በርካታ ሞባይሎችን፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችንና ሌሎች ቁሳቁሶችን በሕገ-ወጥ መንገድ በመኪና ሻግ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለፀ።
በርካታ ሞባይሎችን፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችንና ሌሎች ቁሳቁሶችን በመኪና ሻግ በሕገ-ወጥ መንገድ ጭነው ሲያዘዋውሩ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገለፀ።
ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ለጊዜው ባለቤቱ ባልታወቀ ተሽከርካሪ 202 ፍየሎችን ከላይ፣ ከሥር ደግሞ በርካታ ሞባይሎችን፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ መድሃኒቶችን እና የብር ጌጣጌጦችን በሻግ ጭነው ከያቤሎ በመነሳት አዲስ አበባ ከተማ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ብርጭቆ ፋብሪካ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እንደደረሱ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር ባደረገው ብርቱ ክትትል ከነ-ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኙ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገልፀዋል።
የወንጀል አፈፃፀም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየረቀቀ ቢመጣም የፀጥታ ተቋማት ከዘመኑ ጋር አብሮ እየዘመኑ ወንጀል ፈፃሚዎችን በቁጥጥር ሥር እያዋሉ ሲሆን ኅብረተሰቡም ከተቋማቱ ጎን በመቆም የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪውን ያቀርባል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply