• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ወደ ኤርትራ በኮንትሮባንድ የሚሻገሩ ቆሳቁሶች እየተያዙ ነው

August 11, 2023 12:52 pm by Editor 1 Comment

ከኤርትራ ጋር በተያያዘ የኮንትሮባንድ ጉዳይ መላ እንዲበጅለት ዜጎች እየጠየቁ ነው

ከኢትዮጵያ በኮንትሮባንድን በመላላክ ወደ ኤርትራ የሚሸጋገሩ ቁሳቁሶች የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እየጎዳ መሆኑ፣ በሕዝብ የእለት ተእለት ፍጆታ ላይም ተጸዕኖ እያሳደረ መሆኑን የሚያውቁ መንግሥት መላ ሊፈልግ እንደሚገባ እያሳሰቡ ነው። በትግራይ ክልል በሕዝብ ቁጥጥር በአንድ አቅጣጫ ብቻ በሶስት ወር ውስጥ ከአራት ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ መያዙ ተገልጿል።

በውጭ ገንዘብ ምንዛሬ፣ በግንባታና በዕለታዊ ፍጆታ ዕቃዎች ላይ በስፋት ኮንትሮባንድ ላይ የተሰማሩና የኤርትራ መንግሥት ድጋፍ የሚያደርግላቸው ክፍሎች የአገሪቱን ኢኮኖሚ እየተፈታተኑት እንደሆነ የሚገልጹ ወገኖች “ወዳጅነትና የኮንትሮባንድ ዝርፊያ ለየቅል ናቸው” ሲሉ መንግሥት መስመር ሊያስይዘው እንደሚገባ አመልክተዋል።

ቀደም ባሉት ወራት በድንገት በተደረገ አሰሳና በክትትል በተሠራ ሥራ በሚሊዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሬ መያዙን ያስታወሱ፣ ከነማን ላይ እንደተያዘ በስም መጥቀስ ባይፈልጉም ውንብድናው በወዳጅነት ስም ሽፋን የተሰጠውና በኤርትራ መንግሥት ደረጃ የሚታወቅ እንደሆነ ይጠቁማሉ።

ሻዕቢያ በረሃ እያለ አዲስ አበባና የተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያስነግድ እንደነበር በማስታወስ የአሁኑ መጠኑና ዓይነቱ ከመጨመሩ ውጭ ተመሳሳይ እንደሆነ ያመለክታሉ። መንግሥት ይፋ ባይናገርም ጥብቅ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የሚያውቁ “ቡና እየዘረፈ ከአፍሪካ አንደኛ ቡና ላኪ ሆኖ የነበረው የሻእቢያ መንግሥት እንዳሻኝ ካልዘረፍኩ በሚል ማኩረፉን እናውቃለን። ምን አልባትም በአማራ ክልል በድንገት የነደደው ጦርነት የዚህ ኩርፊያ ውጤትም ጭምር ሊሆን ይችላል” ብለዋል።

በሰሜን ኦምሃጀር በኩል የቅባት ዕህል፣ የምግብ መርቶች ጤፍን ጨምሮ ወደ ኤርትራ እንደሚጋዝ፣ የጎጃም አካባቢ ነጋዴዎች ምርታቸውን ወደ መሃል አገር ከሚልኩ ወደ ኤርትራ ለሚያጓጉዙ እንዲሸጡ ይደረግ እንደነበርና አሁን ላይ ቢቀንስም እንዳልቆመ የሚጠቁሙ ወገኖች በጦርነቱ አማካይነት የፈረሱና የተዘጉ ኬላዎች ዳግም መቋቋም ኮንትሮባንዱን በትሥሥር ለሚቀበሉት ክፍሎች ደስታን አልፈጠረም።

ቲክቫህ ትግራይ በመሄድ በዛላንበሳ በኩል ብቻ ሕዝብ ተባብሮ ቁጥጥር በማድረግ የያዛቸው ወደ ኤርትራ ሊጓጓዙ የነበሩ የኮንትሮባንድ ቁሳቁሶች፣ ከተያዘው በላይ ያልተያዘውን በማስላት ኢትዮጵያ እንዴት እየታለበች መሆኑንን የሚያሳይ ሆኖ ተወስዷል።

በኢትዮጵያ የቀለብ ዕህልና ቁሳቁሶች፣ የግንባታ ግብአትን ጨምሮ በዋጋ መናር ሕዝቡን እያሰቃየ ባለበት በአሁኑ ሰዓት፣ ኢትዮጵያ ዶላር የምታፈስበት ነዳጅ፣ ዘይትና የግንባታ ብረትን ጨምሮ ቡናና የምግብ ምርቶች ወደ ጎረቤት አገር በኮንትሮባንድ እንደሚጋዝ መንግሥት ማስታወቁ አይዘነጋም። (ethio12)

ቲክቫህ ያጠናቀረው የኮንትሮባንድ ሪፖርት ከዚህ በታች ይገኛል።

ከግንቦት እስከ ሐምሌ / 2015 ከትግራይ ወደ ኤርትራ በህገ-ወጥ መንገድ ሊሻገሩ የነበሩ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የቲክቫህ መቐለ ቤተሰብ አባል በድንበር አከባቢ ያለውን ሁኔታ በሚመለከት የሚመለከታቸውን አካላት ለመጠየቅ ወደ “ጉሎመኻዳ ወረዳ” አቅንቶ ነበር። የጉሎመኻዳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሃፍቶም ባራኺ ለቲክቫህ የመቐለ ቤተሰብ በሰጡት ቃለመጠይቅ ፤ “የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ሊያዙ የተቻሉት በህዝብ የነቃ ተሳትፎ በመታገዝ ነው” ብለዋል።

አቶ ሃፍቶም፤ የትግራይ ኢትዮጵያዋ የጉሎመኻዳ ወረዳ ሰፊ አከባቢ ከሃገረ ኤርትራ የሚዋሰን በመሆኑና በጦርነቱ ምክንያት በዛላኣንበሳ ከተማ የነበረው የቁጥጥር ኬላ በመፍረሱ የተለያዩ እቃዎች በኮንትሮባንድ መልክ ወደ ኤርትራ ይተላለፋሉ ሲሉ ገልጸዋል።

“ዛላኣምበሳ ጨምሮ የወረዳው ስድስት ቀበሌዎች በኤርትራ መንግሥት ቁጥጥር ሥር ይገኛሉ” ያሉት አቶ ሃፍቶም፤ በዚሁ በኩል ወደ ኤርትራ ለማሸጋገር የሚደረግ ህገ ወጥ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠርና ለመግታት እንዲቻል ህዝቡ ባለቤት በመደረጉ ምክንያት አመርቂ ውጤት እየተገኘ እንደሆነ ለቲክቫህ አስረድተዋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ የሰጡት የዞኑ የፀጥታ ጉዳይ ሃላፊ አቶ ኪዱ ገ/ፃድቃን እንዳሉት፤ ከግንቦት እስከ ሃምሌ 2015 ዓ.ም  የ4 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው መሰረታዊ ሸቀጦችና የኢንዱስትሪ መሳሪዎች በህገ-ወጥ ኮንትሮባንድ ወደ ኤርትራ ሊሻገሩ ሲሉ ተይዘዋል ብለዋል።

የተያዙት ፦

  • ጤፍ፣
  • የፊኖ ዱቄት፣
  • ቡና፣
  • የመብል ዘይት፣
  • ነዳጅ፣
  • የሞባይል ቆፎዎች፣
  • ጌሾ፣
  • በርበሬ፣
  • የቤት እቃዎች፣
  • ዘመናዊ ማዳበሪያ፣
  • ስሚንቶ፣
  • ቴንዲኖና የቤት ክዳን ቆርቆሮ መሆኑን ገልጸዋል።

ጉሎመኸዳና ኢሮብ ከኤርትራ የሚዋሰኑ የምስራቃዊ ዞን ወረዳዎች መሆናቸው የጠቀሱት አቶ ኪዱ፤ ብዘት ዳሞ፣ ፋፂ ዛላኣምበሳ፣ ሰበያ፣ ደውሃን ዓይጋ የሚባሉት ቦታዎች ዋና የህገወጥ ኮንትሮባንድ መተላለፊያ መስመሮች መሆናቸው ገልፀዋል።

የፀጥታ ጉዳይ ሃላፊው፤ ህዝቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በህገ-ወጥ መንገድ በኮንትሮባንድ የሚሻገሩ ንብረቶች በመቆጣጠር ረገድ ሚናው የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል።

የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ስፍራው ድረስ በመሄድ የአካባቢው ኃላፊዎች ፦

  • የኮንትሮባንድ ዝውውር እንዴት እየተፈፀመ እንዳለ
  • በኤርትራ ኃይል ስር ስላሉት አካባቢዎች
  • በአካባቢው ስላለው የህገወጥ ሰዎች ዝውውር
  • በጦርነት ምክንያት ስለወዳደቁ ብረቶች

የኮንትሮባንድ ዝውውርን ለመከለከል ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር እየተሰራ ስላለው የጋራ ስራ የሰጡትን ቃል በተከታታይ የሚያቀርብ ይሆናል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Left Column, News Tagged With: controband, Eritrea, human trafficking, Isayas Afewerki, poorest country in the world, Poverty in Eritrea

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    August 11, 2023 07:40 pm at 7:40 pm

    ኤርትራ በለው ከቁራሽ ተራፊዋ ኢትዮጵያ በየዘመናቱ ስንገለባበጥ የኖርን ህዝቦች ነን። ገድላችንና ስኬታችን የሚለካው በሌላው ወገናችን ላይ በምናደርሰው የመከራ ዝናብ ነው። ያኔ 30 ዓመት ተፋልመው በግብጽ፤ በኢራን፤ በሊቢያና በሱዳን እንዲሁም በሶሪያ፤ በኢራቅ በሌሎችም ተደግፈው ኢትዮጵያን ንደው ዛሬ ኤርትራን የመሰረቱት ኤርትራዊያን ምድሪቱን ሰው የማይኖርባት ስላደረጓት አዲሷ ኤርትራ ከአሮጌውም የከፋ እንደሆነች እውነት ራሷ ትመሰክራለች። የሚያሳዝነው እልፍ ሰው ተሰዶ በዓለማቱ ሁሉ ፈልሶ ዛሬም ስለ ኤርትራም ሆነ ስለ ኢትዮጵያ ገናናት ሰዎች ሲያወሩ ግርም ይሉኛል። ሃበሻ ማለት እውነት አይኗን አፍጣ እውነቱን እያሳየችው ሜዳውን ገደል ነው ገደሉን ሜዳ ነው የምንል ፍጡሮች ነን። ለዚያም ነው ፌሲቲቫል ኤርትራ በሆነበት ሰው ሁሉ ኤርትራዊያን ተከፍለው የሚፋለሙት። የፓለቲካራ አቲካራ እስከ መቃብር ድረስ የሚያንገላጅጅ በሽታ በመሆኑ መድሃኒት የለውም።
    የእህል ምግቦችም ሆነ ሌላው ነገር ከኢትዪጵያ ወደ ኤርትራ መሄድ መልካም እንጂ ክፉ ነገር አይደለም። ፓለቲካው የከፈለውን ህዝባችን ምን አልባት ንግድ ያቀራርበው ይሆናል። ድባ በማያበቅል ምድር ባድሜ ገለመሌ እያሉ ከመጨራረስ በጤፉና በበርበሬው ንግድ ሳቢያ እየተገናኙ ሃሳብ ለሃሳብ መለዋወጡ በዚህም በዚያም የቆሰለውን ነገር ሁሉ ለመርሳት ይረዳ ይሆናል። ግን ያው ህገወጥ እቃ ተያዘ ሲባል ከማን ኪስ እንደገባ እናውቃለን። ዛሬም ጠበንጃ አንግተው በስማችን በሚነግድ ሙታን ፓለቲከኞች እጅ ገብቶ ዞሮ ተመልሶ ለገቢያ ይቀርባል። ለዚህ ነው የሃበሻው ፓለቲካ ፍሬፈርስኪ ነው የምንለው። የብሄር ነጻነቱም ወንዝ የማያሻግር የውሸት ቱልቱላ ነው። ተገንጣይ ሃገሮች ከአውሮፓም ሆነ ከአፍሪቃ ለህዝባቸው ያስገኙት ነገር መከራና ስደት ብቻ ነው።
    አሁን እንሆ የወያኔ ትራፊዋን የሃበሻ ምድር የኦሮሞ ጽንፈኛ ፓለቲከኞች ተረክበው በጊዜአቸው ተሽከርክረው ራሳቸውንም ያሽከረክራሉ። ትላንት የትግራይ ልጆች ይህን ሰሩ ያን በዘርና በቋንቋ ተገን አበጅ ሰራዊቱን ሁሉ በራሳቸው ሰው ሞሉት እያለ የነገረን ጠ/ሚ አብይ አሁን ደግሞ የፌዴራል መ/ቤቶች 45% በኦሮሞ ልጆች መያዝ አለባቸው ይለናል። እውቀት፤ የሥራ ውጤት፤ የትምህርት ደረጃ ሌላውም ገደል ገብቷል። በዘሩና በቋንቋው እየተገፋ ወንበር ላይ ቁጢጥ ነው። ይህ ከወያኔ አሰራርና አመራር ይሻላል የሚሉ ሁሉ በዘር ጥላቻ ልባቸው የተደፈነ እውራን ብቻ ናቸው። የፓለቲካው ሴራ ለገባውና ለተረዳ ግን በወያኔ 3 ጊዜ የተወረረው አማራና አፋር ክልል ሆን ተብሎ የተደረገ እርስ በእርሳችን እንድንጨራረስ የኦሮሞ ፓለቲከኞች ወያኔን ለማዳከም በቀጥታና በተዘዋዋሪ የለኮሱት እሳት እንደሆነ አሁን በግልጽ ይታያል። ለዚያ ነው ያኔ ኑ ድረሱልኝ ያላቸውን ፋኖዎችና የአማራ ልዪ ሃይልን አሁን ሽፍታና ዘራፊ እያለ ዛሬ ላይ የብልጽግናው መንግሥት በማሳደድ ላይ የሚገኘው። ይህ ሲባል ፋኖ የፓከቲካ ስህተት አልሰራም፤ በዚህም በዚያም ሰውን አይተናኮልም ማለቴ አይደለም። የእኔ ሃሳብ አፍራሽን አፍራሽ እየተካው ሁሌ በተውሶ መሳሪያ እየተገዳደልን የምንኖረው እስከ መቼ ነው?
    ባጭሩ የኤርትራው የቅርብ ጊዜ ነጻነት የኢትዮጵያም የ 3ሺ ዘመን የነጻነት ቆጠራ እንኩሮ ነው። ለህዝባችን ሰላም፤ ብልጽግና፤ የዲሞክራሲ መብቶች የነፈገ አፋኝ/ገዳይ/ አፈናቃይ/ጨቃኝና በዘርና በቋንቋ ፓለቲካ የተሳከረው የ 60 ዎቹ ፓለቲከኞች እኛ እንሻላለን እያሉን ዛሬም በሞት አፋፍ ላይ ሆነው ክፋትና ተንኮልን መከፋፈልን ሲያውጅ መስማት ይዘገንናል። ልብ ያለው የሃበሻውን ፓለቲካ አንቅሮ ይተፋል። በወረፋ የመተሳሰርና የመገዳደል ፓለቲካ ለማንም ለምንም አይጠቅምም። ይልቅስ በዚህም በዚያም ሰውን ከማመሳቀል ሰው ሰርቶ እንዲበላ ሰላም እንስጠው። ወደ ኤርትራ በኮንትሮባንድ ስም የሚገባውንም ቁሳቁስ ህጋዊ በሆነ መልኩ እንዲገባ ካለበለዚያም ሰው በመረጠው መንገድ እንዲገበያይ መተው ነው። እንደዛሬው ሳይሆን ድሮ ገና ዶ/ር፤ ኢንጂኒየር ገለ መሌ እያሉ መሳሪያ ታጥቀው ሳያሸብሩን ህዝባችን የኖረው አንድ ያለውን አቅርቦ የሌለውን ካለው ላይ ሸምቶ ነው የኖርነው። እባካችሁ ህዝባችን አታሰቃዪ! በቃኝ!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule