አቶ ፍፁም አባዲ በኢትዮጵያ አየርመንገድ የካርጎ ክፍል ሃላፊ፣ ምክትሉ አቶ ናትናኤል ጎበና እና የጌታቸው አሰፋ የቅርብ ዘመድ የሆነው አቶ ዮሃንስ አረጋይ በአየርመንገዱ የካርጎ ክፍል የሚሰሩ “የጌታቸው አሰፋ ትሬዲግ” ሰራተኞች ናቸው። በዱባይና ቻይና የሚገኙ የኢትዮጵያ አየርመንገድ የጭነት ወኪሎች፣ የቦሌ ጉሙሩክ ሃላፊ ከነበረው ከአቶ ገብረማርያም እስከ ጥበቃ ክፍል ሰራተኞች የሚደርሰው ሰንሰለት የጌታቸው አሰፋ የኮንትሮባንድ ንግድ ሰንሰለት ነው። እነ ጌታቸው አሰፋ ከስልጣን የተወገዱበትን ሚስጥር፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ በህወሓቶች ስለሚፈፀመው ዘረፋና የኮንትሮባንድ ንግድ በተጨባጭ ማስረጃ የተደገፈ መረጃ ይፋ ወጥቷል። “የጌታቸው አሰፋ ትሬዲንግ” ከሶስት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የ800 ሚሊዮን ብር ኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በአየርመንገድ በኩል ግብር ሆነ ታሪፍ … [Read more...] about “ጌታቸው አሰፋ ትሬዲንግ” በቢሊዮን የሚቆጠር የኮንትሮባንድ ዕቃዎች አስመጪና አከፋፋይ!
controband
ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ!
የጦር መሳሪያ ጨምሮ ሌሎች ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በዚህም፡- 18 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለው ደረቅ ጫት፣ እህል፣ ትምባሆ እና ሌሎች ዕቃዎች በተለያዩ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ እና መቅረጫ ጣቢያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ 13 ሚሊዮን በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለውና 8,980 ኪ.ግ መጠን እንዳለው የተገለጸው ደረቅ ጫት በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ኬንያ ሲጓጓዝ የተያዘ ነው፡፡ ከሱማሌላንድ ወደ ጅጅጋ ሊገቡ የነበሩ ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች እንዲሁም በቀብሪበያህ በኩል በኤፌሳር እና ሚኒባስ ተጭኖ ሊገባ የነበረ የውጭ ሀገር ማሽላ እና ዘይት 3,500,000 ብር አጠቃላይ ግምታዊ ዋጋቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡በኢትዮጵያ ለሚገኙ ለደቡብ ሱዳን … [Read more...] about ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ!
ግምታቸው 14 ሚሊዮን ብር የሚጠጉ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ
በተለያዩ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎችና ኬላዎች ከ13 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ። የተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ሳይፈፀምበት ከመስከረም 4 እስከ 9/2013 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል። ሚኒስቴሩ እንደገለጸው ወደ ሀገር ሊገባ የነበረ ማሽላና ስንዴ፣ ወደ አዲስ አበባ ሲጓጓዝ የነበረ ሲጋራ፣ በሕዝብ ማመላሻ ሚኒባስ ሲጓጓዝ የነበረ የሽጉጥ ጥይት፣ በጭነት ተሸከርካሪ ሲጓጓዝ የነበረ የክላሽ ጥይትና የሞባይል ስልኮች ይገኙበታል። በተጨማሪም ከሀገር ሊወጣ ሲሉ የተያዙ የቁም ከብቶች፣ የብር ጌጣጌጥ፣ የአሜሪካ ዶላርን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች፣ ልባሽና አዳዲስ አልባሳት ይገኙበታል። የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ … [Read more...] about ግምታቸው 14 ሚሊዮን ብር የሚጠጉ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ
ግምታዊ ዋጋቸው ከ5 ሚሊየን በላይ የሆኑ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ!
ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሚኤሶ ወረዳ አሰቦት የተነሳውና የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3-50725/04585 ኢት ቦቴ የነዳኝ መኪና በሁለቱም የነዳጅ ታንከር ውስጥ ከ5 ሚሊየን በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ጭኖ ሳለ በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡ ብዛቱ 23,750 ስቴካ ሻምላን (SHAMLAN) ሲጋራ፣ 863 ስቴካ ሺሻ ጭኖ ወደ ሚሌ መስመር በመጓዝ ላይ እያለ ነው ከህዝብ በደረሰ ጥቆማ አፋር ክልል አዋሽ አርባ ላይ በፌዴራል ፖሊስና የጉምሩክ መረጃ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር የዋለው። ንብረቱም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ገቢ መደረጉን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል። መነሻውን ምዕራብ ሐረርጌ ዞን፣ ሚኤሶ ወረዳ አሰቦት ያደረው ነዳጅ ጫኝ ተሸከርካሪ በሁለቱም የነዳጅ ታንከሮቹ ውስጥ ስቴካ … [Read more...] about ግምታዊ ዋጋቸው ከ5 ሚሊየን በላይ የሆኑ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ!