
ኢትዮጵያ ማር ለማምረት የሚያስችል ያላትን ከፍተኛ ጸጋ በሚገባ እየተጠቀመች እንዳልሆነ ተነግሯል፡፡
ሃገሪቱ በአመት 500 ሚሊዮን ቶን ማር የማምረት አቅም ቢኖራትም እያመረተች ያለችው ግን 10 በመቶ ብቻ ነው ተብሏል፡፡ ይህም ሆኖ የምትመረተዋ አነስተኛ የማር ምርት በኮንትሮባንድ ወደ ውጭ እየወጣች መሆኑን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡
በተለያዩ የሃገሪቷ አካባቢዎች ገበሬዎች የሚያመርቱት የማር ምርት በትክክለኛው መንገድ ወደ ገበያ እየቀረበ ባለመሆኑ እና በኮንትሮባንድ ወደ ውጭ ስለሚወጣ ሃገሪቷን ገቢ እያሳጣት ይገኛል ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ምክትል ዳሬክተር አቶ ታሪኩ ተካ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ደላሎች አዛዥ በሆኑበት የማር ምርት ሃገሪቱ ማግኘት የሚገባትን ገቢ እንዳታገኝ አድርጓታል ብለዋል፡፡ የማር ምርት እና ግብይትን የሚመለከት መመርያም ሆነ አዋጅ ባለመኖሩ፣ የማር ምርት እና ግብይት አደጋ ላይ ወድቋል ሲሉም አክለዋል፡፡
ከዚህ በፊት ኢንስቲትዩቱ ለዘርፉ መመርያ እና አዋጅ እንደሚያስፈልገው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ እንደነበረ አስታውቆ፣ በምን ደረጃ ላይ እንደረሰ አይታወቅም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ይህ አለመፈጸሙ ደግሞ በግብይት ሂደቱ ላይ አሉታዊ ጫና እያደረሰ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡ በንብ ሃብት ኢትዮጵያ ከዓለም አስረኛ፣ ከአፍሪካ ደግሞ ቀዳሚ ብትሆንም የምታገኘው ገቢ ግን እጅግ አነስተኛ እንደሆነ አቶ ታሪኩ አንስተዋል፡፡ የማር ምርት ጥራትን ለማሳደግም ሆነ ከዘርፉ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግ ህገ-ወጥ የግብይት ሰንሰለቱም መቁረጥ እንደሚገባም ጠቅመዋል፡፡
ጎልጉል የደረገጽ ጋዜጣ
ሀገሪቷ ትክክለኛ የሞኒተሪና ፊሲካል ፓሊሲ ስለማትከተል፣ እንዲህ አይነት ህገወጥ እንግዶች ይበራከታሉ። ኢትዮጵያ ለሰላም፣ ለአንድነት ለእኩልነት ፣ ለህግ የበላይነት ለአጠቃላይ እድገት የሚተጋ ፣ በእውቀት የሚመራከዘረኝነት የፀዳ መንግስት እና የህዝብ አስተዳደር ያስፈልጋታል።