ኢትዮጵያ ማር ለማምረት የሚያስችል ያላትን ከፍተኛ ጸጋ በሚገባ እየተጠቀመች እንዳልሆነ ተነግሯል፡፡ ሃገሪቱ በአመት 500 ሚሊዮን ቶን ማር የማምረት አቅም ቢኖራትም እያመረተች ያለችው ግን 10 በመቶ ብቻ ነው ተብሏል፡፡ ይህም ሆኖ የምትመረተዋ አነስተኛ የማር ምርት በኮንትሮባንድ ወደ ውጭ እየወጣች መሆኑን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡ በተለያዩ የሃገሪቷ አካባቢዎች ገበሬዎች የሚያመርቱት የማር ምርት በትክክለኛው መንገድ ወደ ገበያ እየቀረበ ባለመሆኑ እና በኮንትሮባንድ ወደ ውጭ ስለሚወጣ ሃገሪቷን ገቢ እያሳጣት ይገኛል ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ምክትል ዳሬክተር አቶ ታሪኩ ተካ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ደላሎች አዛዥ በሆኑበት የማር ምርት ሃገሪቱ ማግኘት የሚገባትን ገቢ እንዳታገኝ አድርጓታል ብለዋል፡፡ የማር ምርት እና ግብይትን የሚመለከት … [Read more...] about ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል