በደብረ ማርቆስ ከተማ ከ6ሺ ኩንታል በላይ በቆሎ በአንድ ግለሠብ መጋዘን ውስጥ ተከዝኖ ተገኘ።
በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ ዐ5 ልዩ ቦታው ኢንዱስትሪ መንደር ውስጥ በሚገኝ ለሙጫና እጣን ማቀነባበሪያ መጋዘን ውስጥ ከ6ሺ ኩንታል በቆሎ በላይ ተከዝኖ መገኘቱን የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ገልጿል።
የተገኘውን እህል በከተማው ለሚገኙ አስራ አራት ሸማች ህብረት ስራ ማህበራት እንደሚከፋፈል እና በዛሬው ዕለት ሁለት ሸማች ማህበራት ከአራት መቶ በላይ ኩንታል መውሰዳቸውን እና ለህብረተሰቡ እንደሚከፋፈል የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ብርሀኑ መኩሪያው ገልጸዋል።
የወንጀሉ ጉዳይም ፖሊስ አስፈላጊውን ምርምራ እያጣራ መሆኑን አስረድተዋል። (የደብረ ማርቆስ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply