አቶ ፍፁም አባዲ በኢትዮጵያ አየርመንገድ የካርጎ ክፍል ሃላፊ፣ ምክትሉ አቶ ናትናኤል ጎበና እና የጌታቸው አሰፋ የቅርብ ዘመድ የሆነው አቶ ዮሃንስ አረጋይ በአየርመንገዱ የካርጎ ክፍል የሚሰሩ “የጌታቸው አሰፋ ትሬዲግ” ሰራተኞች ናቸው።
በዱባይና ቻይና የሚገኙ የኢትዮጵያ አየርመንገድ የጭነት ወኪሎች፣ የቦሌ ጉሙሩክ ሃላፊ ከነበረው ከአቶ ገብረማርያም እስከ ጥበቃ ክፍል ሰራተኞች የሚደርሰው ሰንሰለት የጌታቸው አሰፋ የኮንትሮባንድ ንግድ ሰንሰለት ነው።
እነ ጌታቸው አሰፋ ከስልጣን የተወገዱበትን ሚስጥር፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ በህወሓቶች ስለሚፈፀመው ዘረፋና የኮንትሮባንድ ንግድ በተጨባጭ ማስረጃ የተደገፈ መረጃ ይፋ ወጥቷል።
“የጌታቸው አሰፋ ትሬዲንግ” ከሶስት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የ800 ሚሊዮን ብር ኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በአየርመንገድ በኩል ግብር ሆነ ታሪፍ ሳይከፍል ያስገባ መሆኑን፣ ከቦሌ እስከ መርካቶ ላሉት የኤሌክትሮኒክስ ቤቶች፣ ካዛንቺስ ለሚገኙት የጽህፈት መሣሪያ መደብሮች፣ ለፒያሳ ወርቅ ቤቶች የሚሸጡትን ዕቃ የሚያቀርበው “ጌታቸው አሰፋ አስመጪና አከፋፋይ” ነው።
አዲስ አበባ ውስጥ የሚሸጡት የወንድ ሱፍ ልብሶች፣ ትሪደንት ማስቲካ፣ 22 አካባቢ የሚጨሰው ሺሻና የሚሳበው ኮኬይን፣ ከቦሌ እስከ አራት ኪሎ የሚገኙት የኮምፒውተር፣ ሞባይልና ሌሎች ኤሌክትሮኒክስ መለዋወጫዎች አቅራቢ ይሄው ድርጅት ነው።
ሌላው ቀርቶ ተክለሃይማኖት የሚገኙት የመኪና መለዋወጫ እና የመኪና ጎማ መሸጪያ ቤቶች ዋና አስመጪና አከፋፋይ በጌታቸው አሰፋ የሚመራው የኮንትሮባንድ ድርጅት ነው።
“ጌታቸው አሰፋ መቀሌ ተደብቋል፣ የተባለውም የኮንትሮባንድ ንግድ ተቋርጧል” የሚለውን ሃሳብ የሚከሽፍ መረጃ ነው በዚህ ትንታኔ ላይ የቀረበው። የሚያስደንቀው ነገር የህወሓት መረብ እና የገንዘብ ቋቱ እንዳልደረቀ የሚያሳየው መረጃ መግቢያው ላይ የተጠቀሱት ሶስት የአየርመንገድ ኃላፊዎች አሁንም ሥራቸውን በመሥራት ላይ መገኘታቸው ነው።
በእርግጥ ቀድሞ የኮንትሮባንድ ዕቃ ወደ ሀገር ቤት ያስገቡ ነበር። አሁን ደግሞ የጌታቸው አሰፋን ዶላር በውድ ማዕድናት በመቀየር ወደ ውጪ በማሸሽ ላይ ይገኛሉ። ይሄ መረጃ ተራ አሉባልታ አይደለም። በራሱ በጌታቸው አሰፋ በሚመራው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት ሥር የነበሩ ጥቂት ሀገር ወዳዶች በህይወታቸው ከሞት እስከ እስራት የሚደርስ ውድ ዋጋ የከፈሉበት ነው።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply