታተሉ የኢትዮሪቪው የመረጃ ሰዎች እንዳሉት፣ ከግብጽ በወሰደው ውክልናና ከግል ስጋቱ በመነሳት ከኤርትራ ውጭ በኢትዮጵያ ግዛት ሊጀመር ያሰበውን ጦርነት ለማቆየት የወሰነው ምድር ላይ ባሉ አስገዳጅ ሁኔታዎች ሳቢያ ዓቅሙ እንደማይፈቅድ ተረድቶ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት “ጦርነት አንፈልግም። ከነኩን ግን ምላሹ የከፋ ይሆናል” ማለቱ የሚታወስ ነው። እንደ ዜናው ሰዎች ከሆነ የመጀመሪያው ምክንያት በትግራይ … [Read more...] about ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው
Isayas Afewerki
መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን!
የመለስ ዜናዊ የግል ጠባቂ/አጃቢ የነበረው ሚኪ ራያ ሰሞኑን በማኅበራዊ ሚዲያ በተሰራጨ ቪዲዮ ላይ የቀድሞ ጌታውን ማንነት ባልታወቀ ምክንያት እያዝረከረከው ነው። በትግሪኛ የተናገረውን አስፋው አብርሃ በቴሌግራም ገጹ ተርጉሞ አቅርቦታል፤ መለስ ዜናዊና ስብሃት ነጋ ከኢትዮጵያ በበለጠ ለኤርትራ ያስቡና ይጨነቁ ነበር። ይህ የሁለቱ ሰዎች ስሜትና ባህሪ በተለያዩ አጋጣሚዎች ተገልጧል - ከ1992ቱ ጦርነት በፊት፣ በጦርነቱ ወቅት እና ከጦርነቱ በኋላ ምንም ያልተቀየረ ስሜት! ከጦርነቱ በፊት .... ሚኪ ራያ "መለስ ዜናዊ መዝናናት ሲፈልግ ወደ አስመራ ይመላለስ ነበር፤ በረራውም Unofficial በረራ ነበር ይለናል - ያው በድብቅ ማለት መሆኑ ነው። “መለስ ዜናዊ ከስራ ውጪ መዝናናት ሲፈልግ አስመራ ነበር የሚሄደው። የራሱን ሰዎች ብዙም … [Read more...] about መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን!
አሜሪካ ኢሳያስንና ሻዕቢያን የማስወገድ ዓላማዋን ይፋ አድርጋለች
የሻዕቢያና የኢሳያስ አፈወርቂ ማብቂያቸው እየተቃረበ ይመስላል። ይህንኑ የሚያረጋግጡ ምልክቶች እዚያም እዚህም እየተሰሙ ነው። በተለይም ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር የመመለሷን ጉዳይ አጥብቀው በሚፈልጉ ጡነቸኞቹ አገራት ዘንድ አቋም የተያዘ ይመስላል። በኢትዮጵያ ሕዝብ ፍጹም የማይፍለገውን ትህነግን እንደ ሕጻን አዝላ የኖረችው አሜሪካ አሁን ላይ ሁለቱም እንደ አመጣጣቸው እንዲሰናበቱ አቋም ስለመያዟ ከምልክት በላይ መረጃዎች እየወጡ ነው። ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተን ኢሳያስን፣ መለስን፣ ሙሴቪኒንና ካጋሜን አንድ ላይ "የአዲሱ ትውልድ መሪዎች" ብለው ለምስራቅ አፍሪቃ ሲያጩ በድጋፍ ስልጣን ላይ የመጡት ሻዕቢያና ወያኔ ካርዳቸው አልቋል። አሁን ላይ ኢትዮጵያ የገነባችው ኃይልና ዘመናዊ የውትድርና ቴክኖሎጂ ሻዕቢያን ለማስወገድ ከትህነግ በላይ አስተማማኝ በመሆኑ አሜሪካ ትህነግን መሽከም … [Read more...] about አሜሪካ ኢሳያስንና ሻዕቢያን የማስወገድ ዓላማዋን ይፋ አድርጋለች
ወደ ኤርትራ በኮንትሮባንድ የሚሻገሩ ቆሳቁሶች እየተያዙ ነው
ከኤርትራ ጋር በተያያዘ የኮንትሮባንድ ጉዳይ መላ እንዲበጅለት ዜጎች እየጠየቁ ነው ከኢትዮጵያ በኮንትሮባንድን በመላላክ ወደ ኤርትራ የሚሸጋገሩ ቁሳቁሶች የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እየጎዳ መሆኑ፣ በሕዝብ የእለት ተእለት ፍጆታ ላይም ተጸዕኖ እያሳደረ መሆኑን የሚያውቁ መንግሥት መላ ሊፈልግ እንደሚገባ እያሳሰቡ ነው። በትግራይ ክልል በሕዝብ ቁጥጥር በአንድ አቅጣጫ ብቻ በሶስት ወር ውስጥ ከአራት ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ መያዙ ተገልጿል። በውጭ ገንዘብ ምንዛሬ፣ በግንባታና በዕለታዊ ፍጆታ ዕቃዎች ላይ በስፋት ኮንትሮባንድ ላይ የተሰማሩና የኤርትራ መንግሥት ድጋፍ የሚያደርግላቸው ክፍሎች የአገሪቱን ኢኮኖሚ እየተፈታተኑት እንደሆነ የሚገልጹ ወገኖች “ወዳጅነትና የኮንትሮባንድ ዝርፊያ ለየቅል ናቸው” ሲሉ መንግሥት መስመር ሊያስይዘው እንደሚገባ አመልክተዋል። ቀደም ባሉት … [Read more...] about ወደ ኤርትራ በኮንትሮባንድ የሚሻገሩ ቆሳቁሶች እየተያዙ ነው